>
5:13 pm - Sunday April 19, 8703

የዐፄ ቴዎድሮስ መካነ መቃብር የት እንደሚገኝ ያውቁ ይሆን? (ትንቢተ ኢትዮጰያ)

የዐፄ ቴዎድሮስ መካነ መቃብር የት እንደሚገኝ ያውቁ ይሆን?
ትንቢተ ኢትዮጰያ

ዐፄ ቴዎድሮስ የተቀበሩት በተማሩበት ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ነው።ማኅበረ ሥላሴ ገዳም የሚገኘው ጎንደር መተማ በረሃ ውስጥ ሲሆን የዐፄ ቴዎድሮስ መቃነ መቃብርም የሚገኘው በፎቶ በምታዮት በጥራርና በቆርቆሮ በተሰራች ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ነው።
ይኼም የሆነበት ምክንያት ዐፄ ቴዎድሮስ “ማኅበረ ሥላሴ ቅበሩኝ” ብለው በመናዘዛቸው በልጃቸው በመሸሸሻ ቴዎድሮስ አማካኝነት እዚሁ ስፍራ ሊቀበሩ ችለዋል።
ማኅበረ ሥላሴ ገዳም በ4ኛው መክዘ በወንድማማቾቹ የአክሱም ነገሥታት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን እንደተሰራ ይነገራል።ዳግመኛም በ17ኛው መክዘ በተነሡት ጻድቁ ዓምደ ሥላሴ በተባሉት ደገኛ አባት ይበለጡን ተሥፋፍቶ ሥርዓተ አበው ሰፍቶ እስካሁን ድረስ የጥንቱን ሥርዓት ሳይለቅ ሥርዓቱን እንደጠበቀ የሚገኝ ገዳም ነው።
Filed in: Amharic