>

ባዘንባቸው ቀናት ፈንታ በደስታ ዘይት ፊታችን እየበራ ነው! ዛሬም ተመስገን! (ደጀኔ አሰፋ)

ባዘንባቸው ቀናት ፈንታ በደስታ ዘይት ፊታችን እየበራ ነው!!!!! ዛሬም ተመስገን!!!!!
ደጀኔ አሰፋ

እነሆ በሁለት ቀናት በተደረገው ኦፕሬሽን
በሸዋ ግንባር የቀወት ወረዳ፣ ለምለም አምባ፣ ጀውሐ፣ ሰንበቴ፣ አጣየ እና ካራ ቆሬ ከተሞችና አካባቢዎች ከወራሪው ኃይል ሲፀዱ…. በጋሸና ግንባር ኮን እና ዳውንት በወረኢሉ ግንባር ልጓማ ከተማ ሙሉ በሙሉ ነጻ ወጥተዋል!!!!! ሁላችንንም እንኳን ደስ አለን!!!! ድሉ ይቀጥላል!!!!! ፈፃሜውም ቀርቧል!!!!!
በውስጥም በውጭም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን እየገለፁ ነው!!!! ወዳጆቻችን ደስ ብሏቸዋል!!!! ኢትዮጵያን የሚወዱ እና ፍትህን የሚሹ ሁሉ እየተደሰቱ ነው!!!! የደስታቸው ምንጭ ጁንታው እየተደመሰሰ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የላኪዎቹ እና የአጨብጫቢዎቹ አንገት ስለተሰበረም ጭምር ነው!!!!
በምዕራባዊያኑ እርዳታ እና በታሪካዊ ጠላታችን ግብፅ እንዲሁም በሱዳን ወታደራዊ መንግስት ታግዞ አፈር ልሶ የተነሳው አሸባሪው የትግሬ ወራሪ ሃይል አማራ እና አፋር ክልሎችን በመውረር አያሌ ጥፋት አጠፋ:: ንፁሃንን ገደለ:: በጅምላ ረሸነ:: መሰረተ ልማቶችን አወደመ:: ዘረፈ:: የገበሬውን ሰብል አጠፋ:: የሃይማኖት ተቋማትን አቃጠለ:: ለንግግር የሚከብዱ እና ከኢትዮጵያዊያን ባህል ውጭ የሆኑ ፀያፍት ነገሮችን ፈፀመ:: ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል ድረስ እወርዳለሁ በማለት አቋሙን በማያሻማ ቋንቋ ግልፅም አደረገ:: እነሆም ከትቢያ አንስተው ከአቅሙ በላይ አንጠራርተው ላኪዎቹ እንዳሻቸው ይጋሉበት ያዙ:: ኢትዮጵያን ያፈርስልናል ህዝቡንም ይበትንልናል ህዳሴ ግድቡንም ያስቆምልናል በመጨረሻም ኢትዮጵያ ውስጥ ተላላኪ መንግስት እንመሰርታለን … ወዘተ ብለው ጮቤ ረገጡ::
አሁን ግን ነገሩ ተገለበጠ!!!!!!
ያዘነው ተደስቶ
በእብሪት ሲቦርቅ የከረመው ፊት መንጨቱን እና ደረት መደቃቱን ጀምሯል!!!! መንከባለሉም አይቀሬ ነው!!!!
በዚህ ሰዓት የጁንታው ደጋፊዎች እና አክቲቪስቶች ደንግጠው ጭው ብለዋል!!!! ሲደግፏቸው በነበሩ ሃገራትም ተስፋ የቆረጡ ይመስላል!!!! የጁንታው የዲያስፖራ አክቲቪስቶች (ስታሊን : አሉላ : ዳደ : ሃይለሚካኤል… ) የአዕምሮ መቃወስ ገጥሟቸዋል!!!! አንድ ንግግር ጀምረው መጨረስ እንኳን አይቻሉም!!!! እዚህም እዚያም ይረግጣሉ!!!! ዝብርቅርቅ ብሎባቸዋል!!!! ያ ፊታቸው ጠቁሮ… የንቀት ሳቃቸው ጠፍቶ … መወጣጠራቸው ረግቦ…. እብሪታቸው ተሰባብሮ… ትዕቢታቸው ተንፍሶ … እነሆ #ትንንሽየ_ፊኛ ሆነዋል!!!! ትን…ፍስስስ ብለዋል!!!! አስተውሎ ላያቸው ሰው በእሳት የተኮማተረ ጀሪካን ይመስላሉ!!!!
