>

አውሮፓ ቁጭ ብሎ በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ለመነጋገር መጠራራት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እንደ መሳለቅ ይቆጠራል‼ (ኢ ፕ ድ) 

አውሮፓ ቁጭ ብሎ በኢትዮጵያ ስለተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ለመነጋገር መጠራራት በሰብዓዊ መብቶች ላይ እንደ መሳለቅ ይቆጠራል‼
(ኢ ፕ ድ)

ከሀዲው ሕወሓት እና ተባባሪዎቹ እየፈጸሙባት ባለው ወረራና ግፍ ብዙ ዜጎች በአሳሳቢ የሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የደህንነት ኃይሎች ጥምረት ከአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ነጻ በወጡ የአማራና አፋር ክልሎች ቡድኑ የፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አስመልክቶ እየተሰሙ ያሉ የስቃይ ድምጾችና በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የተለያዩ ተቋማት ላይ ቡድኑ የፈጸማቸውን ዘረፋዎችና ውድመቶች አስመልክቶ እየቀረቡ ያሉ ዘገባዎች ይህንኑ ያስገነዝባሉ።
አሸባሪው ሕወሓት ያደረሰው ሰብዓዊ ቀውስ ተዘርዝሮ አያልቅም። በአማራን አፋር ክልል አሁን ቡድኑ የፈጸመውን ዘግናኝ ድርጊት የሚያውቁት ወረራው የተፈጸመባቸው ዜጎች፣ ወረራው የተፈጸመባቸው አካባቢዎች ሕዝብ ፣የክልሎቹ ነዋሪዎች፣ የየክልሎቹ መንግሥታትና ሕዝብ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ብቻ ናቸው።
ምሉዕ ባይሆንም አምነስቲ ኢንተርናሽናልና የኢትዮጵያና የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽኖች ባወጡት መግለጫ አሸባሪው ሕወሓት በንጹሃን ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ መፈጸሙን፣ ታጣቂዎቹ በጦር መሳሪያ እያስፈራሩ በቡድን ሴቶችን አስገድደው መድፈራቸውን፣ ጌጣ ጌጣቸውን መቀማታቸውን ፣ ጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ልዩነቶች እንዳሉ ሆነው እነዚህ ተቋማት ላደረጉት ጥረት አድናቆቱን ገልጿል።
በዚህ ወቅትም ለኢትዮጵያ ከሚያስፈልጉት መካከል አንዱ ይህ ነው። ችግር የደረሰበት ቦታ መገኘትና በፍትሐዊነትና በገለልተኝነት ማጥናት ችግሩን ፈጥሯል የተባለውን ቡድን በይፋ ማውገዝ፣ ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዘ ሥራ ከሚሰሩ ተቋማት ይጠበቃል። ይህን ሳያደርጉ ለሰብዓዊ መብት እቆረቆራለሁ ማለትም ሆነ ተፈጸመ ስለተባለው ሰብዓዊ መብት ጥሰት ማውራት ተገቢ …
የዚህን ዜና ሙሉ መረጃ ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
Filed in: Amharic