ዶ/ር ሰማህኝ ጋሹ
ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነትና ስለ ጎጠኞች መናኛነት በአስደማሚ ሁኔታ የሚገልፀው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ መታሰሩ አስገራሚ ነው:: ኢትዮጵያዊ አንድነት ከምንግዜውም በላይ በተነሳሳበት በዚህ ወቅት ታምራት መታሰሩ የሚያሳየው አገዛዙ ይህንን ጦርነት ለማሸነፍ ኢትዮጵያዊነትን ቢያቀነቅንም አሁንም ከተጣባው የጎሳ ፖለቲካ ለመውጣት ሃሳብ እንደሌለው አመላካቸ ነው:: ወያኔም የሻእብያን ወረራ ለመቀልበስ ኢትዮጵያዊነት እንዲነሳሳ ካደረገ በሁዋላ ጦርነቱ ፍፃሜ ሲያገኝ ወደ ዘረኝነቱ ተመልሷል:: አሁንም ህዝቡ ህገ መንግስታዊ ለውጥ እንዲመጣ ከፈለገ አንድን ሰው ተስፋ አድርጎ ከመቀመጥ ለውጥ እንዲመጣ ተደራጅቶ መታገል አለበት:: ታምራት ልቀቁትና የሚወዳትን ኢትዮጵያ እንዲተርክ ፍቀዱለት::