>

ባለውለታዎቻችን....   !!! (ዘመድኩን በቀለ)

ባለውለታዎቻችን….   !!!

ዘመድኩን በቀለ

*…. እግዚአብሔር ባወቀ እኒህ ሶዬዎች ለሂዊ መድቀቅ… ለኢትዮጵያ ትንሳኤም ምክንያት የሆኑ የኢትዮጵያም የዐማራም ባለውለታዎች ናቸው። እንዴት? አትሉኝም…  ያው ከታች የተቀመጠውን ጦማር አንብቡት….!

“… አቶ ጌታቸው ጌታቸው ረዳ ማለት በዘመናችን ኢትዮጵያንም ዐማራንም ያነቃ የኢትዮጵያም የዐማራም ባለውለታ የሆነ ሰው ነው። በእውነት እኔ እንደምጠረጥረው ከሆነ ሟች ሴኮቱሬ ጌታቸውና ተጠባባቂ ሟች አቶ ጌታቸው ረዳን ፈጣሪ ለኢትዮጵያችን ትንሣኤ፣ ለወያኔም ውድቀትና ሞት መፋጠን ምክንያት አድርጎ የላካቸው መልእክተኞች ናቸው ብዬ ነው የማምነው። ከምር ምስጋናዬ ካሉበት ይድረሳቸው።
…በተለይ የራያው ተወላጅ አቶ ጌታቸው ረዳ ካሣ… ዐማራ ሆኖ መፈጠሩ ለወገኑ ለዐማራና ለሃገሩ ለኢትዮጵያ ትልቅ የመዳን ምክንያት ነው የሆነላት። እህቱ የዐማራ ፖሊስ ናት አሉ። ይሄም በእውነት ትልቅ ጥቅም ነበረው። በመረጃ መለዋወጥ በኩል ማለት ነው። ጌታቸው ረዳ ገና በልጅነቱ ነው ወደ ፖለቲካው የተቀላቀለው ይላሉ አጎቱ። የራያ ማንነት አስመላሽ ይሁን የራያ ራዩማ ብቻ የሆነ የራያ ፓርቲ አቋቁሞ አዲስ አበባ ይሄዳል። ነቃ ያለ፣ ቀልጣፋ፣ ምላሰ ረጅም መሆኑን መለስ ዜናዊ (ነአ) ያየውና ይሄ ሰው ይጠቅመናል ብሎ ሰብኮ አስቀረው ይላሉ አክስቱ።
…ወጪ አውጥተው አስተማሩት። የሚፈልገውን መጠጥና ሴት በአይነት በዓይነት አቀረቡለት። የህወሓት ምላስ አንደበቷ የነበረው መለስ ዜናዊ ወደ መቃብር ሲወርድ ህወሓት ምላሷ ተቆረጠ። ተብታባ ብቻ በህወሓት ውስጥ በዛ። ከመሃላቸው ምላስ ያለው ጌታቸው ረዳ ብቻ ሆኖ ተገኘ። እናም ይናገርላቸው፣ ይከራከርላቸው ዘንድም መረጡት። በላያቸውም ላይ ሾሙት። አነገሡት ይላሉ ታሪኩን የሚያውቁት አያቱ።
…ጌቾ በዚህ በኩል የዐቢይ አሕመድ ጓደኛ ነው። ያውም የልብ ወዳጅ የሚሉም አሉ። ይሄንን ጌቾ ራሱ ብዙ ጊዜ ተናግሮታል። በዚህ ወገንም ሚሽን ተሰጥቶታል ይሉታል ፈረንጆቹ በእኛ ደግሞ ተልዕኮ ተሰጠው እንደማለት ያለ ነው። እሱን ሚሽኑንም ምሱንም ተቀብሎ ነው ህወሓትን ድምጥማጧን ለማጥፋት ተመሳስሎ መሃላቸው የገባው የሚሉም አሉ። አስመራ ተወልዳ፣ አስመራ አድጋ፣ ከዐቢቹ ጋር አስመራን የጎበኘችው ኬሪያ ኢብራሂምም እነ አቦይ ስብሃት ያሉበትን፣ እነስዪም መስፍን የተደበቁበትን ጠቁማ ሚሽኗን ስትጨርስ መጀመሪያ ለመከላከያ እጇን የሰጠችው የእነ ዐቢይ አሕመድ ሰላይም ድሮንም ስለነበረች ነው ይላሉ ዘመዶቿ።
…አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸውም ወዶ ገብ ዐማራሂዊ ሲሆን በፈቃዱ ትግሬ መባልን የመረጠ የወያኔ ዛር የሰፈረበት ምስኪን ነበርም የሚሉም ጓዶች አሉ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፊቱን ፀፍቶ፣ አንደበቱንም ከፍቶ ህወሓት የሰሜን ዕዝ ላይ “መብረቃዊ ጥቃት” መክፋቷን ቴሌቭዥን ወጥቶ ባይመስክር ኖሮ የሀሰት አባት፣ የሀሰት ፈጣሪዋ ወዩ ሂዊ ይሄኔ ሸምጥጣ በካደች ነበር። የኢትዮጵያ አምላክ፣ የንፁሐን አምላክ፣ ግን በወዶ ገቡ ከሃዲዐማራው በአቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው ላይ አድሮ እውነት በመናገር ሂዊን አስበላት ይላሉ ጓደኞቹ።
…ጌታቸው ረዳም እንደዚያው ነው። “ኢትዮጵያን ሲኦል ድረስም ቢሆን ወርደን እናፈርሳታለን” ባይል ኖሮ ኢትዮጵያውያን እንዲህ ግልብጥ ብለው ወጥተው በመትመም የትግሬን ወራሪ ጦር ባልደቆሱት ነበር። ዐማራው አቶ ጌታቸው ረዳ በአደባባይ ወጥቶ “ከዐማራ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን” ባይልና ባይናገር ኖሮ ዐማራው እንዲህ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ሂዊን ሳንዲዊች ባላደረጋት ነበር ይላሉ ጎረቤቶቹ።
… ጄ ጻድቃን ገብረ ትንሣኤ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ዶ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ አቶ ሴኮቱሬ ጌታቸው፣ ጎንደሬው አክ ቱ ሺስት አቶ እንዳ በርበረ አሉላ ሰሎሞን፣ አስር አለቃ እስታሊን ገብረ ሥላሴ፣ ኢትዮጵያን በማዋረድ፣ ዐማራን በመስደብ፣ በማብሸቅም ዐማራውን ጀት ያደረጉ፣ ኢትዮጵያን በማዋረድ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያቸውን እንዲያስከብሩ ያነሣሡ ባለውለታዎቻች ናቸው። ኢትዮጵያን እናፈርሳለን በማለት ደስኩረው፣ ፎክረው፣ አቅራርተው የኢትዮጵያውያንን በላ በላያቸው ላይ ያዘነቡ ባለውለታዎቻችን ናቸው ይላሉ ኢትዮጵያውያኖቹ። እንጂማ በዐቢይ አሕመድ ፉገራ፣ በታዬ ደንደአ እና በሽመልስ አብዲሳ ፉከራ ፈቅም አይባል ነበር። የአቶ አገኘሁ ሽጉጤን እጠጣለሁ ማለትም ወሬ ሆኖ በቀረ ነበር። ዕድሜ ለእነ ጌታቸው። ፒፕሉን አበሳጭተው ድባቅ ተመቱ። እንደ ንብ መንጋ ነው የሰፈረባቸው።
