>

“ ጦርነቱ ያልተፈለገና ትርጉም የለሽ በመሆኑ  ከጅምሩም መደረግ አልነበረበትም...!!!!" (ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ)

ጦርነቱ ያልተፈለገና ትርጉም የለሽ በመሆኑ  ከጅምሩም መደረግ አልነበረበትም…!!!!”
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

“…. በጊዜው ልዩነቶች ወደ ጦርነት እንዳያመሩ ብዙ ከለፉት ውስጥ አንዱ ነኝ ፤ ዛሬ ላይ ግን ያ ልዩነት ሰፍቶ አገሬን የሚያሳጣኝ ከሆነ መከፈል ያለበትን ዋጋ እከፍላለሁ…!!!
የህወሓት ኃይሎች በቅርቡ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች መዝለቃቸውን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሩት የመንግስትን ጥምር ጦር በመከተል ዘመቻው ላይ የተሳተፈው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ምን ይላል?
ኃይሌ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ “ያልተፈለገና ትርጉም የለሽ ጦርነቱ ከጅምሩም መደረግ ያልነበረበትና ልዩነቶች ወደ ጦርነት እንዳያመሩ ብዙ ከለፉት ውስጥ አንዱ ነኝ” ይላል፡፡
ለአሁናዊው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት መፍትሄው የሚመጣው “ከራሳቸው ከኢትዮጵያውያን ብቻ ሲሆን ነው” ሲል አስተያየቱንም ገልጿል ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ፡፡
ቪዲዮ ፡- ስዩም ጌቱ (DW) ከአዲስ አበባ

https://fb.watch/9YhIzArEu0/

Filed in: Amharic