ተራራ ኔትዎርክ ሚድያ
*.... በ ፍርድ ቤት ቆይታውም አቃቢ ህግ የጠየቀው የ 14ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶለታል!
የተራራ ኔትዎርክ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከአዲስአበባ ፖሊስ ተላልፎ በኦሮሚያ ክልል ገለን ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንደታሰረ ታውቋል።
ጋዜጠኛው ላለፉት ስምንት ቀናት የት እንዳለ ሳይታወቅ ቆይቶ በትናንትናው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቡንም ባለቤቱ ወይዘሮ ሰላም በላይ አስታውቀዋል ።
በፊንፊኔ ዙሪያ የገለን ከተማ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የ14 ቀን ቀጠሮ እንደሰጠውም ተነግሯል። ባሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰደ ሲሆን ላለፉት 7 ቀናት የት እንደታሰረ ቤተሰቦቹ ማወቅ እንዳልቻሉ ተናግረው ነበር።
ጋዜጠኛ ታምራት በ አሁን ሰዓት በገላን ከተማ ኦሮሚያ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ እንደሚገኝ ባለቤቱ ወ/ሮ ሰላም በላይ ተናግረዋል። ከፌደራል ፖሊስ ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ በ ኦሮሚያ ፖሊስ ጠያቂነት እንደተዛወረም ታውቋል።
በ ፍርድ ቤት ቆይታውም አቃቢ ህግ በጠየቀው የ 14ቀን የጊዜ ቀጠሮ መሰረት የተፈቀደለት መሆኑን እንዲሁም የታምራት ቤተሰቦች ብቻ ለጥየቃ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ባለቤታቸው ወ/ሮ ሰላም ተናግረዋል ።