>
5:21 pm - Saturday July 20, 7697

"እምዬ ምኒልክን "ሂትለር" ለማለት የደፈረው ኢያስፔድ ማን ነው? - ከሰማያዊ ፓርቲ እስከ ኦነግ ካምፕ...!!!" (ዘመድኩን በቀለ)

“እምዬ ምኒልክን “ሂትለር” ለማለት የደፈረው ኢያስፔድ ማን ነው? – ከሰማያዊ ፓርቲ እስከ ኦነግ ካምፕ…!!!”
ዘመድኩን በቀለ

 

“…ኢያስጴድ ተስጳዬ ፀረ ሚኒልክ… ፀረ ዐማራ… ፀረ ጦቢያ ሳይሆን በፊት… ጃዋር መሀመድ፣ ለማ መገርሳ፣ ሽመልስ አብዲሳም ሳያገኙት በፊት ከጎደኛው ከዮናታን ተስጳዬ ጋር የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ነበር። 
 
…ኦነግ ከኤርትራ በረሃ ሲገባ፣ ጃዋር ከሚኒሶታ ሲመጣ ሁለቱንም ተከትሎ ከሰማያዊ ከአንድነት ፓርቲም እልም ብሎ ወጣ። ወጡ። 
 
… የመምሬ ተስፋዬ ልጅ ዮናታን ጌታን ተቀብሎ ሲበለጽግ የጋሽ ተስጳዬ ልጅ ኢያስጴድ ደግሞ ወደ ኦነግ ካምፕ ተሸክመው የመጡት ሻንጣ ዶላር መስሎት እበላ ብሎ ገባ ተጠቅልሎ። 
 
• አሁን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በወራሪው የትግሬ ሠራዊት ላይ ትኩረቱን ባደረገ ወቅት ብልፅግና ወኦነጉ ኢያስጴድ ለምን የሌለ የከረመ የጠነባ፣ የሸተተ፣ የገማ አጀንዳ ይዞ እንዲመጣ ተደረገ? 
 
• ኢያስጴድን እንዲህ እንዲናገር መብት የሰጠው ቀጣሪው፣ ድርጎውን የሚሰፍርለት ባለሥልጣን ማነው? 
 
• ጃዋርን ባይተካላቸውም እንደጃዋር ጃዋር ጃዋር እንዲጫወት ፈትቶ የለቀቀው ባለሥልጣን ማነው? የሚለውን ቆይተን እንመለስበታለን። 
 
… የሚገርመው ነገር የትም ቦታ ቢሆን “ሰው” አለን። ኢትዮጵያ መቼም ሰው አታጣም። ስለዚህ ማርያምን እልሃለሁ ኢትዮጵያማ ታቸንፋለች‼
 
