>

"የህውሃት አመራሮችን - ሁሉንም ግፈኞች  በተገኙበት ለፍርድ ማቅረብ   ይገባል...!!!" (ያሬድ ሀይለማርያም)

“የህውሃት አመራሮችን – ሁሉንም ግፈኞች 
በተገኙበት አለም መክሰስና ለፍርድ ማቅረብ   ይገባል…!!!”
ያሬድ ሀይለማርያም

የወያኔ/ኢህአዴግ አመራሮች 27 ዓመት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለፈጸሙት ግፍ እና ሰቆቃ ተጠያቂ መሆን አለመቻላቸው የጨካኝነት ደረጃቸውን ወደ ለየለት እብደት ከፍ ያደረገው መሆኑን በአማራ እና በአፋር ክልል የፈጸሙዋቸው ሰቆቃዎች ከበቂ በላይ ማሳያዎች ናቸው።

ሴቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ ደፍረዋል፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን፣ አየር ማረፊያዎችን አውድመዋል፣ በርካታ ተቋማትን ዘርፈዋል።
ይህ የግፍ ግፍ አድራጎት ልክ ትግራይ ላይ የተፈጸሙትን ተመሳሳይ ጥፋቶች የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከUN ጋር በጣምራ አጣርቶ እንዳወጣው ሁሉ በአፋርና በአማራ ክልል በተፈጸሙት ሰቆቃዎችም ላይ ተመሳሳይ ምርመራ ማድረግና አጥፊዎችን ለፍርድ እንዲቀርቡ መደረግ ይገባ። ከዚህ በፊት የህውሃት አመራሮችን በተገኙበት አለም ለመክሰስና ለፍርድ ለማቅረብ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተጀመሩ ጥረቶች አሁንም ሁሉንም ግፈኞች ለፍርድ ለማቅረብ ተጠናክረው ሊቀጥል ይገባል።
Filed in: Amharic