>

"  አፍሪካ የጥቁር አልማዞች አህጉር " (ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ)

”  አፍሪካ የጥቁር አልማዞች አህጉር “
         ከአለባቸው ደሳለኝ አበሻ

ድልድዩን ከመስበርህ በፊት ዋና እንደምትችል እርግጠኛ ሁን'” ይላሉ ሊቃውንቶች  
      
የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል ወደ ሰማይ እንዲስፋፋ ምክንያት የሆነው “ተቃዋሚዎቻችን” ሩሲያ እና ቻይና “ለአሜሪካ ሳተላይቶች ስጋት የሆኑ አዳዲስ የጦር መሣሪያዎችን እራሱ ወደ ጠፈር ለማምጣት እየሰሩ” መሆናቸው ነው ፡፡ ነገር ግን በዋናው የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ምናባዊ መጥፋት ቢኖርም ፣ ሩሲያ እና ቻይና በተባበሩት መንግስታት አዳራሾች ውስጥ ዓለም እንዲህ ያሉትን መሳሪያዎች በ “ስትራቴጂካዊ መረጋጋት” ውስጥ  ያሉ ቦታዎችን ለማስቆም ወይንም ትጥቅ ለማስፈታት ለዓመታት ሲከራከሩ ቆይተው ድምፅን በድምፅ ከመሻር ያለፈ ጉንጭ አልባ ንትርክ ፈቀቅ ማለት አልቻሉም: :
ይሁን እንጂ የጎሪጥ እርስ በእርስ እየተሳለሉ  አይናቸውን በጥቁር አልማዞች አህጉር ጥለው ሲፈልጉ  በጉልበት ሲያቅታቸው  በእርዳታና በድፕሎማሲ ጥበብ  ለሁለተኛ ዙር ቅኝ፣ግዛት አፍሪካን ለመውረር  እየተዘጋጁ ለመሆናቸው ምልክቶች እያየን ነው  ::
 የጥቁር አልማዞች አህጉር. አንትሮፖሎጂስቶች የሥልጣኔ ዋሻ ብለው የሚጠሯት አፍሪካ  ከስድስቱ ዓለማት አንዷ ናት ።
አፍሪካ  የመላው የሰው ዘር ዝርያ እናትና አባት ተብሎ የሚጠራው በዋነኝነት የመጀመሪያው አፅም (ሉሲ) በተገኘበት መነሻ ምክንያት
ከዓለም ሁለተኛ ትልቅ አህጉር ሲሆን  54 ሀገሮች ይዛ አጠቃላይ  1ነጥብ 3 ቢሊየን ህዝብ ብዛት  በዚች አህጉር ሲኖርባት የቆዳ  ስፋቷ 29.3 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ ነው: :
 ነገርግን በአቅራቢያ ያሉትን ደሴቶች ከግምት ውስጥ የምናስገባ ከሆነ ደግሞ የአህጉሪቱ ስፋት 30.3 ሚሊዮን ካሬ ኪ.ሜ ያድጋል ፡፡
 በጠቅላላ. አፍሪካ የዓለምም አራተኛ ክፍል ነው ተብሎ የሚሰጠውን ግምት መነሻ በማድረግ  ሰፊ አህጉር ነው ለማለት ያስችለናል: :
የአፍሪካ አህገራት ሀብቶች ከፍተኛ መጠን ያለው የወርቅ እና የድንጋይ ከሰል ያለበት  ፡፡  ለማዕድን ኢንዱስትሪ ተፈላጊ ስለሆነ አህጉሩ
በቅኝ ግዛት ተስፋፊዎች  የተዘረፈ ቢሆንም ለድጋሚ ስውር ቅኝ አገዛዝ   ኢላማ ውስጥ ከገባ አመታት ተቆጥረዋል: :
አፍሪካ  በአህጉሪቱ የዓለም ወርቅ ግማሽ ያህሉ ማዕድናት  ለባለሀብቱ ስትሆን  የዝሆን ጥርስ ፣ የከበሩ ድንጋዮች እና ብረቶች የኮኮዋ ባቄላ መጠን 60% ላኪ ባለቤት በመሆኗ  ከጠቅላላው የዓለም መጠን 27% ፣ ቡና – 22% እና የወይራ ፍሬዎች 16% የሚሆነው ኦቾሎኒ. ለአለም ሕዝብ ታከፋፍላለች  ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም. የዘይት ፣ ታሊየም ፣ ኒዮቢየም ፣ አልማዝ ፣ ወርቅ ፣ ማንጋኒዝ ፣ ብረት ፣ ታንዛን ፣ ቢዩዝ ፣ ዩራኒየም ፣ ታንግስተን እና የድንጋይ ከሰል ሐብቶቿ የባእዳን ኃይሎች. ትኩረት በመሳባቸው አሁንም በእጅ አዙር ኮሎኒ ሊያንበረክኳት የቤት ስራቸውን እየሰሩ ነው . ።
…..የወደፊቷን የአፍሪካን ራዕይ ከነጻነት አኳያ ብቻ ሳይሆን በአንድነታችንም አኳያ የምናየየው ነው :: አፍሪካውያን የተለያየ ባህል ባለሃብቶች ብቻ ሳይሆኑ  ልዩ ተሰጥኦና ልምዶችም.እንዳሏቸው ታሪክ አረጋግጦላቸዋል :: ያም ሆኖ ሰዎች በበርካታ የሚያለያያቸው ሁኔታ ቢኖረንም በመግባባትና በመተሳሰብ አንድነት ማምጣት  እንደሚችሉም  እንገነዘባለን፡፡…