💪🏿💪🏿💪🏿 ሚኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው ‼
 
 
ኢያስጴድ ተስፋዬ ማነው? 
…ይሄ ገልቱ ውርንጭላ የሆነ በማንነት ቀውስ ውስጥ ተዘፍቆ ፀረ ኢትዮጵያ… ፀረ ምኒልክ… ፀረ ዐማራ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያለ አቅሙ ዊኒጥ ዊኒጥ የሚለው ኢያስጴድ ተስፋዬ ማነው? መጀመርታ ነገር ዱራንዱሪሲኔ እሱን እናያለን። ለምን በአሁን ሰዓት አዲስ አጀንዳ እንዲስብ ተደረገ? የኢትዮጵያ፣ የዐማራ፣ የምኒልክና የኦርቶዶክስ ጠላትም ሆነ ለሚለው መንደርደሪያ ስለሚሆነን ቅድሚያ የኢያስጴድን የቤተሰብ ማንነት በስሱ እንመልከታለን።
…ኢያስጴድ ከአክራሪ ኦርቶዶክስ ዐማራ አባቱ ከአቶ ተስፋዬ ታደሰ አበበ እና ከኦሮሞ እና ጉራጌ ቅልቅሏ ከአክራሪ ጴንጤዋ እናቱ ከወ/ሮ ተሻለች ቡልቻ የተወለደ ውህድ ማንነት ያለው የኢትዮጵያ ልጅ ነው።
… አባቱ አቶ ተስፋዬ ታደሰ ወሎ ቦረና መካነ ሰላም የዐማራ ሳይንት ሰው ሲሆኑ በልምድ በጥብቅና ሙያ የሚተዳደሩና ከዚያም ባሻገር በነፃው ፕሬስ ዘመን የሉባርና የመስታወት ጋዜጦችም ባለቤት ነበሩ። በዚህ ተግባራቸው የሚበሳጨው የመለስ ዜናዊው የትግሬ መንግሥት የዐማራ ሳይንቱን ዐማራውን አቶ ተስፋዬን ታደሰን ለሦስት ይሁን ለ4 ዓመታት ከርቸሌ ወርውሮ በእስር አሰቃይቶ ፈትቷቸዋል።
…የኢያስጴድ አባት ዐማራው አቶ ተስፋዬ ታደሰ ከመለስ ዜናዊ ወኅኒ ቤት እንደወጡ በቀጥታ የመላው ዐማራ ድርጅትን ተቀላቅለው ዐማራን ማደራጀት የጀመሩ ሲሆን በዚህ ተግባራቸው የበገነው ፀረ ዐማራው የመለስ ዜናዊ መንግሥት አቶ ተስፋዬን ኮሪያ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ጋር ወክ አድርጎ በመመለስ ላይ ሳለ ገዳይ የህወሓት አረመኔ ጨፍጫፊ ቡድን በመላክ በጩቤና በገጀራ በመኖሪያ ቤታቸው በራፍ ላይ ጨፍጭፈው ገድለዋቸዋል። ይህን በተመለከተ በወቅቱም ዓለምአቀፉ የጋዜጠጮች ተከራካሪ ቡድን የሆነው ሲፒጄ እንዲህ ብሎም ነበር የዘገበው።
https://ifex.org/journalist-tesfaye-tadesse-murdered/ ፦ እንግዲህ ልጅየው የአባቱን ገዳዮች ነው እንዲህ የሚናፍቀው። ምን አይነት ፍቅር ነው በማርያም።
… ኢያስጴድ አባቱ ያወጣለት ስሙ አንተነህ ተስፋዬ ሲሆን ኋላ ላይ ነው በቅርቡ ዐማራ አባቱ፣ ኦርቶዶክስ አባቱ ያወጣለትን ስሙን ተፀይፎ ከአንተነህ ወደ ኢያስጴድ ያስለወጠው። የኢያስጴድ እናት ወ/ሮ ተሻለች ቡልቻ አክራሪ ጴንጤ የነበሩ ሲሆን፣ አባትየው አቶ ተስፋዬ ደግሞ አክራሪ ኦርቶዶክስ የነበሩ ሰው እንደነበሩ ተገልጿል። የኢያስጴድ አባት አቶ ተስፋዬ እናቱን ያገቡት በድርጅታቸው ውስጥ በጸሐፊነት ቀጥረው እያሠሯቸው ከመላመድ ብዛት የተነሣ በዚያው ተዋደው ይሁን ተሳስተው በተፈጠረ ግኑኝነት  የያኔው አንተነህ የአሁኑ ኢያስጴድ በመፀነሱ ምክንያት ነው ይባላል። ኢያስጴድ በስህተት የተረገዘ ቢሆንም የአቶ ተስፋዬ ቤተሰብ እንዲወለድ አለመፈለጋቸውም ይወራል። እናቱ ደግሞ በስህተት ብትጸንስም ዕድሉ እንዲያመልጣቸው ስላልፈለጉ ስድቡንና ነቀፌታውን ሁሉ ችለው ወልደውታል። ይሄንንም ለልጃቸው እያስተማሩት፣ የዐማራና የኦርቶዶክስንም