>

ህወሓት የሰጠውን መግለጫ፣ በረቀቀ የአረብኛ አነጋገር ዘይቤ ተተርጉሞ  «.በ''12ቱም.» የግብፅ መንግስት ሚዲያዎች ተነቧል...!!! (ሱሌማን አብደላ)

ህወሓት የሰጠውን መግለጫ፣ በረቀቀ የአረብኛ አነጋገር ዘይቤ ተተርጉሞ  «.በ”12ቱም.» የግብፅ መንግስት ሚዲያዎች ተነቧል…!!!
   
ሱሌማን አብደላ

የህወሓት መግለጫ ከካይሮ ቤተመንግሥት ለግብፅና ለአረቡ አለም ህዝብ የተሰጠ መግለጫ እስኪመስል ድረስ እየተቀባበሉ አንብበታል።
መግለጫው ከአማራና ከአፋር ክልል በጦርነተ ተሸንፈን ሳይሆን የጦርነት እስትራቴጂ ለመቀር ነው ለቀን እየወጣን ያለነው የሚለው ቃል እየተደጋገ ይነበባል።
አያይዞም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን መሳሪያ ሁሉንም ቀምተናል፣ የቀረውን ደምስናል የሚለውን ቃል እየመዘዙ መዝሙር እስኪመስል እያጠበቁና እያላሉ አንብበውታል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ሁሉንም የደመሰሰና መሳሪያ የቀማ ቡድን ለምን ከሞላሌ እስሰ ቆቦ ድረስ መውጫ አጥቶ በየቤተክርስቲያኑ አድኑን የቀን ሰራተኛ ነን እያሉ በአስርሽዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎቹ መውጫ አጥተው በየቀኑ እንደሚሞቱ የሰሙት አይመስልም።
የግብፅ ሚዲያዎች ይሄንን መግለጫ ያነበቡት፣ በየቀኑ ለህዝባቸው
አብይ ወደቀ፣ መከላከያ ተደመሰሰ እያሉ በቅጥረኛው ህወሓት ተማምነው የወደፊቱን ተስፋ ሲጠብቁ ተዋጊ ወኪላቸው ሚዲያ ላይ እንደሚናገሩለት ሳይሆን መሬት ላይ በኢትዮጵያውያን ክንድ ብርቱ ተጋድሎ እገባበት ጉድጎድ ሳይወጣ ተቀብሮ መቀሩትን ለማስተባበል ህዝባቸውን በውሸት እያፅናኑ ነው። ያው ህዝባቸው አማርኛ ትግረኛ ወይም ኦሮሚፋና አፋርኛ ስለማይችል በቋንቋቸው ተደብቀው እያፅናኑት ነው።
የፀጉራቸው ጭራ እስኪነቀል ሚስጥርና ስራቸውን ነውራቸውን የሚያጋልጣቸው
 አል አለሚ ጋዜጣና GUBA times ግን ህወሓት አብቅቶለታል የምን በውሸት መፅናናት ነው፣ የምን ማስመሰል ነው
እያሉ በግብፅ ሚዲያዎች ተሳልቀውባቸዋል። ኢትዮጵያዊዩ ጋዜጠኛ
መሃመድ አል አሩሲ ሳይቀር በስራቸው ተርገሞ ሲሳለቅባቸው አይተናል። ጁባ ታይምስ ግን ይቺን ሀቅ ተናግሯል ! ኢትዮጵያዊያን አፍሪካውያንን በራሳቸው ስነልቦና ለመቅረፅ በኢኮኖሚ በፖለቲካ ን በወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ቀመር ግብፅን መብለጥ አለባቸው ብሏል።
Filed in: Amharic