…አሁንም ቢሆን አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚዲያ ባይርቅ ጥሩ ነበር። ኮንጆ ኮንጆ ጋለሞታ ከፊቱ ደርድሮ፣ አረቄና ጠጅ እየጋቱ ማይክ ማስጨበጥ ብቻ ነው ለኢትዮጵያ የሚያዋጣው። ጌታቸው ሲናገር ድል አለ። አሁን በዚያ ሰሞን ሚዲያ ላይ ወጥቶ “አሜሪካ አንድ ጊዜ ወደ አዲስ አበባ ግቡ ትለናለች፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ቆይ ተረጋጉ ትለናለች” ብሎ በመናገሩ እንዴት ለኢትዮጵያ እንደጠቀማት አይታችኋል። እነ #NOMOሮችን ሁሉ ነው ያስናቀው። አሜሪካም “እኔ የለሁበትም፣ አቶ ጌታቸው ስሚያወራው ነገር የማውቀው ነገር የለም” ብላ እሪሪ እስክትል ያደረሳት፣ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋ በኩል አፍራ በአስመራ ኤምባሲ በኩል እስክትቃወም ያደረሳት የአቶ ጌታቸው ምላስ ነው ይላሉ ታዛቢዎቹ። የጌቾን ምላስ አይጠፍብን።
…እንደ ጌታቸው ረዳ ዓይነት ነጥብ የሚጥል ፋውል የሚሠራ ማኖ የሚነካ ተጫዋች በሜዳው ላይ በዚያ ወገን ባይሰለፍ ባይኖርም ኖሮ ኢትዮጵያማ ለዋንጫ ጨዋታው አታልፍም ዋንጫውንም አትበላም ነበር የሚሉም አሉ። ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ወገን ለኢትዮጵያ የሚጫወቱ ዲፕሎማቶች የጌታቸው ረዳን ያህል ሲጠቅሟት አልታዩም። አምባሳደር ፍፁም አረጋ አሜሪካን ያህል ሃገር ተቀምጠው ምን ፈየዱ? እርሳቸው በማኅበራቱ ስብሰባ ላይ በመገኘት ዳቦ ሲቆርሱ ከመዋል በቀር ምን አመጡ? አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ፣ አምባሳደር ካሣ ተክለብርሃን ባሉበት ሃገር ይኑሩ ይሙቱ የሚያውቅ እንኳ የለም። እናም ከሁሉም አምባሳደሮች በላይ ለኢትዮጵያ ማሸነፍ እንደ ጌታቸው ራዳ የጠቀማት የለም ይላሉ የዲፕሎማቶቹ ጫማ ጠራጊ ሊስትሮዎች።
…እኔ ግን እላለሁ ጌታቸው ረዳ እና ደብረ ጽዮን ሚሽናቸውን የጨረሱ ስለሚመስለኝ በጊዜ እጃቸውን ለኢትዮጵያ መንግሥት ቢሰጡ መልካም ነው እላለሁ። እስከአሁን በውስጥ ሆነው ሂዊን ያደቀቋት ይበቃል። እናም ወያኔዎቹ ነቅተው ሳይተናኮሏቸው መላ ቢፈለግላቸው መልካም ነው። ከምር ከነቁ  ይገድሏቸዋል። እስከአሁን ድረስም ስላልባነኑ ነው እንጂ ትልና ታቀሳስራለህ… ለማንኛውም እኔ ዝምብዬ ነው ቀኝ ትከሻዬን ስለሸከከኝ የቀባጠርኩት። ደግሞ የምር ወስዳችሁ እነ ጌቾን ተተናኮሏቸው አሏችሁ። ኢትዮጵያ ግን ታፈርስሃለች እንጂ እሷ መቼም ከቶም ቢሆን አትፈርስም። አፍራሽ ነኝ ባይ ሁላ አናት ልብህ ኩላሊት አንጀትህ ይፈረስ… አሜን በል  ‼
• የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን አንብባችሁ ስትጨርሱ እከፍትላችኋለሁ። እስከዚያ ኮምኩሙት።
Filed in: Amharic