>
5:28 pm - Thursday October 9, 6994

“ያፈገፈግነው የጀመርነውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል ብቃትም አቅምም ለማግኘት ነው” ( ጌታቸው ረዳ)

“ያፈገፈግነው የጀመርነውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል ብቃትም አቅምም ለማግኘት ነው”
አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል

የሞት የሽረት የመጨረሻ ብሎ ባደረገው  እንቅስቃሴ የአካል ጉዳተኛ የአእምሮ ህመምተኛ የሚመስሉ ከንግግራቸው ግምት ውስጥ አስገብተሽ የቀድሞ የጦር መኮንኖች ዘፈኞች ፣ዳንሰኞች ሁሉንም አይነት ሰው እያሰባሰበ በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀው የዘር ማጥፋት ዘመቻ የመጨረሻ ቅርፅ ለማስያዝ ያደረገው እንቅስቃሴ ሲያደርግ አይተናል፡፡
የእነዚህ ሰዎች ጩሀት ወታደራዊ በሆነው መስክ ላይ የለወጠው ነገር ባይኖርም ጠላት በተለይ ወደ ትግራይ ያቀርቡኛል ብሎ ያሰባቸው አካባቢዎችን  ለማጥቃት ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ነበሩ እነዚህ እንቅስቃሴዎች መገደብ ነበረባቸው ብቻ ሳይሆን ደብረብርሃን አካባቢ ያለው ሃይል ሌላ አካባቢ ወታደራዊ ጠቀሜታ በወቅቱ ስላልነበረው ያልነካናቸው አካባቢዎች ነበሩ ፡፡ እነዚህ ወታደራዊ ጠቀሜታ ስላልነበራቸው ያልናቸው አካባቢዎች ጭምር ሁሉም ወጮፎም ጓንዴም የተሸከመው ሀይል ጭምር ገጀራም የተሸከመ ሀይል በማሰባሰብ የግርግር ማእከላት ለማድረግ መንቀሳቀስ የጀመረበት ሁኔታ ነበር፡፡
ስለዚህ ይሄንን መልክ የማስያዝ ሰራዊታችን ሙሉ ትኩረቱ ጠላት በመደምሰስ ላይ እንዲያደርግ ትግራይ በአንድም በሌላ መልኩ ጥይት እንዲተኮስባት ለማድረግ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችንም ሰራዊታችን በተሟላ መልኩ እርምጃ እንዲወስድበት ከተፈለገ ፊት ያለው እንቅስቃሴ በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ መቀጠል መቻል አለበት ይህንን ለማድረግ የሚያስችል አጠቃላይ ቦታ ማስተካከያ ነው ያደረግነው ፡፡
 ሌሎች ታክቲካል አንፃር እነዚህ ነገሮች አሉ ኦፕሬሽናል ከሆኑ አንፃር የተወሰዱ እርምጃዎች አሉ ስለዚህ በሁሉም አቅጣጫዎች ባሉ የውጊያ እንቅስቃዎች በተናጠል ሲታዩ እዚህ ግባ የሚባል ትርጉም ባይኖራውም የሰራዊታችን ፍጥነት ከመግታት አንፃር በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ተፅእኖ እንዳይኖራቸው ያንን ተፅእኖ ማክሸፍ አለብን ብለን ስላመን ነው ያንን ስራ የሰራነው ፡፡
ዋናው ጦርነታችን አሁንም የትግራይ ህዝብ ህልውና በአሰተማማኝ ሁኔታ ማረጋገጥ እስከሆነ ድረስ ይህንን በአንድ ወይም በሌላ መልኩ ሊሸራርፉ የሚችሉ የትኩረት አቅጣጫችን የሚያዛቡ ነገሮች እነሱን መልክ ማስያዝ ስላለብን ወደኋላ ለመመለስ የሚያስችል ውሳኔ ወስነናል ያ ውሳኔ ከስትራቴጂካል ጠቀሜታዎች አንፃር አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት የጀመርነው ወታሃደራዊ እንቅስቃሴ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የሚችል ብቃትም አቅምም ስለሚፈጥርልን ያንን ግምት ውስጥ አስገብተን የወነው ውሳኔ ነው፡፡
