>

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ታሰረ....!!!" (ተራራ ኔትዎርክ ሚድያ )

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ታሰረ….!!!”
ተራራ ኔትዎርክ ሚድያ 

 

*…. ሀሳብን እና ትችትን ከህውሓት በላይ የሚፈራው ብልፅግና ጋዜጤኞችን ማሰሩን ስራየ ብሎ ተያይዞታል‼ ዛሬ ረፋዱ 4:30 ላይ Tamrat Negera መታሰሩን ሰማን። ያስዛናል በጣም! ጥሬ ሀቁ ግን ትችት ላወቀበት ምርኩዝ ነው

የተራራ ኔትዎርክ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዷል
 ጋዜጠኛ ታምራት ከመኖሪያ ቤቱ በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ገደማ  ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ነው  ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰደው።
የጋዜጠኛውን የመኖሪያ ቤት
 እና ቢሮ በመፈተሽም ለመረጃ ይፈለጋሉ ያሏቸውን  የሚዲያ ዕቃዎች በሙሉ ወስደዋል።
 ዕቃዎቹ  በዋናነት፣ ላፕቶፕ ፣ኮምፒተሮች፣ መቅረፀ ድምፅ፣ ፋላሽ ሚሞሪ፣ እና ሌሎች የሚዲያ መገልገያ መሣሪያዎች ናቸው።
 ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በምን ምክንያት እንደታሰረ የተገለፀ ነገር እንደሌለና ለጥያቄ ትፈለጋለህ በሚል ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደተወሰደ ታውቋል።
Filed in: Amharic