>

ክራይስስ ግሩፕ አዲስ መግለጫና አዲስ ጥሪ አቀረበ!!!! (ደጀኔ አሰፋ)

ክራይስስ ግሩፕ አዲስ መግለጫና አዲስ ጥሪ አቀረበ!!!!
ደጀኔ አሰፋ 

የጁንታው ሞት አይቀሬ መሆኑን እና የኢትዮጵያን አሸናፊነት የሚያረጋግጥ መግለጫ ነው!!!! 
 
የኢትዮጵያ መንግስት በጁንታው ተይዘው የነበሩትን በርካታ ቦታዎች መቆጣጠሩን እና ትልልቅ ድሎችን ማስመዝገቡን ተከትሎ የትህነግ አፍቃሪ በሆነው ዊሊያም ዴቪሰን የሚመራው ክራይስስ ግሩፕ አዲስ መግለጫ እና አዲስ ያልተለመደ ጥሪ አቅርቧል::
“…. የሁሉም ወገኖች ዕርምጃ የሰላም ድርድር ሂደቱ እንዲቀጥል ስለሚያደርግ
የትግራይ መሪዎች የፌደራል መንግስት ህጋዊነትን እውቅና እንዲሰጡ እንጠይቃለን” ብሏል::
በመግለጫውም… ወደ ድርድር ካልተገባ ጦርነቱ ላይቆም ይችላል ወዘተ የሚል በርካታ እንቶ ፈንቶዎችን እያንሻፈፈ የዘረዘረው ክራይስስ ግሩፕ: ያቀረበው ረዥም ሃተታ በዋነኛነት አንድ ሃሙስ የቀረውን ጁንታ ከማይቀርለት ሞት ለማዳን መሆኑ ከግልፅም በላይ ግልፅ ነው:: ‘ለማያቁሽ…’ ብለነዋል!!!  https://www.crisisgroup.org/africa/horn-africa/ethiopia/time-end-ethiopias-unwinnable-civil-war
በተለይ የክራይስስ ግሩፑ ዊሊያም ዴቪሰን እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ጁንታው አዲስ አበባን እንደሚቆጣጠር : የሚሌን መስመር እንደሚዘጋ… በእርግጠኝነት ሲናገር የነበረ ሲሆን ጁንታውን ከዓለም አቀፍ ውግዘት ለማዳን በየቀኑ በሚባል ደረጃ ሚዲያዎች ላይ እየቀረበ ስለ ጁንታው ጥብቅና የሚቆም በሰላም ስም የሚነግድ የአሸባሪው ጁንታ ቀንደኛ ተከፋይና ተላላኪ ነው!!!!
ታዲያ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር ተነስተው ወራሪውን አሸባሪ ሊደመስሱ ጫፍ በደረሱበት በዚህ ጊዜ  “ጁንታው የፌደራል መንግስት ቅቡልነትን እውቅና ይስጥና ወደ ድርድር ይገባ…ወዘተ”  የሚል ጥሪ ማቅረቡ በርግጥም የጁንታው ፍፃሜ እጅግ ቅርብ መሆኑን ያረጋግጣል!!!! የክራይስስ ግሩፕ መግለጫ የጁንታውን አይቀሬ ሞት ከማረጋገጥ የዘለለ ፋይዳ የለውም!!!!
በአጠቃላይ… ይህ በክራይስስ ግሩፕ በኩል የወጣው መግለጫ የጁንታው የድረሱልኝ ጩኸት እና የእሪታ ጥሪ መሆኑን ልብ ይሏል!!!!! ዳሩ ማንም አይሰማቸውም!!!!! ጁንታው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ካልተወገደ በቀር እረፍት የለም!!!! ይህም በቅርቡ ይረጋገጣል!!!!! ይህንን ሃቅ እነ ዊሊያም ያዩና ያለቅሳሉ!!!! ኢትዮጵያ እና ወዳጆቿም የድል ሳቅን ይስቃሉ!!!!!
በእርግጥም ኢትዮጵያ አሸንፋለች!!!!!!
ታላቅ ክብር ለኢትዮጵያ አምላክ!!!!! 
ክብር ለጀግኖቹ ሰማዕታት!!!!!
ክብር በየአውዱ ለሚዋደቁ ጀግኖቻችን በሙሉ!!!!!
Filed in: Amharic