>

ትላንት የታምራት ነገራ ዛሬ ደግሞ የመዓዛ መሐመድ መታሰር ስርዓቱ ምን ላይ እንዳለ የሚነግረን ፍንጭ አለ...!!! (ሰለሞን አላምኔ)

ትላንት የታምራት ነገራ ዛሬ ደግሞ የመዓዛ መሐመድ መታሰር ስርዓቱ ምን ላይ እንዳለ የሚነግረን ፍንጭ አለ…!!!
ሰለሞን አላምኔ

*…. አብይ አህመድ በፍፁም ህውሓትን ለማጥፋት አይፈልግም! እንዳለውም ደጋግሞ ለሀገር [ትርጉሙ ግን ለስልጣኑ] ስጋት እንዳትሆን  ማድረግ ነው። ሰሜኑን ለማድቀቅ ነው። ሁለቱም የሀገር ፀር የሆነው የህገ መንግስቱ ጠበቆች ናቸው
ህውሓት በአፏ እንደ ምትለው አብይ አህመድን አስወግዳ ስልጣን ለመያዝ አይደለም ይሄን የምታደርገው!! አማራን ለማጥፋት ብቻ እና ብቻ ነው።
አብይ አህመድ በፍፁም ህውሓትን ለማጥፋት አይፈልግም! እንዳለውም ደጋግሞ ለሀገር [ትርጉሙ ግን ለስልጣኑ] ስጋት እንዳትሆን  ማድረግ ነው። ሰሜኑን ለማድቀቅ ነው።
ሁለቱም የሀገር ፀር የሆነው የህገ መንግስቱ ጠበቆች ናቸው
በመቃብራችው ላይ ካልሆነ መቀየር አይፈልጉም። ጥያቄው ግልፅ ነው። ትግላችንም ግልፅ ነው። ሁለቱንም ፀረ ሀገርና ሀገር አፍራሾችን በጋራ ታግሎ ማስወገድ ነው። የግሌ አቋም ነው። so ደጋግሜ እንደምለው በአብይ አህመድ ዘመን የምትባባስ ኢትዮጲያ እንጅ የምትሻሻል ሀገር የለችም‼
ትላንት የታምራት ነገራ ዛሬ ደግሞ የመዓዛ መሐመድ መታሰር ስርዓቱ ምን ላይ እንዳለ የሚነግረን ፍንጭ አለ።አምባገነኖች መውደቂያቸው ሲቃረብ የሚያደርጉት ነገር በሙሉ አሁን ላይ በኢትዮጲያ እየተደረገ ነው። ልክ የሞላ የወንዝ ውሃ ከብትን ሲወስደው አይነት ነገር። ይቀጥላልም በርካታ ነገሮችም ከዚህ በኃላ ይፈጠራሉ። እኔ በግሌ የምጠብቀው ነው።
ሌላው ሰሞኑን እየታሰሩ ያሉት ሰዎች ላይ ሁለት አይነት ሰዎሽን እየተመለከትኩ ነው። አንደኛው በተሰጣቸው ጊዜያዊ አጀንዳ ብቻ የሚያምኑና የሚቀበሉ ኤርሚያስ ለገሰ እንደሚለው ጎርፍ አመጣች ፖለቲካ አቀንቃኞች ፊት ላይ መጥተው የአምባገነን ስርዓት እያዋለዱልን ይገኛሉ።
ሁለተኞቹ ግን ልክ ያኔ በዘመነ ህውሃት ጊዜ ለስርዓቱ አንደኛ አጎብዳጅ ሆነው ሲያገለግሉ እና እየጠቆሙ ሲያሳስሩ እንደነበሩት ፣ ዛሬም በዘመነ አብይ ኦህዴድ ለስርዓቱ ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ አገልጋይነትን አምነው የተቀበሉ እና የራስ የሆነ አቋም እና ህይወት የሌላቸው ” አይተነው ጊዜ ወደ አደላው ” አይነት ሰዎችም ፊት ላይ ዱላ እያቃበሉ ይገኛሉ።
በአብይ አህመድ ዘመን የምትባባስ ኢትዮጲያ እንጅ የምትሻሻል ሀገር የለችም። ዛሬ ላይ አምባገነን ስርዓት እያዋለዳችሁ ያላችሁ ነገ እናንተ ላይ እስሩ እንደማይቀር ላሳስባቸሁ እወዳለሁ። አብዬት ልጃን ብቻ ሳይሆን ውታፍ ነቃዩን ጭምር ትበላለች። ራሳችሁን በጊዜ በትፈትሹ ጥሩ ነው።
ትግሉ ይቀጥላል ዲሞክራሲ ታሸንፋለች ያኔ ሁላችንም ነፃ ነን
Filed in: Amharic