ሱሌማን አብደላ
የመካከለኛው ምስራቅ ትልቁ ጋዜጣ፣ ዘ-ጆርዳን ታየምስ አንድ ሚስጥር አውጥቷል። አሜሪካ በኬኒያ በኩል ወለጋ ያለውን የህወሓት ክንፍ ለመርዳት ኬኒያን ጠይቃ፣ ኬኒያ አልቀበልም ብላ መመለሷን አጋልጧል።
ይህ ድብቅ ሴራ ጠቅላይ ሚኒስቴሩን በጉልበት ለማሶገድ የምትወስደው እርምጃ ሲሆን፣ አሜሪካ፣ የወያኔ አንድ እግር የሆነው ሸኔ ከወያኔ ቀድሞ አዲስ አበባን ቢቆጣጠር የተሻለ ይሆናል የሚል ግምት ነበራት። ይሄንን ግምት ያሰላችው ህወሓት በ27 አመት” የስልጣን ቆይታው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በፈፀመው ግፍ ተቀባይነት የለለው በመሆኑ የማዕከላዊ መንግስቱን በወኪሉ ሸኔ ቢገለበጥ፣ ኦነግ ሸኔ በስልጣን ላይ ለኢትዮጵያ አዲስ ድርጅት ስለሆነ ምናልባት ህዝቡ ከህወሓት የተሻለ አማራጩ አድርጎ ሊያየው ይችላል የሚል ግምት ነበራቸው።
የማዕከላዊ መንግስቱን ማንሳት አካባቢውን የሽብር ቀጠና ማድረግ ነው የሚል አቋም ያላት ጎረበት ኬኒያ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ቀንድ ተወካዩ ጀፍሪ ፊልትማን ያቀረቡትን የፀረ ኢትዮጵያ ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች።
ፊልትማን በዚህ ዙሪያ ሁለት ጊዜ ኬኒያ እየተመላለሰ ቢሸመግልም ሁለቱንም ጊዜ ሽምግልናው ሳይቀናው በሄደበት እግሩ ተመልሷል።
ከፊትማን ቀጥሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አንቶኒዮ ኪሊተን (ቢል) ለፕሬዚዳንት ኡኹሩ ኬኒያታ ሀሳቡን ቢያቀርበውም፣ ፕሬዚዳንቱ አይደረግም ብለው መልሰዋቸዋል ሲል ዘጆርዳን ታየምስ ዘግቧል።
.
በተቃራኒው ፊልትማን ከህወሓትና ከሸኔ መሪዎች ጋር በዚህ ዙሪያ ተወያይቶ ህወሓት እሽ ይሁን ብላ ሸኔም እፈፅማለሁ ብሎ የተዘጋጀ ቢሆንም፣ ኬኒያ ቋምጠው እንዲቀሩ አድርጋቸዋለች።
በአፍሪካ ቀንድና በመካከለኛው ምስራቅ
ሚስጥር አፈንፍኖ በማገኘት ተወዳዳሪ የለለው የሲአይኤ እና የሞሳድ መረጃ ተቀላቢው ዘጆርዳን ታየምስ፣ አዲስ አበባ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ ተደጋጋሚ ጊዜ በሰላማዊቷ ከተማ ላይ የአሜሪካ ዜጎች ለቃችሁ ውጡ የሚል ቅስቀሳ የሚያደርገው፣ ምናልባት አሜሪካ በወለጋ በኩል፣ ወይም በሱዳን ድንበር አካባቢ ያሰበችው ነገር ይኖሮ ይሆን ሲል ጥያቄና መላምቱን አንድ ላይ አስፍሮታል።
በሌላ በኩል የሱዳን ጦር ኢትዮጵያ ውስጥ የቀረውን መሬቴን ለማስመለስ እየተዘጋጀሁ ነው ብሏል። ጦሩ ድንገት ኢትዮጵያ ጥቃት ፈፀመችብኝ፣ ወታደሮቸ ተገደሉ፣ መሬቴን ወረረችብኝ፣ እያለ ከፍተኛ የሆነ የሚዲያ ፕሮፓጋንዳ በመስራት እየሰራ ነው።
የሱዳን ጦር ማንም ሳይነካው ድንገት እንደተልባ መጮህ የጀመረው ያሰበው ወይም የተሰጠው ሜሸን ይኖር ይሆን ወይ ብለን እንድንጠይቅ ያደርገናል።
እንደሚታወቀው ህወሓት ሱዳን ውስጥ በቀላሉ 30ሺ ቁጥር ያለ ወታደር፣ በግብፅና በሱዳን የጦር ጠቢቦች ሲሰለጥን ከርሞ ለተልዕኮ ተዘጋጅቶ ተቀምጧል። ይህንን ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግስት በስለላ ተቋሙ የደረሰበት ያደባባይ ሚስጠሩ ነው።
ይህ ጦር ተደጋጋሚ ጊዜ በሱዳን ወታደሮች ሽፋን ተሰቶት ወደኢትዮጵያ ለመግባት ሙከራ ቢያደርግም በወገን ሀይል በሚደረስበት ብትር እየተደመሰሰ ህልማቸው እንዳይሳካ ሲሆን ከርሟል። ባለፈው ቅዳሜ ለሊት 6ሺ የሰው ሀይል ያለው የህወሓት ጦር ከሱዳን ወደኢትዮጵያ ለመግባት ሙከራ አድርጎ፣ በወገን ሀይል ተቀጥቅጦ ተመልሷል። ሱዳን ወታደሮቸ ተደበደቡ የምትለው፣ የኢትዮጵያ መንግስት በህወሓት አሸባሪዎች ላይ የወሰደውን እርምጃ ነው።
.
ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ጦር ወደ ግዛቴ ገብቶ ተኩስ ከፈተብኝ የሚልፕሮፓጋንዳ የሰራችው ሱዳን፣ ትናንት የወታደራዊ ልዩ መልዕክተኛው ሀሽም ሀቢኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር ወደ ሱዳን ድንበር እያስጠጋች ነው የሚል መግለጫ ሰቷል። በመግለጫው ላይ ሱዳን ኢትዮጵያ ውስጥ የቀረ መሬቷን የመመለስ ስራዋን አጠናክራ ትቀጥላለች ብሏል። ይህ የሱዳን እንቅስቃሴ አሁን ላይ ሆን ተብሎ የተደረገው ያለ ምክኒያት አይደለም። አንድም በሞት አፋፍ ላይ ቆሞ የድል ኮኮብ የሚቆጥረውን ህወሓት ለማዳን ነው። ሁለትም አሜሪካ ለኬንያ ያቀረበችውን ጥያቄ ለሱዳን ጀነራሎች አቅርባ፣ ሱዳን ሰልጥኖ ለተልዕኮ የተዘጋጀውን የህወሓት ሀይል ወደኢትዮጵያ አስገብተው ህወሓትን ከሽንፈት ለማዳን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው። ኢትዮጵያ እነዚህ ጉዳዮችበደንብ አጥንታ፣ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄዎች አድርጋ መራመድ አለባት።