የአብይ ጀነራሎች በተደጋጋሚ ሞክረው በአስር ሺዎች ነው የሚያስበሉት በየውጊያው ፣ሁሉም ሰራዊት አስፈጀተውታል አሁን ከምንገጥማቸው በምረኮም፣ ሞተው ከማናገኛቸው የጠላት መረጃዎች በአስር ሺዎች ነው የሚያልቀው ከዛ የ2014 ዓም ምልምል አንዳንዱ አንድ ወር አንዳንዱ 3 ቀን የሰለጠነ አለ ፣ጠብመንጃ ያለው አለ፣የሌለው አለ ስለዚህ ይህንን አስፈጅተሽ ለፎቶ የሚሆን ድል የሚመስል ነገር ከተገኘ የሚል እንቅስቃሴ አለ፡፡ ጦርነቱ የሞት የሽረት ነው ተብሎ ስለታመነ ጠላት አድርሰንበት ባለው ከፍተኛ የመዳከም ሁኔታ ሁኖ ጭምር የመጨረሻው ጦርነት ደም አፋሳሽ ለማድረግ የመጨረሻው ስራ እየሰራ ነው ይሉንታ ምናምን ቀርቶ ሽበት ያበቀሉ ሰዎች ሳይቀሩ እየወጡ ባልሆነ መንገድ የትግራይ ህዝብ መጨፍጨፍ እንዳለባቸው በአደባባይ እየሰበኩበት ያለ ሁኔታ ነው ያለው ፡፡
የአብይ ዘምቻሎህ ድራማ የለውጠው ነገር አለ ብየ አላምንም የለወጠው በእኛ በኩል ከእንቅስቃሴያችን አንፃር ምንድንነው በሁሉም አከባቢዎች  ትግራይን በቅርብ ርቀት ለማጥቃት ያስቹልኛል ብሎ ያሰባቸው አከባቢዎች በተለያየ አይነት የሰው ቁጥር በተለያየ አይነት ጠብመንጃ አድርጎ የሚሞክራችው እንቅስቃሴዎች ነበሩ እነሱን አክሽፈናል፡፡ እነሱን ብቻ ሳይሆን ደብረብርሃን አከባቢ የተከማቸ ሰራዊት ካለ ደብረ ብርሃን ተጠቃለህ ደብረታቦር የተከማቸ ጠላት ካለ ደብረታቦር ታጠፋዋለህ እዚህ ላይ ለእኛ ጠላት ለማጥፋት ብምናደርገው እንቅስቃሴ እዚህ ቦታ ካልሆነ ብለን የምንሟጎትብት እሰከ መጨረሻው አንገታችን ለሰይፍ እንሰጣለን የምንልበት ጂኦግራፊ የለም ፡፡ እስከመጨረሻ አንግታችን የሚስጥለት ጂኦግራፊ የትግራይ ግዛት ነው፡፣ ለዛ ሲባል ማንኛውም መስዋእት እንክፍላለን፡፡
ሁሉንም አከባቢዎች ስንወጣ ሁሉም አከባቢዎች ላይ በውጊያ እንዳልወጣን የአከባቢው ህዝብ ያውቃል የሚታዘበን ህዝብ ነው አብይ ፎቶ የተነሰባቸው አጋጣሚዎች አሉ ፎቶ የመነሳት አባዜ አለበት ከዛ በዘለለ እኛ መድረስ አለብን ብለን ያስቀመጠን ቦታ አለ በሙሉ አቅማችን መሰበር ያለበት መስበር መቻል አለብን ያንን ለማድረግ የሚያስችለን አቀም ይዘን ነው ፡፡በእግር 248 ኪሜ ተጉዞ በእዝ ደረጃ ለምሳሌ በኮምቦልቻ እና ከሜሴ መሀል ከአፈር በኩል በጣም ህዙፍ ሀይል በማስገባት የሰራዊታችን እንቅስቃሴ ለመግታት ተሞክሮ ነበረ እንድ እዝ ሙሉ ጨፍልቀን ነው ወደ አሰብንበት ቦታ የተመልስነው፡፡ ስለዚህ ለአብይ ለፎቶ ለመነሳት የሚሆኑ ከተሞች አግኝነቶ ሊሆን ይችላል ሰራዊቱ ከመበተን ከመደምሰስ ውጪ ይህንን አርገናል የሚያስችል ሞራል የለውም፡፡ዋናው ነገር የትግራይ ህዝብ ህልውና በአስተማማኝ ለማረጋገጥ የሚያስችል ማንኛውም ስራ እንሰራለን ከማንኛውም አይነት ጠላት ትግራይ ውስጥ የሚተኮስ መኖር የለበትም እስካሁን ድረስ ነፃ ያልወጣ የትግራይ አካባቢ አለ በምናደርገው እንቅስቃሴ ነፃ መውጣቱ አይቀርም የሚያጠራጥር ነገር የለውም፡፡
 አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ሴንተራል ኮማንድ አባል ከጣቢያችን ካደረጉት ቆይታ የተወሰደ
Filed in: Amharic