ጥላቻ እየጋቱት ከእናቱ ጋር ባለው ቀረቤታም የተነሣ የእናቱን ሃይማኖት ይዞ ጴንጤ ሆኖ አድጓል። ነገር ግን ለየት ያለው ጴንጤ የእነ ዐቢይ አሕመድ የብልጽግና ወንጌል ሃይማኖት ተከታይ የሆነው ግን ከለውጡ በኋላ እንደሆነ ይነገራል። ኢያስጴድ የአባቱን ዘር የጠላው በእናቱ ሰበካ እንደሆነም የሚጠረጥሩ አሉ። የእናቱን ጋብቻ ያልተቀበሉት የአባቱ ቤተሰቦች እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የፍርድ ቤት ክርክር ላይ እንደነበሩም ይነገራል።
…ኢያስጴድ ትምህርት የጀመረው ኢትዮፓረንት ትምህርት ቤት ሲሆን ከዚያ ቆይቶ አሁን የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የንስሐ አባት የሆነው ፓስተር ዮናታን ገዝቶ ቸርች ሊሠራበት የሚያፈርሰውን “እንቡጥ” የተባለው ትምህርት ቤት ተቀላቀለ። አንተነህ/ኢያስጴድ ከልጅነቱ ጀምሮ የስለላ መጻሕፍትን በማንበብና የስለላ ፊልሞችን በማየት ጊዜውን ማሳለፍ የሚወደው የነበረ ሲሆን አንተነህ ወይም ኢያስጴድ በዚህ በማንነት ቀውስና ውዝግብ ላይ እያለ ነበር ከእነ ዐቢይ አሕመድ ግሩፕ ያውም ከቁማርተኞቹ ስብስብ ጋር የተገናኘው። የእነ ጃዋርና ለማ ግሩፕ፣ የኦፌኮና የአቢቹ ግሩፕ ከላይ በሺ ምክንያቶች የተጣሉ ይምሰሉ እንጂ ዋናው ዓላማቸው አንድ ነው። ዐማራና ኦርቶዶክስን ማጥፋት። አከተመ።
…ኦሮሞነትን በእናቱ፣ ጴንጤነትም በእናቱ ያገኘው አንተነህ/ኢያስጴድ አሁን የቅርብ አለቃ ተመድቦለት፣ ደሞዝም ድርጎ ከብልፅግና እየተሰፈረለት ለዐማራው አዲስ አጀንዳ በመስጠት እንዲረብሽ ያለመከሰስና ያለመታሰር መብት ተሰጥቶት እንዲፏልልብንም ፈቃድ አግኝቶ ይምበጫበጭብናል። የኢትዮጵያ አምላክ ሴራችሁን ያፈርሰዋል። እኔማ አልፋታችሁም። ማርያምን አልፋታችሁም። የኢያስጴድ የቅርብ አለቃው ማነው? እሱንም እንዲሁ በመረጃ እንመለስበታለን።
… በነገራችሁ ላይ ከዚህ ከኢያስጴን ጦርነት በድል ከተመለስን በኋላ ከዐቢይ አሕመድ በኋላ ለጠቅላይ ሚንስትርነት ስለተዘጋጀው እና ስለታጨው አንድ የ30 ዓመት የወለጋ ለግላጋ ወጣት በሰፊው እናወጋለን። ይህ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በውሰት ወደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ከተመደበ በኋላ ዐቢይ አሕመድን ቁጭ ብድግ ስለሚያደርገው፣ ተነሥ፣ ውጣ፣ ተኛ ስለሚለው ድንቅ ወጣት፣ ሚስቱንና የሚስቱን ቤተሰቦች ዲሲ፣ የራሱን ቤተሰቦች ወደ ዳላስ ስላሻገረው ስውር ዕጩ ጠቅላይ ሚንስትር አጫውታችኋለሁ። ስለዚህ ብዙዎቻችሁ የምታውቁ አይመስለኝም። እኔ ግን ቀጣዩን ጠቅላዬን ከአሁኑ ስላየሁት ደስስ ብሎኛል። በፎቶ በቪድዮ ጭምር የደረሰኝን አንድ ቀን ትከሻዬን የሸከከኝ ቀን አፈነዳላችኋለሁ።
• 💪🏿💪🏿💪🏿 ሚኒልክ ዛሬም ንጉሥ ነው ‼
• ማርያምን ኢትዮጵያማ ታሸንፋለች  ‼
• ድል ለዐማራ ፋኖ ‼
• ድል ለዐማራ ልዩ ኃይል ‼
• ድል ለዐማራ ሚኒሻ ‼
• ድል ለዐፋር ልዩ ኃይል ‼
• ድል ለአፋር ሚኒሻ ‼
• ድል የኦነጋዊያኑን ሴራ ተቋቁመው ሃገሬን ብለው ለሚዋደቁ ለመከላከያ ሠራዊት አባላት በሙሉ ‼
• ድል ለኢትዮጵያ ‼
Filed in: Amharic