>
5:26 pm - Thursday September 15, 4889

ከኢትዮጵያ በታች ነን ....!!! ሀይሌ ገብረስላሴ

ከኢትዮጵያ በታች ነን ….!!!

ሀይሌ ገብረስላሴ

አይደለም ሀገር ለማፍረስ ከተነሳ ቡድን ጋር የሚሰለፍ ይቅርና !ሀገርን ለመታደግ ከህዝብ ጎን የተሰለፍነውም ማንኛችንም አካል ከኢትዮጵያ በታች ነን ።
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ለማስነሳት ያለመ ዘመቻ እየተካሄደ ነው!!
 በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆነውን አሸባሪው ህወሓትን በውጭ በመምራት ላይ የሚገኘውን ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ለማስነሳት ያለመ ዘመቻ እየተካሄደ ነው።
አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን እንዲሁም ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂ የሆነውን የአሸባሪው ህወሓት ድርጊቶችን ማስረጃ በመያዝ የሽብር ቡድኑን አመራሮች ተጠያቂ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው።
በዚህም የዓለም ጤና ድርጅት መርህ ከሚያዘው ገለልተኝነት፣ ታማኝነትና ግልጸኝነት ውጪ በመስራት ለአሸባሪው ህወሓት በውጭ ድጋፍና አመራር በመስጠት ላይ የሚገኘው ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖምን ተጠያቂ ለማድረግ የፊርማ መሰባሰብ ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ዶክተር ቴድሮስ ዓለም አቀፍ ሀላፊነቱን በመጠቀም የሽብር ቡድን በአገር ውስጥ የሚፈጽማቸውን ዓለም አቀፍ ወንጀሎች በመሸፈንና ይልቁንም በሚሊየኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሊጠቅሙ የሚችሉ የጤና ተቋማት በሽብር ቡድኑ ሲወድሙ ባላየ በማለፍ ለሽብር ቡድኑ ሽፋን መስጠቱ ዘመቻው ለዓለም ጤና ድርጅት በሚልከው የፊርማ ማሰባሰቢያ ዘመቻ አመልክቷል።
    ሁሉም ሰው ከኢትዮጵያ በታች ነው !
     እናሸንፍለን..(ይቻላል)
Filed in: Amharic