>

ሽንፈቱን የደበቀው ሕወሓት ጦርነቱ ባጠረና በፈጠነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የቦታዎችና የግንባሮች ማሻሻያዎችን አድርገናል አለ

“ሕወሓት “የቦታዎችና የግንባሮች ማሻሻያ” ማድረጉን በመግለጫው አሳወቀ”
ኢትዮጵያን እናድን

*ሽንፈቱን የደበቀው ሕወሓት ጦርነቱ ባጠረና በፈጠነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የቦታዎችና የግንባሮች ማሻሻያዎችን አድርገናል አለ
 
ህወሓት ስርዝ-ድልዝ የበዛበት መግለጫ አውጥቷል። የመግለጫውን ሙሉ ይዘት ወደ አማርኛ ተርጉመን አቅርበናል ።
ከጠላቶቻችን ጋ የምናደርገው ሁሉን አቀፍ ጦርነት ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየደረሠ ነው። እስካሁን ባደረግነው ጦርነት ጠላት ከሚያደርሰው ጥፋት ከማድረስ አቅሙን ከማዳከም አልፈን ህልውናው ራሱ አደጋ ውስጥ እንዲገባ የሚያደርጉ ስትራተጂካዊ ድሎች አስመዝግበናል። ከሰኔ ወር ጀምረን ባደረግነው ጦርነት ጠላት ሰራዊቱ ላሽቋል፣ የነበረው የተኩስ አቁም ተመናምኗል፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ተዳክሟል ሁሉም ነገሩ የተዳከመና ለመውደቅ ያዘመመ መንግስት ሆኗል።
ሁሉንም የሰላም አማራጮች የዘጋው ፋሽሽት ሃይል በጦርነቱ ሽንፈትን እየተከናነበም ቢሆን አሁን ላይ የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ እየጣረ ነው። ይሄንን ሃይል እያጠፋነው ያለነው ሰላማችንን በክንዳችን ማምጣት የግድ ስለሆነ ነው።
እስካሁን ይዘናቸው የነበሩ አከባቢዎች ምንም እንኳ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታቸው ከፍ ያሉ ቢሆኑም አሁን ላይ የፋሽሽቱ ሃይልና የአማራ ተስፋፊዎች እየፈጠሩብን ካለው እንቅፋት ፈጥኖ መውጣት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። በዚህ ምክንያት ጦርነቱ ባጠረና በፈጠነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የቦታዎችና የግንባሮች ማሻሻያዎችን አድርገናል።
ይህም ሆኖ ጠላት እኛ ለስትራቴጂና ለተጨማሪ ማጥቃት የለቀቅናቸውን ቦታዎች አሸንፎ እንደያዘ አድርጎ ህዝብ እያደነቆረ ይገኛል። ጭራሹኑ የኛ ሃይል ያልነበረባቸውን ቦታዎች ሳይቀር አስለቀኳቸው እያለ እየጮኸ ነው። የካሜራ የመውደድ በሽታ የተጠናወተው ይሄ ፋሽሽት  ውሎ አዳሩ ፎቶ ላይ ሆኗል።  ለ30አመታት ታግለው ያልጣሉትን ሃይል(ህወሀትን) ዛሬ ላይ ከዚ ከዚህ ያልሰለጠነና የ60ና70 አመህ ታጣቂ ሰብስበህ የሚፈጥሩት ድል ፈጽሞ አይኖርም። በዚህ ሰአት ወደኋላ የምንለውም የምናቆመውም ትግል የለም። ያለጥርጥር የዚህ ፋሽሽት ሃይል መቀበሪያው ቅርብ ነው።
ሁላችሁም የትግራይ ህዝብና ደጋፊዎቻችን ድላችን ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየደረሰ ነው። የጠላትን የሀሰት ወሬ ትታችሁ የተለመደውን ሁሉ አቀፍ ትግል እንድትቀጥሉና እንድትረባረቡ የትግራይ ወታደራዊ ክማንድ ጥሪ ያቀርባል።
⇑የህወሓት መግለጫ 
Filed in: Amharic