>

የአማራን መጨፍጨፍ እንዳያስቆም ኦህዴድን ያባለጉት የአማራ ፖለቲከኞች እነማን ናቸዉ? (ሸንቁጥ አየለ)

የአማራን መጨፍጨፍ እንዳያስቆም ኦህዴድን ያባለጉት የአማራ ፖለቲከኞች እነማን ናቸዉ?
ሸንቁጥ አየለ

ከንባብ በፊት ማስታወሻ:-
                 የአማራ ፖለቲከኞች ሲባል የአማራ ሰዎችን/በነገዳቸዉ አማራ የሆኑ ፖለቲከኞችን/ ማለት እንጅ  አንዳንዶች እንደሚሉት  የአማራ 
 የፖለቲካ ፓርቲ ዉስጥ ወይም ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ዉስጥ ያሉትን  ማለት አይደለም::
==========================
—“በአማራ ብሄረተኝነት ምለዉ ተገዝተዉ ጉዟችን እስከ ቀራኒዮ ነዉ ብለዉ ሲያበቁ ተንደርድረዉ ወደ ጎጣቸዉ ከተወሸቁ ሰዎች ጋር ያልተነካካ ሰዉ ምስጉን  ነዉ::እኔን ግን ጉድ አደረጉኝ” አለኝ አንዱ ደዉሉ::
–አብራራዉ አልኩት::ሰዉዬዉ ሁሌም አቋሙ ወደ ነፈሰበት አይነት ስለሆነ ደግሞ ወደዬት ሊነፍስ ይሆን ብዬ በማሰብ ማድመጥን መርጫለሁ::ወደ ነፈሰበት የሚነፍሱ እና ብልጣብልጥ የፖለቲካ ስሌት የሚከተሉ ፖለቲከኞችን በሀሳብ አታሳምናቸዉም::ጉልበት ካለህ ከመሰላቸዉ ግን ፈጥነዉ ሰጋጅ ናቸዉ::
–ቀጠለ “ገንዘቤን እና ጊዜዬን ለአማራ ብሄረተኝነት ብዙ አጥፍቻለሁ:: ሆኖም ዛሬ ቤተሰቦቼ በምዕራብ ሸዋ ተፈናቀሉብኝ: ጭፍጨፋ ደረሰባቸዉ ብዬ ለአንዳንድ የአማራ ብሄረተኛ ጓደኞቼ ብነግራቸዉ “ዝም በል” አሉኝ:: “አሁን እሱን ለማንሳት ጊዜዉ አይደለም::ይልቅ አሁን ዝም በል::ማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚጮሁ አንዳንድ ሰዎች ነገር አታባብስ:: መንግስት ቀስ ብሎ በሂደት ጭፍጨፋዉን ያስቆመዋል” ብለዉ መለሱልኝ” ሲል አብራራልኝ::እየተናደደ መሆኑ ነዉ::ያዉ አቋሙን የሚለዋዉጥ ሰዉ ንዴት ስለሆነ ግን ብዙም ወደ ልቤም አልገባም::
–“እና ምን ደነቀህ?” አልኩት :: ጥያቄዬም የእዉነቴ ነዉ::
–እሱ እራሱ በብልጣብልጥ ፖለቲካ ስሌት አቋም አልባ ሆኖ ሲዳክር የኖረው ሰዉ ስለሆነ ይሄ ነገር ባልደነቀዉ ነበር:: በርካታ ቁጥር ያላቸዉ የአማራ ፖለቲከኞች (አንድነት ፓርቲም ዉስጥ ቢገቡ ወይም የአማራ ብሄረተኝነት ድርጅትም ዉስጥ ቢገቡ) አንድ ባህሪ ነዉ ያላቸዉ::እራሳቸዉን ችለዉ ከመቆም እና ለእዉነት ከመሟገት ይልቅ  የድርጅታቸዉን ፕሮፖጋንዳ ብቻ ነዉ የሚያደምጡት::
–አንድ ሰዉ ፖለቲካ ድርጅት ዉስጥ ሲገባ ሀሳብ ይዞ ድርጅቱ ዉስጥ ያለዉን አስተሳሰብ ለመቀዬር እና ለማስተካከል እንጂ እንደ ፖስታ አመላላሽ በቅሎ የነገር ጭነት እየተጫኑ ለመሮጥ ብቻ አይደለም:: ሆኖም  ላለፉት ብዙ አመታት ከሀገር ቤት እስከ ዉጭ ሀገር ያስተዋልኩት ነገር ብዙ ቁጥር ያለዉ የአማራ ፖለቲከኛ አንዴ ድርጅት ማምለክ ከጀመረ እግሩን ጅብ ቢበላዉ ልክ እንደ ሴትዮዋ “የኔን እግር ጅብ እየበላኝ ነዉ ዝም በል” ይልሃል እንጅ ለራሱ ህልዉና በራሱ ተጠይቅ አጣቅሶ አይቆምም::
