>
5:09 pm - Wednesday March 3, 4534

"አትደነቁ!!! ቁልፉ ያለዉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ነዉ...!!!" (ሸንቁጥ አየለ)

“አትደነቁ!!! ቁልፉ ያለዉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ነዉ…!!!”
ሸንቁጥ አየለ

 

*…. ቁልፉ ያለዉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ነዉ። የበሩ መክፈቻም መዝጊያም ኢትዮጵያዊነት ነዉ። ያን ቁልፍ በትክክል ያገኘ የራሱንም የሌላዉንም ነገድ ያድናል።ኢትዮጵያዊነት እንኳን በትክክል ተሰርቶበት ይቅርና በማጨናበር ብዙ ጉልበት አለዉ
የክፍለ ሀገር ፖለቲካ የትም አይደርስም። አንድ ጋጥ ውስጥ ተሰባስቦ ከመጨፈር፡ ከማሽካካት እና ከመሸለል የዘለለ እርምጃ አይሄድም። እንኳን የክፍለ ሀገር ፖለቲካ ቀርቶ የብሄር ፖለቲካ እራሱ ሆድ ለመሙላት ሌላዉን ነገድ ለመጨፍጨፍ እና በጎሳ ዘፈን እየዘለሉ ስሜት ለማብረድ ካልሆነ በቀር ዘመን የሚሻገር አንዳች ቁም ነገር አይፈይድም። አሁን ህዉሃት ለትግሬ ህዝብ ጥፋት እና መጠላት እንጂ ምን አተረፈለት? ህዉሃት በትግራይ የገነባዉ ሁሉ በወራት ወድሟል።
በህዉሃት የተነሳ ቀሪዉ ኢትዮጵያዊ ነገድ ብቻ አሳሩን በልቶ አልቀረም። በህዉሃት የጎሳ ፖለቲካ ምክንያት የትግራይ ህዝብ አበሳ ገና ሀ ብሎ ጀምሯል። እንኳን የክፍለ ሀገር ፖለቲካ የነገድ ፖለቲካ እራሱ እይታዉ የማያድግ፡ ወደ ዞን እና ወረዳ ብሎ ወደ ቀበሌ ገበሬ ማህብር ብሎም ወደ ጎጥ ሲዘልም ወደ ዘመዳሞች እና ቤተሰብ ቆጠራ የሚያድግ  ነዉ:: የቁልቁለት ጉዞ መቆሚያ የማይኖረዉ አዘቅት ዉስጥ ይዞ የሚገባ ነዉ።
ቁልፉ ያለዉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ነዉ። የበሩ መክፈቻም መዝጊያም ኢትዮጵያዊነት ነዉ። ያን ቁልፍ በትክክል ያገኘ የራሱንም የሌላዉንም ነገድ ያድናል።ኢትዮጵያዊነት እንኳን በትክክል ተሰርቶበት ይቅርና በማጨናበር ብዙ ጉልበት አለዉ።
ኦነግ 70 አመታት ታግሎ ያልተሳካለትን ኢትዮጵያን የማወዳደም ስራ አቢይ አህመድ በሃሰት በማስመሰል እና በማጨናበር ኢትዮጵያዊነት እያለ በ7 ወራት ዉስጥ እጅግ አስፈሪ የሰይጣን ስራ መስራት ችሏል።
አማራዉን እና ሌላዉን ኢትዮጵያዊ አፉን አስከፍቶ አማራዉ በኦህዴድ፡ በኦነግ እና በሸኔ በሚሊዮን ቁጥር ሲጨፈጨፍ አማራዉን አፉን አሲዞ እያዘለለ ብዙ የዘር ፍጅት መፈጸም ችሏል። ይሄም የሆነዉ ኢትዮጵያዊነትን ለማስመሰያ እንደ አርማ በማንሳቱ ነዉ።
የሆኖ ሆኖ የኢትዮጵያን ቁልፍ ማግኘት ቢያቅት የአማራነትን ቁልፍ መፈለግ ሲገባ በክፍለ ሀገር ወርዶ ስትራቴጂ መንደፍ  እና ሌሎችን ለመቆጣጠር መሞከር ታላቅ መሳለቂያ መሆን ነዉ።
ምናልባትም ይሄን ሰነድ ከኦህዴድ ጋር ሆነዉ አዳዲስ የአቢይ ወዶ ገቦች አዘጋጅተዉ ወደ እኛ እንዲደርስ አድርገዉት ሊሆን ይችላል። የኦህዴድን የፕሮፖጋንዳ ክህሎት ለማወቅ ጥቂት ነገር ብቻ ወደ ኋላ ሄዶ ማዬት በቂ ነዉ።
ኦሮ አማራ የሚል የማጭበርበሪያ ፕሮፖጋንዳ ፈጥሮ ጥቂት የአማራ ወዶገቦችን ከብአዴን አካቶ መላዉ ኢትዮጵያን በተለይም መላዉ አማራን ጨርቁን እስኪጥል አስጨፍሮት ነበር።
ወራት ሳይቆይ ግን የአማሮች ደም እና ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዉያን ጎሳዎች ደም ከዉሻ ደም እንኳን ያነሰ ዋጋ እንዳለዉ ኦህዴድ ነገረን። ኦነግ ሸኔ ይጨፈጭፋል ኦህዴድ ቆሞ ያስጨፈጭፋል። ሌሎች ነገዶች እራሳቸዉን ሊከላከሉ ሲሞክሩ ኦህዴድ ትጥቅ ያስፈታል።
 የኦህዴድ ፖለቲከኞች በመላዉ ኦሮሚያ ሚሊዮኖች ሲጨፈጨፉና ግለሰቦች ተዘቅዝቀዉ ሲሰቀሉ መላዉን የአማራ ፖለቲከኛና ምሁር አይኑን አደንዝዘዉ አፉን ለጉመዉ መያዝ የቻሉት ብዙ የተራቀቀ የፕሮፖጋንዳ ስልት በመከተል ነዉ።
 እናም ኦህዴድ የዋዛ ፕሮፖጋንዳ ጉልበት የለዉም።
በመሆኑም አሁን አማራዉን በክፍለ ሀገር ለመከፋፈል የተወሰኑ ወዶ ገቦችን ይዘዉ ያዘጋጁት ሰነድ ሊሆን ይችላል። የሆነ ሆኖ ግን ሰነዱ የአጼ ቴዎድሮስን ጀግና ልጆች ፈጽሞ አይወክልም።
 ከብአዴ፡ እንዲሁም በአማራ ብሄረተኝነት ከሚያጨበረብሩ የአሳማ ብሄረተኞች የተወሰኑ ምናምንቴዎችን ኦህዴድ በመቃረም እንዲህ አይነት ሰነድ አዘጋጅቶ ለኛ እንዲደርሰን እና እርስ በርስ በጥርጣሬ እንድንተያይ እየሰራ ሊሆን ይችላል።
ሲጠቃለል ግን ቁልፉ ያለዉ ኢትዮጵያዊነት ላይ ነዉ። የበሩ መክፈቻም መዝጊያም ኢትዮጵያዊነት ነዉ። ያን ቁልፍ በትክክል ያገኘ የራሱንም የሌላዉንም ነገድ ያድናል።
Filed in: Amharic