“ኢትዮጵያ አሸነፈች ” የምትሉ ጅሎች እፈሩ!!!
ሉሉ ከበደ
*…. ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆነው ሕዝቧ የውጭና የውሰጥ ጠላቶቹን ባጸዳ ማግስት የዚህ ሁሉ በሽታ ፣ ላገራችን ፣ ለወንድማማችነታችን ነቀርሳ ሆኖ ደም የሚያቃባን ቫይረስ ሲወገድ ነው። የወያኔን ተውሳክ ሐገ-መንግስት ቀዶ የፍቅር ፤የህብረት ፤የአንድነት ፤ ቃልኪዳን የሰፈረበት ሕገ መንግት አርቆ ስራ ላይ የሚያውል መንግስት ኢትዮጵያ ስታገኝ ነው አሸነፈች የምንለው። የኢትዮጵያ መሬት ተሸንሽኖ የጥቂት ዘሮች ንብረት መሆኑ የተረሳ ቀን ፤ምድሪቱ የሁላችንም የሆነች እለት ፤ ከክልሌ ውጣ ብሎ ወንድም ወንድሙን መግደል ያቆመ እለት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።
መልካም ነው ። የትግሬው ነጻ አውጪ ነኝ የሚለው ደም ያሰከረው የእብዶች ስብስብ፥ የሚፈልገውን ነገር በበቂ ሁኔታ ካደረገ በኋላ ፥ የወረረውን አካባቢ በግድም በውድም ጥሎ በመሄድ ላይ ይገኛል። ሰማእታቱ ፤ ተገፊ ፤ ጀግኖቻችን ፤ፋኖ ፤ ሚሊሺያው ፤ ሕዝባዊ ሀይሉ ፤ የኢትዮጵያ ወታደር ፤ በታላቅ ጀግንነት ህይወታቸውን ገብረው ራሳቸውን ሀገራቸውን ለጊዜው ነጻ አድረገዋል።ይሁንና ወራሪው የትግራይ ወንበዴ ብቻ አይደለም ። ኦነግ የዳቦ ስም እየቀያየረ ሶስት አመት ሆኖታል ወረራና ዘረፋ ጭፍጨፋ ከጀመረ። ሱዳን ሁለት አመት ሆኖታል ከሀምሳ ኪሎ ሜትር በላይ ዘልቆ መሬት ይዞ መግደል መዝረፍ ከጀመረ። እኔ ኢትዮጵያን እንደወረሩ ነው የማስበው። የክልሉ መንግስትም ፌዴራሉም የአማራ መሬት ነው በማለት አቅልለው ስላዩት ዝም ብለው ከርመዋል ። የኢትዮጵያ ህዝብ በሀገሩ መደፈር ፤ በክብሩ መዋረድ ፤ በሞቱ መብዛት ውስጡ በመንደድ ላይ ይገኛል። ራሱንና ዳር ድንበሩን ለማስከበር እንዳይችል አላስታጥቅ ፤አላደራጅ ፤ የሚል መንግስት በመምጣቱ ለፈርጀ ብዙ ጥቃት ተጋልጦ ዋጋ እንዲከፍል ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሁኑን ዘመቻ ማንቀሳቀሱ ራሱም መዝመቱ ጥሩ ነው። ሕዝቡ ጠላቶቹን ሊደቁስ እድል አገኘ።
ቀድሞም በትንሽ መስዋእትነት እዚያው በቀዬአቸው ሊገቱ የሚችሉ ትንኞች ናቸው አዲስ አበባ ጥግ ድረስ መተው ፣ እንደልባቸው እየገሰገሱ ኢትዮጵያ ልትሸከም የማትችውን ውድመት ያደረሱት። ካቀዱት በላይ ያሰቡትን ውድመት አድርሰዋል ። እንደ ሀገር ከዘለቀች ኢትዮጵያ ለአርባ አመት ወደኋላ ተመልሳ የምትሰራው ስራ ሰተዋታል ። ወደ መጡበት ቢመለሱም አሸናፊ እነሱ ናቸው። “ኢትዮጵያ አሸነፈች ” የምትሉ ጅሎች እፈሩ። እስከሚበቃቸው ገለው ፣ ዘርፈው አውድመው፥ አትርፈው ነው የሄዱት። እኛ ነን ከቁስላችን ጋር የቀረነው። በሌላ በኩል የትግራይ አረመኔዎች የሚሰሩትን ስራ የኦነግ አረመኔዎች ለሶስት አመት አየሰሩት ነው ። አማራ በሚሊዮኖች ቁም ስቅል እያየ በየቀኑ እንደ ጭዳ ዶሮ አየታረደ ነው። ንብረት እየወደመ እየተዘረፈ ነው። ከተማ እየተቃጠለ። አብይ በኦነግ ላይ ለመዝመት ሕዝቡንና ሰራዊቱን ለማንቀሳቀስ እነሱም እንደወያኔ ቤተ መንግስቱ አጠገብ መገኘት አለባቸው? ሱዳን ስሙም አይነሳ፥የሰው አገር ይዞ ተረጋግቶ ተቀምጧል። መቸ ነው አብይ ድንበራችንን እንድናስከብር የሚፈቅደው? የኢትዮጵያ ህዝብ አንጀቱ አሮ ቆስሏል። ኦነግ አይደለም ፤ ወያኔ ፤ ሱዳን አይደለም ፤የፈለገው ሀያል ይምጣ ለሕዝባችን የውስጥና የውጭ ጠላቶቹን ለማጥፋት ሶስት ወር ይበቃዋል። ማን ያደራጀው? ማን ያስታጥቀው?
አብይ አህመድ ጀምሮታል ። ዘመቻው ቢቀጥል ኢትዮጵያ ባጭር ጊዜ ትጸዳለች። ምንም የማይበግረው የተገፋ ሕዝብ ስላለ። ኢትዮጵያ አሸናፊ የምትሆነው ሕዝቧ የውጭና የውሰጥ ጠላቶቹን ባጸዳ ማግስት የዚህ ሁሉ በሽታ ፣ ላገራችን ፣ ለወንድማማችነታችን ነቀርሳ ሆኖ ደም የሚያቃባን ቫይረስ ሲወገድ ነው። የወያኔን ተውሳክ ሐገ-መንግስት ቀዶ የፍቅር ፤የህብረት ፤የአንድነት ፤ ቃልኪዳን የሰፈረበት ሕገ መንግት አርቆ ስራ ላይ የሚያውል መንግስት ኢትዮጵያ ስታገኝ ነው አሸነፈች የምንለው። የኢትዮጵያ መሬት ተሸንሽኖ የጥቂት ዘሮች ንብረት መሆኑ የተረሳ ቀን ፤ምድሪቱ የሁላችንም የሆነች እለት ፤ ከክልሌ ውጣ ብሎ ወንድም ወንድሙን መግደል ያቆመ እለት ኢትዮጵያ ታሸንፋለች።