-ለምሳሌ አሁን የአብን አባላት እና ደጋፊዎችን ተመልከቷቸዉ::አብንን ከመጠዬቅ እና ትክክለኛ አቅጣጫ እንዲይዝ ከመጎትጎት ይልቅ በብርድልብሳቸዉ ተጠቅልለዉ ተኝተዋል::ለምሳሌም ኢዜማ ዉስጥ ያሉ የአማራ ፖለቲከኞችን ተመልከቷቸዉ::የብርሃኑ ነጋን ንግግር እንደ ገደል ማሚቶ ከማስተጋበት የዘለለ አንዳች የተለዬ አቋም አይዙም::
–ብርሃኑ ነጋ የተባለ የፖለቲካ ነጋዴ በራሳቸዉ በአማራ መገናኛ ብዙሃን ቀርቦ ለአማራ ብሄረተኞች እና ለብአዴኖች እንዲሁም ለኢዜማዎች “አማራ በነገዱ ተለይቶ አልተገደለም” ሲላቸዉ የኢዜማ አባላት እና ደጋፊዎች ከዉጭ እስከ ሀገር ቤት “ትክክል ነዉ” እያሉ ሲዘሉ ነበር::በጣም ያስገረመኝ ታዲያ ወለጋ ያደጉ እና ቤተሰቦቻቸዉ በአማራነታቸዉ እየተጨፈጨፉ ያሉ የአማራ ፖለቲከኞች/አንቂዎች/ጋዜጠኞችም ብርሃኑ ነጋን ተከትለዉ መዝፈናቸዉ ነዉ::ለማመን ይከብዳል::ጭልፊቱ ብርሃኑ ነጋ አማራ በነገዱ ተለይቶ አልተጨፈጨፈም ባለበት ጊዜ ብቻ ከወለጋ እና ከቤኒሻንጉል ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ አማሮች እንደተፈናቀሉ እና እንደተጨፈጨፉ መረጃዎች ያሳዩ ነበር::
-በአንድነት ድርጅትም ሆነ በአማራ ብሄረተኛ ድርጅት ዉስጥ የሚመላለሰዉ የአማራ ፖለቲከኛ የመጀመሪያ ስራ የሚያደርገዉ የራሱን ሀሳብ ገሎ የድርጅቱን ፕሮፖጋንዳ ብቻ ለመሸከመ ብልታብልጥነት የተሞላበትን አካሂያድ መምረጥ ነዉ::
-ጭልፊት አሞራዉ የአብኑ ሊቀመንበር በለጠ ሞላ ደግሞ ይባስላችሁ ብሎ አማራ የሚባል ነገድ የለም ያለዉን አንዳርጋቸዉ ጽጌን “የትግል አራያዬ ነዉ” ብሎ ሲመጣ የአብን አመራሮች እና አባላት ዝም ጭጭ አሉ::አንዳንዶቹም እንዲያዉም በለጠ ሞላን ጀግናችን ነዉ እሰዬዉ አሉ::አብን በመሪዉ በኩል የአማራ ነገድ የለም ያለ ሰዉዬን የትግል አርማዉ ሲያደርግ ከአመራሩ እና ከአባላቱ ብሎም ከደጋፊዎቹ የተቃወመዉ ሶስት ጣት ደጋፊ ወይም አመራር ወይም አባል ይገኝ እንደሆነ እጅግ ብዙ ነዉ ብሎ ማሰብ ይቻላል::
— የአማራ ፖለቲከኞች ባህሪ እንዲህ ነዉ::እንመራዋለን ብለዉ ድርጅት የመሰረቱለት ነገድ የለም ሲባሉ ዝም ጭጭ ብቻ ሳይሆን ተስማምቶ እጃቸዉን ታጥበዉ መባላት::ኢዜማ ዉስጥ ያሉ የነፍጠኛ ልጆች የሚባሉት አማራዎች ከአማራ ክልል ዉጭ ያለዉ ወገናቸዉ በነገዱ ተለይቶ እየተቸፈጨፈ ሳለ የፖለቲካ ነጋዴዉ ብርሃኑ ነጋ “አማራ በነገዱ ተለይቶ አልተጨፈጨፈም” ሲላቸዉ በብልጣብልጥ አካሂያድ ጥግ ጥጋቸዉን ይዘዉ ዝም ጭጭ ነዉ:: እንዲያዉም አሁን ይሄን የኔን ጽሁፍ ቢያገኙት ሊመክሩኝ ሁሉ ይመጣሉ::አንዱ ጅማ ተወልዶ ያደገ አማራ ከዚህ በፊት አንድ ምክር ለግሶኝ ነበር::”እርግጥ ነዉ በጅማ አማሮች እየተለዩ ተገድለዋል::ቢሆንም ይሄን ነገር እንዲህ ፍጥጥ አድርገን መዘገቡ ብሄሮችን ያጋጫል” ሲል መክሮኝ ነበር::
— ፐ ! ወግ ነዉ እቴ ሲዳሩ ማልቀስ::ሲገደል አትግደሉኝ ለማለት የሚሽኮረመም ሰዉ ተነስቶ መጋጨቱ ለእንዲህ አይነት ሰዉ በምን ስሌት እንደታዬዉ አስቡት::
