>

"የአገዛዙ ነቃፊ ነኝ፤ ሆኖም ግን  ፋሽስት ወያኔ  ኢትዮጵያውያንንን ማሸነፍ አይችልም...!!!" (አቻምየለህ ታምሩ - ለቢቢሲ)

“የአገዛዙ ነቃፊ ነኝ፤ ሆኖም ግን  ፋሽስት ወያኔ  ኢትዮጵያውያንንን ማሸነፍ አይችልም…!!!”
አቻምየለህ ታምሩ ለቢቢሲ

ከሁለት ሳምንት በፊት ፋሽስት ወያኔ አዲስ አበባን ከብቤያለሁ በሚልበት ወቅት BBC News Africa እ.ኤ.አ. ኅዳር 26 ቀን 2021 ዓ.ም. ወደ ሰላሳ ደቂቃ የፈጀ ቃለ መጠይቅ አድርጎልኝ ነበር። የቢቢሲው ጋዜጠኛው ያለ ወትሮው እኔን ቃለ መጠይቅ ሊያደርግ ቀጠሮ ያያዘው ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር ዘምቻለሁ ባለ በበነጋታው ነበር። እኔን ቃለ መጠይቅ እንዲያደርግ የተላከውም የአገዛዙ ተቃዋሚ እንደሆንሁ ነግረውት ዐቢይ አሕመድን ቢዘምትም ይሸነፋል፤ ሕወሓትም አዲስ አበባን ይቆጣጠራል እንድልለት ነበር። ጋዜጠኛው በቃለ መጠይቁ  የጠበቀውን አላገኘው። ክርክራችን ዱላ ቀረሽ ነበር። እሱ ይጠይቀኝ የነበረው “ሕወሓት አዲስ አበባን ከብቤያለሁ እያለ ነው”፤ “ዐቢይ መዝመት ምን ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?” ወዘተ የሚል ነበር። እኔ የሰጠሁት መልስ “የአገዛዙ ነቃፊ ነኝ፤ ሆኖም ግን  ፋሽስት ወያኔ ይኼን ያዝሁ፣ ያንን ተቆጣጠርሁ በማለት ያሻውን ያህል ቢደነፋም ኢትዮጵያውያንንን ማሸነፍ እንደማይችልና በስተመጨረሻም ኢትዮጵያውያን እንደሚያሸንፉ ምንም ጥርጥር እንደሌለኝ ነግረው ነበር።”
ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት በሁለት ግንባር የተከፈተባቸውን ጦርነት እየተዋጉ እንደሆነ፤ አንደኛው ቢቢሲን ጨምሮ የምዕራባውያን ሜዲያዎችና አለማቀፍ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት neocolonial disinformation and misinformation ጦርነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በነሱ የሚታገዘው ፋሽስት ወያኔ በአማራና በአፋር ላይ እያካሄደ ያለው የዘር ማጥፋት ጦርነት ነው የሚል ነበር። ይህ ሁሉ ተቆርጦ ቀርቷል። ቃለ መጠይቁን ላያስተላልፉት ይችላሉ በሚል ቀድቼዋለሁ። ለጊዜው ቢቢሲ ከዘጠኝ ቀናት በፊት (on November 28) ያቀረበው የቃለ መጠይቁ የመጀመሪያ ክፍል እነሆ!
Filed in: Amharic