እፍረት ውርደት እና ሃዘን የቀን እንጀራቸው ሆኗል!!!! በልብስ ሊደብቁት የማይችሉት እንባና ሳግ ከውስጣቸው ይደመጣል!!!! ግራ ግብት ብሏቸዋል!!! ሽንፈታቸውን ማስተባበል እስከማይችሉ ድረስ የውርደት ፅዋን ተጎንጭተዋል!!!! እራሳቸው ዞሮባቸው ሳለ በህወሃት ዘንድ የአቋም ለውጥ እንደሌለ ኦነግ ሸኔን ለማሳመን ይዳክራሉ!!!! ስልታዊ ማፈግፈግ ነው በሚል ደም ስራቸው እየተገታተረ ለማስረዳት ይቃትታሉ!!!! ሸኔን እንደከዱት እንዳይታወቅባቸው ይርበተበታሉ!!!! ስራቸው ሁሉ መንተባተብ ሆኗል!!!! መቼም የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው እንጅ ሁለት ቀናት ያህል ጠፍተው ነበር!!!! እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝ ያመጣል እንዲሉ እንደዛው ሆነዋል!!!!!
ህወሃት እና የሰራዊት ኮማንድ ፖስት የሚባሉትም በየፊና መግለጫ ይሰጣሉ!!!! እርስበርስ እየተቆራቆሱ ለመሆኑ ብዙ መረጃዎች አሉ!!!! አይዟችሁ ተረጋጉ ለስትራቴጅ ነው ቦታዎችን የለቀቅነው እያሉ እራሳቸው ሳይረጋጉ የትግሬ ዲያስፖራዎችን ለማረጋጋት ይጋጋጣሉ!!! ጋላቢዎቻቸውን ለማረጋጋት ይንተባተባሉ!!!! በጣም ያስቃሉ!!!! ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ አይነት ተጋላቢው ጋላቢውን ላለማስቅየም ይሟሟታል!!!! የትግሬ ዲያስፖራም በጭንቀት እና በሃዘን በአንድ ጊዜ ክሰል መስለዋል!!!! አውጥተው ህወሃትን እንዳይሰድቡ ወይም ምን እየተካሄደ እንዳለ እንኳን እንዳይጠይቁ “ጠላት” በሚሉት ህዝብ ፊት ህወሃትን እንደማሳጣት ቆጥረው ለብቻቸው ይብሰለሰላሉ!!!!! ጁንታው ለማያሸንፈው እና በእብሪት በገባበት ጦርነት ያን ሁሉ የትግሬ ታዳጊ ህፃን አስፈጅቶ አሁንም ለመጨረሻ ጊዜ በውርደት እየተደመሰሰ መሆኑን ልቦናቸው ቢያውቅም መቀበል ግን አልፈለጉም:: ስለዚህ የትግሬ ዲያስፖራ ብቻውን እዬዬውን እያስነካው ነው!!!!
ለማንኛውም ጉዳዩ እንዳለቀ እርግጥ ሆኗል!!!!
ዋናው ጦርነት በድል ተጠናቋል!!!!
አሁን የቀረው ጥቂት ውጊያ ለዚያውም የተረፈው ውራሪ ሃይል ፈርጥጦ ትግራይ ለመግባት በሚያደርገው ሩጫ ሊኖሩ የሚችሉ የፈርጣጭ እና የአስፈርጣጭ ተኩስ ካልሆነ በቀር የጁንታው ሃይል ተበትኗል ፈርሷል!!!! መደበኛ ውጊያ የሚያካሂድበት ቁመናው ውልቅልቁ ወጥቷል!!!! መሪዎቹ አልቀዋል!!!! ትርፍራፊውም ሃይል ፍፃሜውን ሊያገኝ የእውር ድንብር ሩጫውን ተያይዞታል!!!! ከአማራ ክልል በህይወት የሚወጣ ጁንታ ካለ እርሱ እንደ ታላቅ ፃድቅ ሰው ሻማ ይበራለታል:: ዳሩ ከአማራ ክልል በተዓምር ቢያመልጥ እንኳን እዚያም ቢሄድ … ቆላ ተንቤን ቀርቶ የእናቱ ቀሚስ ውስጥ ቢደበቅ ያች ከጥምር ጦሩ የታዘዘችበት የሞት ፅዋ ከእርሱ አታልፍም!!!! ሁሉም የእጁን ያገኝ እና የዘራውንም ያጭድ ዘንድ የተፈጥሮ ህግ ያስገድዳል!!!!! ኢትዮጵያንስ ወግቶ ማን በህይወት ይኖራል?!? አዲዬስ!!!
ድልን ለሰጠን የኢትዮጵያ አምላክ ምስጋና ይገባዋል!!!!!
ክብር ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን!!!!!
ክብር ለጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል ሚሊሻ እና ፋኖ!!!!!
ክብር ለበርሀ አናብስቱ የአፋር ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ!!!!
ኢትዮጵያ በወራሪዎች መቃብር ላይ ታብባለች!!!!
Filed in: Amharic