>
5:29 pm - Wednesday October 10, 1483

 በማንነቱ የማይደራደር ነፍጠኛው አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገር...!!!" (አዲሱ ጎንቻ)

 በማንነቱ የማይደራደር ነፍጠኛው አርበኛ ዘመነ ካሴ ነገር…!!!”
አዲሱ ጎንቻ

ኢትዮጵያ ሀገሩን አብዝቶ ይወዳል፤ ዋጋም ይከፍላል…!
በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ሰለሆነ የመጀመሪያና 2ኛ  ዲግሪውን እጅግ በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቅ ባለ ምጡቅ አዕምሮ ትንታግ ሙህር ነው::
በአማራ ህዝብ ላይ የሚፈፀመውን ግፍና በደል ለማስቆምና ሀገሩንም ለማገልገል በውጭ ሆኖ ከመቃወም ይልቅ ውሰጥ ገብቶ መታገል ይሻላል በሚል እሳቤ  በክልል ደረጃ ትልቅ  ሰልጣን ጨብጦ  አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ጥረት አድርጓል::
ለእራሱ የተደላደለ ህይወት ቢኖረውም በውሰጥ ትግል ጨቋኙን ስርዓት መገርሰሰ  እረጅም ጊዜ የሚፈጅ ሰለመሰለው የኢትዮጵያ ህዝብ ከጭቆና ቀንበር የሚላቀቅበትን የድል ቀን ለማሳጠር  በመጓጓት ሰልጣኑም:ገንዘቡም: ቤቱም ይቅርብኝ ብሎ  ነፍጥ አንሰቶ በርሃ በመግባት ህወሓት/ኢህአዴግን በትጥቅ የታገለ አልሞ ተኳሽ አርበኛ ነው::
 በህወሓት የበላይነት የሚዘወረው ጨቋኙ ኢህአዴግ በኢትዮጵያዊያን የተባበረ ክንድ ፍርክሰክሱ ወጥቶ መጠነኛ የስርዓት ለውጥ በተደረገ ማግስት ነፍጡን አሰቀምጦ የግል ኑሮውን መምራት የጀመረ ሰላም ወዳድ ሰው ነው::
በጠ/ሚ አብይ አህመድ  አሰተዳደር ወቅት አማራው በቤኒሻንጉል:በኦሮሚያ:በሲዳማ:በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች መጨፍጨፍ ሲጀም ግን እንደ ሌሎች አድሃሪያን ዝምታን አልመረጠም:ይልቁንሰ በአደባባይ ከመቃወም አልፎ  ህዝቡን ለመታደግ ሰሜን ሸዋና መተከል በመዝመት የወገን አለኝታነቱን በተግባር ያረጋገጠ ጀግና ነው::
የአማራ ዘላለማዊ ጀግና  የሆነውን ብ/ጀ አሳምነው ፅጌን እና እነ ዶ/ር አምባቸው መኮነን ባጣንን ማግሰት ግን ከጠላት ጋር  የተለጠፉ ጥቂት የውሰጥ ባንዳዎች ዘሜን ለመግደል ቃታ ሰበው:ለማሰርም ሰንሰለት ይዘው ቢያሰሱትም ግንባሩን ለጥይት:እጁንም ለካቴና ያላሰቀመሰ አንበሳ ነው::
 ለቃሉ ታማኝ:ለወዳጆቹ ምቹ የሆነው ለጠላቶቹ ግን እንደ እሳት የሚፋጀው አርበኛ ዘመነ ካሴ አሳዳጆቹን ቤቱ ሆኖ እየተንቀጠቀጠ የሚጠብቅ ሳይሆን ምሸጉን ጫካ አድርጎ  ሊገድሉት የሄዱትን ሲያሰበረግግ የከረመ ጀግና ነው::
የአርበኛ ዘመነ ካሴን እጅ መጨበጥ ያቃተው ባንዳው የብአዴን ክንፍ በሌለበት የወንጀል ክሰ ቢመሰርትም ለህሌናቸው ያደሩ ዳኞች ዘሜን በነፃ ማሰናበታቸውን ተከትሎ አሳዶጆቹን ይቅር ብሎ እየተገማሸረ ከተማ የዘለቀ ኩሩ አማራ ነው:
በመጨረሻም የትግራይ ወራሪ ሀይል ህዝብን ለማጥፋትና ሀገራችንን ለማፍረሰ የጀመረውን ሁለተኛ ዙር ወረራ ቅዠት ለማድረግ የጎጃም አማራን ጀግኖች እና የሌላ አካባቢ ሀቀኛ የአማራ ፋኖዎችን አደራጅቶ  እየመራ ከወገን ጦር ጎን በመሰለፍ ጠላትን እንደ ቅጠል እያረገፈ: የተወረሩ አካባቢዎችን ነፃ እያወጣ የሚገኝ የቁርጥ ቀን ጀግና ነው::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን የአማራ ህዝብ አንድነት የሚኮሰኩሳቸው:በመንደር የተደራጁ የብአዴን ጎጠኛ ካድሬዎችና ምንጣፍ ጎታች ደጋፊዎቻቸው:የአማራ ህዝብ ሀቀኛ ጀግና እንዳያወጣ ከሚያሴሩ ዘላለማዊ ጠላቶች እና የኢትዮጵያ አለመፈረካከስ እንቅልፍ ከሚነሳቸው ቅንቅናም  ቡድኖች ጎን ተሰልፈው ሰሙን ከማጠልሸት አልፈው ማጎሪያ ቤት ለማሰገባት እየተጋጋጡ ይገኛሉ::
ለማንኛውም አርበኛ ዘመነ ካሴ በዚህ ወቅት ሞት የየደቂቃዎች ትዕይንት:መትረፍ ደግሞ ተዐምር በሚሆንበት የጦር አውድማ ተሰልፎ ከጠላት ጋር እየተዋደቀ ነው:ህዝቤ ከሚያልቅና  ከሀገሬ ከምትፈርስ ይልቅ መተኪያ የሌላት ህይወቴ ትጥፋ ብሎ ከሞት ጋር ፊትለፊት እየተጋፈጠ በሚገኝበት ቅፅበት ጥቂት የትውልድ አተላዎች ግን በጠላት እጅ ከምትሞት እኛ ወንድሞችህ ቀድመን እንገደልህ ወይም ደግሞ ጠላትን ከመማረክህ በፊት ባንተ እጅ ላይ ካቴና ሳናሰገባ ከምንቀር ሀገር ብትፈርሰ ይሻላል የሚል  ሰንኩል የሴራ-ወጥመድ ዘርግተው አሁንም ድረስ እያሳደዱት ሰለሚገኙ አማራ ነኝ የምትሉና ኢትዮጵያን የምትወዱ ሰዎች ሁሉ ከጀግናው ዘመነ ካሴ ጎን የምትቆሙበት ወቅት አሁን ነው::
Filed in: Amharic