>

"ጀፍሪ ፊልትማን አዲሱ ዘዋሪ ...!!!" (ሱሌማን አብደላ)

“ጀፍሪ ፊልትማን አዲሱ ዘዋሪ …!!!”

.ሱሌማን አብደላ

በሰፈር ውስጥ አንድ የታወቀ ነብር ነበር። አንድ ቀን ከተኛበት ጉድጓት ወጣ ብሎ አካባቢውን ባይኑ መቃኛት እንደጀመረ ፊለፊቱ አለው ጋራ ላይ ያካባቢው ሚዷቋዎች ተሰብሰው ይመለከታል። ማንኛዋን ነው ዛሬ ለቁርስ የማደርጋት እያለ ከራሱ ጋር ሲመክር ሁሉም አንድ አይነቶች ይሆኑበታል። ቀርቦ ካላረጋገጠ ማንኛዋ የተሻለ ስጋ እንዳላት ማውቅ አልቻለም። በዚህ መሀል ተደናገረና ለነገሩ  እነዚህ ሁሉ ሚዳቆች የኔ ናቸው። የትስ ቢዘሉ ዘላለም አምልጠው አይኖሩም አለ። ሚዳቆ ከነብር ዘላለም እንደማታመልጠው ሁሉ የጀፍሪ ፊልትማን ዙረትም ከኢትዮጵያውያን አያልፍም።
.
የሆነው ሆኖ ፊልትማን እንደ ሱዳኗ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሬም ሳዲቅ እና እንደ ግብፁ ሳሚ ሽኩሪ የሚያዞር በሽታ ይዞታል። መሬም ኢትዮጵያ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ አለባት ብላ፣ የመጀመሪያውንም፣ የሁለተኛውንም የውሃ ሙሊት ለማስቀረት፣ ያልዘረችው አለም የለም ነበር። ከግብፁ ውጭ ጉዳይ ሳሚ ሽኩሪ ጋር በዙረት ፖለቲካ ተጠምደው የአለም መሳቂያ ከመሆን የዘለለ አንድም ያገኙት ውጤት የለም።
ይልቅ እኛ ውሃውን ሞልተን ጨርሰን ከዙረት ገላግለናቸዋል። ኢትዮጵያም ዘላለምሽን ዘዋሪ አይጣሽ ተብላ የተፀለየላት ይመስል ከአረብ ዘዋሪ ወደ ፈረንጅ ዘዋሪ አሸጋግሯታል።
ሰውየው የምስራቅ አፍሪካ አገሮችን ከአንዴም ሦስት ጊዜ ዞሯቸዋል። የመካከለኛው ምስራቅ አገሮችንም እንደዚሁ ዞሯቸዋል። ኬኒያማ በየሦስት ቀኑ እየመጣ መቀበሉ ሲያስችገራት ኧረ ይሄንን ሰውየ በምን ልገላገለው ብላ ያመጣውን አጀንዳ ሁሉ አፈር አስበልታ እንዳይመለስ አድርጋ ሸኝተዋለች። እሱኮ አያፍርም ተመልሶ ኬኒያም ይሄድ ይሆናል ።
የቀረችው የኢትዮጵያ ዘላለማዊ ጥላት የሆነችው ግብፅ ናት። ምቀኝነት ይላታል ሱዳናዊ ጋዜጠኛ ኢብራሂም አሊ፣ ምቀኝ ግብፅ ለኛ ምን እንደምታስብ እንኳን ፊልትማን የሦስት አመት ህፃን ልጅ ያቀዋል። ሰውየው በኬኒያ በሱዳን በአፍሪካ ህብረት በተመድ በቃ በሁሉም መንገድ ህወሓትን ለማዳን ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም። በሁሉም መንገድ ተዘግቶበታል። አቋማችንን በደንብ አይቶታል።
የመጨረሻ ያለውን የተስፋ መቁረጫ ( የብስጭት ጉዞውን) ጀምሯል። ቱርክን በኢትዮጵያ ጉዳይ አራት ጊዜ አናግሯታል። ስልክ በመደውል፣ በመሄድ ደብዳቤ በመፃፍ አሁን ደሞ ሄዶ ሊያናግራት ነው።
ኤምሬትን ብዙ ጊዜ ለምኗታል። ሁሉም መስመር ዝግ ነው። የቀረችው  የአል አለሚው ጋዜጠኛ እብራሂም አሊ ምቀኝነት የሚላት ግብፅ ናት። እሷን ምን እንደሚላትና እሷም” ምን እንደምትለው የታወቀ ነው። ግብፅ  እንኳን አሜሪካ ጋር አይደለም፣ ፊራኡን አስሮት የሄደው ሰይጣንም ጋር ተባብራ ኢትዮጵያን ለመበተን ያልሞከረች የሴራ አይነት የለም ሳይሳካ ቀረንጅ።
እኔን የገረመኝ ግን ጀፍሪ ፊልትማን በኢትዮጵያዊያን ምን ያህል ተበሳጭቶ ነው ብስጭቱን ለመወጣት ከግብፅ ጋር ስለኢትዮጵያ ጉዳይ እመክራለሁ ያለው .?
እንዲህ እንዳቃጠልነው አላቅም ነበር። ለማንኛውም ከኢትዮጵያ መንግስት ስለ ፊልትማን የግብፅ ጉዞ ጠንከር ያለ መልስ እንፈልጋለን።
Attachments area
Filed in: Amharic