>
5:13 pm - Tuesday April 20, 8371

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ስለወገናቸዉ የተሰዉ ጀግኖችን አንረሳም ያሉት ነገር እዉነት ከሆነ ይሄዉልዎት አቋራጩ መፍትሄ (ሸንቁጥ አየለ)

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ስለወገናቸዉ የተሰዉ ጀግኖችን አንረሳም ያሉት ነገር እዉነት ከሆነ ይሄዉልዎት አቋራጩ መፍትሄ
ሸንቁጥ አየለ

እርስዎ ከኦህዴድ ጋር ተሰልፈዉ የአማራ ነገድ  በኦነግ/ሸኔ ሲፈጅ ቆመዉ እያስተዋሉ ነዉ::ይሄን ነገር ድርጅትዎት ብአዴን ሲቆጣበት ወይም ለስላሳ መግለጫ እንኳን ሲያወጣበት አይታይም::ይሄን ነገር ቀን በቀን እግር በ እግር ለምንከታተል ሰዎች ሀመም ብቻ ሳይሆን መራራ የጥላቻ ምንጫችን ነዉ::
ግዴለም ይሄን ነገር እግዚአብሄር ይያዘዉ እና ለአሁኑ እንለፈዉ::
————–
ዛሬ የሰጡት መግለጫ ግን ጥቂት ስሜቴን ስቦኛል::ለህዝባችን  ክብር የተሰዉ ጀግኖችን አንረሳም ብለዋል::እዉነት ከሆነ በጣም ደስ ይላል::የአማራ ክልል አመራር:የብአዴን ባለስልጣናትን ስነልቦና በደንብ አዉቀዋለሁ::ዳተኛ ብቻ ሳይሆኑ  አድፋጭ እና አቀርቃሪ :የራሳቸዉ ጓዳ እስካልጎደለ ቀጥሎ ያለዉ ጎረቤታቸዉ ቤት ስለሚመላለሰዉ መቅሰፍታዊ ድህነት ግድ የማይሰጣቸዉ ናቸዉ::ለዛሬ እርስዎን ከዚያ ቡድን አወጣዎታለሁ::ይሄን የገቡትን ቃል ያልፈጸሙ እንደሆነም መልስሼ እዚያዉ ዝርዝር ዉስጥ አካትትዎታለሁ::
———
እንግዲህ የተሰዉ የጀግኖችን ቤተሰቦች  በዬወረዳዉ : በየዞኑ ያለዉ የብአዴን አመራር ግዴለሽ እና እጅግ እራስ ወዳድ ስለሆነ አይረዳቸዉም::ፕሮፖጋንዳዉን ግን እየተዉረገረገ እንደሚነፋ እርግጥ ነዉ::ያዉም አንገቱን እያረዘመ:ጣቱን እያፍተለተለ : ነገር እየሰበቀ ነዋ::
—–
እና ምን ይሻላል ብለዉ መጠዬቅዎት አይቀርም::
መፍትሄዉ በጣም እጅግ በጣም ቀላል ነዉ::
—-
የራስዎት ቢሮ የሚቆጣጠረዉ : ለተሰዉ ጀግኖች ቤተሰቦች ብቻ የሚዉል የጎፈንድ ሚ በራስዎት የቢሮ ሰዎች ይከፈት::በአፋጣኝም የተሰዉ ጀግኖች ዝርዝር ተጠናክሮ ከጎፈንድ ሚዉ ጋር ይዙር::
–ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ ጥሪ የተደረገለት ዲያስፖራም እያንዳንዱ አንድ ዶላር/ሁለት ዶላር እንዲያዋጣ ለመላዉ ዲያስፖራ በዬአድራሻዉ እንዲደርሰዉ ይላክለት::
–በተመሳሳይም ደረጃ የራሳችሁ የመንግስት ሚዲያ የሚባሉ በማህበራዊ ሚዲያ እና በዩቱዩብ እንዲለቁት መንግስት ተብዬዉ/የኔ ነገር እረስቸዉ ለካ የራሳችሁ መንግስት ነዉ????/ አቅጣጫ ይስጥበት::
–ህዝቡም የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዉም ጋዜጠኞችም በአጠቃላይ የምትከፍቱትን ጎፈንድ ሚ እንዲያሰራጭ በራስዎት አንደበት በአክብሮት ይጠይቁ
—–
እንኳንስ መላዉ አማራ : መላዉ የኢትዮጵያ ህብዝ ለጀግኖቹ ቤተሰብ ያዋጣል::
የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትህ አሳቢ ህዝብ ነዉ::የበሽታዉ ምንጭ የነገድ ፖለቲካ ተሸክመዉ ያመጡበት የፖለቲካ ድርጅቶች እንጂ::ስለሆነም የተሰዉ የጀግና ቤተሰቦችን የኢትዮጵያ ህዝብ በአንድ ሆኖ ይንከባከባቸዋል ለማለት ነዉ::
——-
ቁልፍ ነጥብ:-የሚከፈተዉ ጎፈንድ ሚ በራስዎት ቢሮ ቁጥጥር ስር መሆን ይኖርበታል::
—–
ይሄን ያደረጉ እንደሆነ ቢያንስ በወለጋ የአማራ ህዝብ ሲያልቅ ቆመዉ እየተመለከቱም ቢሆን ለወገን የተሰዉ ጀግኖች ቤተሰቦች መከራ እንዳይደርስባቸዉ ማድረግ ይችላሉ::
—-
በተሰበሰበዉ ገንዘብም በሚመረጡ ማዕከላዊ ወረዳዎች/ ወይም የተሻለ አማካይ ስፍራዎች/  በጀግኖች ቤተሰቦች የሚቋቋም በሼር ካምፓኒነት የሚፈጠር ቋሚ የገቢ ማስገኛ ቢዝነስ ወይም ደግሞ የተሻለ በጥናት የተረጋገጠ ቋሚ የገቢ ምንጭ የሚሆን ድርጅት ይመስረት::
——
እኛም ቆመን አፍጥጠን እያስተዋልን ነዉ::ይሄን ቅዱስ ስራ ያደርጉት ወይም አያደርጉት እንደሆነ::ይሄንንም ነገር ያደረጉ እንደሆነ እኛም የምንችለዉን እናግዛለን::
Filed in: Amharic