አፍሪካውያን ለጣምራ ግባቸው  የተባበረ ሀይላቸውን   በማዋል ለዕውነተኛው የአፍሪካ ወንድማማችነት አንድነታቸው በህብረት መቆም ግድ ነው፡፡
ከታሪክ ብንነሳ እንኳን  አውሮፖውያን የራሳቸውን ሐሳብ  ከመሸጣቸው .በፊት..አፍሪካውያን የራሳችን የሆነ  ሐገር በቀል ስልጣኔና ስርአተ መንግስት ባለቤቶች እንደነበርን መቀበል እስከ አሁን. ድረስ ከባድ ሆኖባቸዋል : :
ኡጋንዳዊው አክቲቪስት  “ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ጦርነት እየተዋጉ ነው” ሲል በፌስ ቡኩ ላይ ያሰፈረውን እውነታም ፅሁፌን ያጠናከረው ይመስለኛል ::
“ሁኔታው አሁን ላይገባንና ላናደንቀው እንችላለን፤ ነገር ግን ኢትዮጵያውያን የአፍሪካን ጦርነት እየተዋጉላት ነው።
አሜሪካ ወደ አፍሪካ የመግቢያው በር በኢትዮጵያ በኩል እንደሆነ ታውቃለች። ኢትዮጵያን ዝም ማሰኘት ከቻሉ ሌላውን ከዋሽንግተን በሚሰነዘር አንድ ቃል ያንበረክኩታል። ስለዚህ እኛ ማድረግ የምንችለው ቢያንስ ኢትዮጵያን መደገፍ  ነው::
 ​​ኢትዮጵያ ቀን አላት!
የተሰወረው የሚገለጥበት ፣የተዳፈነው የሚወጣበት ፣ ጥበቧ፣ ሃብቷ፣ እወቀቷ ፣ታሪካዊ አሴቷ፣ ተዝቆ የማይያልቁት ማዕድኖቿ የሚወጡበት፣ የተሰወሩ ከተሞች ተቆፈረው ለአለም ይፋ የሚሆኑበት ፣
በአለም አብሪ ኮከብ ሁና የምትታይ ፣ ህዝቡ  ለድኩማን ታዛ መጠጊያ ፣የአለም ስደተኞች ማረፊያ፣ ለተቸገሩ ለተጨነቁ መጠለያ ፣ የምትሆንበት ቀን ከተራራው ጀርባ ከ አውሎ ነፋሱ በኋላ ይታየኛል።
ኢትዮጵያችን እደተሰውረ የሚቀር የማይገለጥ እውነት አይኖራትም የተሰጣት ጸጋ የተነገረላት የተስፍ ቃል በጊዜ የሚገለጥ ህያው ነው።
በማለት ሀሳቡን ሲቋጭ. የጥቁሩ አልማዝ መሪዎች በበኩላቸው
  አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቢያንስ ሁለት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራትና በምክር ቤቱ ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት  ይገባታል  አፍሪካ በደንብ እንድትወከል እና እንድትደመጥ እንፈልጋለን
ሲሉ እየተሟገቱላት ነው ::
የአፍሪካ  መሪዎች ጠንካራ ጥያቄ በማንሳት በምክር ቤቱ ኢ-ፍትሃዊ አሰራር ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና ለማስቆም ኢትዮጵያ የጀመረችውን ዓለም አቀፍ የ’በቃ’ ‘#NoMore’ እንቅስቃሴ መቀላቀላቸው አይቀሬ መሆኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል  ::  ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም ይህን አህጉራዊ የፍትሃዊነት እንቅስቃሴ በግልጽ መቀላቀላቸውን ዛሬ በትዊተር ገጻቸው
ሲገልፁ የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል እና የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ትናንት በሴኔጋል ዳካር ከተማ የጋራ ውይይት ካደረጉ በኋላ  በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ለአፍሪካ ተገቢውን  ቦታ መስጠት የምክር ቤቱ ግዴታና ሀላፊነት ጭምር መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል: :
” ድልድዩን ከመስበርህ በፊት ዋና እንደምትችል እርግጠኛ ሁን'”
ማለት ይህው ነው: : . ’በቃ’ ‘#NoMore’   አፍሪካ እንቅስቃሴ በቅርቡ መጀመሩ እንደማይቀር አብሪ ጥይቱ ተተኩሷል ::
እኔም ለዛሬው በዚሁ አበቃሁ: : በሌላ ዝግጅት እስክንገናኝ ቸር ይግጠመን: :
Filed in: Amharic