ሰላም ሙሉጌታ
በኢትዮጵያ ጉዳይ የተዛባ አቋም እያራመዱ ባሉና ጫናውን ለማበርታት ባለሙ አካላት ተዘጋጅቶ የቀረበው ‘በትግራይ የዘር ማጥፋት ተፈፅሟል’ የሚል በሀሰት የተቀናበረ ሰነድ በአሜሪካ ኮንግረስ ውድቅ ተደረገ።
ሰነዱ የአሜሪካ ኒውጀርሲ ግዛት ሹመኛው ማሊወንስኪ በኩል ተዘጋጅቶ ለኮንግረሱ ከ2 ቀን በፊት ቀርቦ ክርክር ሲደረግበት እንደነበር ዋልታ በኢትዮ-አሜሪካዊያን የልማት ጉባኤ የቲውተር ገጽ ላይ ከተያያዘ ሰነድ ተመልክቷል።

ሰነዱ ከአሜሪካ ብሔራዊ መከላከያ ፍቃድ ሕግ /National Defense Authorization Act-NDAA/ እንዲወገድ ነው የተደረገው።
ይህ ውንጀላ በመንግሥት ላይ እንዲቀርብ የተዘጋጀው ሰነድ ማስረጃ አድርጎ ያቀረበው ትውልደ ሱዳናዊቷ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ኒማ ኤልባገር የሽብር ቡድኑ ሕወሓት አባል የሆነን አንድ ግለሰብ አናግራ ከወራት በፊት የሰራችው ቅጥፈት የታጨቀበት ‘የጅምላ ግድያ የተፈፀመበት መቃብር ተገኘ’ የሚለው የፈጠራ ዘገባ መሆኑንም ዋልታ ከሰነዱ አስተውሏል።
የኢትዮ-አሜሪካዊያን የልማት ጉባኤ ዲያስፖራው ላደረገው ብርቱ ትግል አመስግኖ በቀጣይም በሴናተር ክሪስ ኩንስ የተዘጋጀውን የማዕቀብ ምክረሐሳብ በተመሳሳይ ውድቅ ለማስደረግ ጫና ማሳደሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።
ፅንፍ የያዙ የውጭ ኃይሎች ‘የትግራይ ዘር ጭፍጨፋ’ የሚል ድርሰትን በተደጋጋሚ ይዘምሩት እንጂ የተባበሩት መንግሥታት የሰብኣዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብቶች ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት ምርመራ መንግሥት የዘር ማጥፋት ወንጀል አለመፈፀሙን ግልፅ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ይልቁንም አሸባሪው ሕወሓት ጦርነቱን ከከፈተበት ጥቅምት 24/2013 ጀምሮ በማይካድራና ሌሎችም በርካታ የአማራና አፋር አካባቢዎች የዘር ጭፍጨፋና ዓይነተ ብዙ የጦር ወንጀሎችን እየፈፀመ ይገኛል።