-ገና የዩኒቨርስቲ እያለሁ አዲስ አበባ አንድ የነገስታ እና የመሳፍንት ወገን ነኝ የሚል ዘመዴን አግኝቸዉ ነበር::ምናልባት ያኔ 21 አመቴ ቢሆን ነዉ::እናም ከዚህ ዘመዴ ጋር ስንነጋገር ሁሌም በአባቶቹ ታሪክ ኩሩ ነዉ::በአማራነቱም ኩሩ ነዉ::ሆኖም አንድ ቀን ፕሮፌሰር አስራትን መተቸት እና ማናናቅ ያዘ::”የወረደ ፖለቲካ ያራምዳል:: የጎሳ ድርጅት መስርቶ..” እያለ ይቀባጥራል::እናም አላስቻለኝም “አንተ የምትፎክርበት አማራነትህ ለጓዳ ብቻ ነዉ? አደባባይ አይወጣም?አደባባይ በአማራነቱ እየታረደ ያለ ህዝብ በአማራ ተደራጅቼ ሞቴን አስቆማለሁ ካለ ምኑ ነዉ ጥፋቱ? አንተ የአማራ ድርጅት አያዋጣም ካልክ ደግሞ የኢትዮጵያ ድርጅት መስርተህ ህዝቡን መታደግ እስካልቻልክ እራሱን ለመከላከል የሚሞክርን ወገን መተቸትህ ፍትሃዊ ነዉ?” ብዬ ብሞግተዉ “አንተ ልጅ ነህ::ገና ፖለቲካ አልገባህም” ሲል ዉይይታችንን አቄረጠዉ::ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እሱም ሊያገኘኝ ስለማይፈልግ እኔም ላገኘዉ ስለማልፈልግ ተገናኝተን አናዉቅም::በስልክ እንኳን አንጠያዬቅም::
አሁን የዲያስፖራ አማራም:በኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖረዉ አማራ ባህሪዉ እንደዚህ ዘመዴ አይነት ነዉ::አማራነቱን እጓዳዉ ይፎክርበታል::ሆኖም ሌሎች በአደባባይ አማራ ተብለዉ ሲጨፈጨፉ ነገሩ ወደ እሱ የሚመጣ ስለማይመስለዉ በጆሮ ዳባ ልበስ ማለፍ ብቻ ሳይሆን “አማራ ሊገደል አይገባም” የሚለዉን ሙግት ይሄ ዘረኝነት ነዉ ይልሃል::ቀጥ ያለ ወጥ መርህና ፍልስፍና ይዞ መከራከር እና ለዚያ እዉነት እስከ ዳር መቆም የለም::በብልጣብልጥነት መከረባበት ይበዛል::
–አማራ እራሱን ለማዳን የግድ በአማራነት መደራጀት አያስፈልገዉም::የታመነ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ቢኖር ኖሮ አማራዉንም መላዉ ኢትዮጵያንም ያድን ነበር::ግን የታመነ ድርጅት  የሚመሰረተዉ በሰዎች ነዉ::የአማራ ፖለቲከኞች ግን ገና ፓርቲ ፖለቲካ ዉስጥ ሲገቡ ብልጠት እና መከረባበት ይጀምራሉ::ስለዚህ ለሚጨፈጨዉ አማራ እናት እና አባታቸዉ የገቡበት ድርጅታቸዉ የተቃዉሞ መግለጫ እንዲያወጣ እንኳን አምርረዉ አይቀሰቅሱም::
-እናም ለዚህ ነዉ ይሄ ሰዉ የገጠመዉ ነገር ያልደነቀኝ:: እናም ሰዉዬዉ ቢናደድም ባይናደድም አልገረመኝም::ይሄ ሰዉዬ ከጥቂት አመታት በፊት አንድነት ፓርቲ ዉስጥ ይርመጠመጥ በነበረበት ጊዜ የቀለም ቀንድ የምትባል ጋዜጣ አቋቁመን ለግፉዓን ሁሉ(የአማራን ህዝብንም እንዲሁም አጠቃላይ የኢትዮጵያን ግፉዓን በማካተት)  ድምጽ ለመሆን ተነስተን ነበር: እናም ይሄ በዚያን ጊዜ አንድነት ፓርቲ ዉስጥ ይርመጠመጥ የነበር ሰዉ መገናኛ አካባቢ ለጋዜጣ አዟሪዎች “ይሄን የቀለም ቀንድ የተባለ ጋዜጣ ጋዜጣን አታዙሩት:: ምክንያቱም የተነሳበት አላማ አክራሪነት::ከዚህ ጋዜጣ ጀርባ መላዉ አማራ ህዝብ ድርጅት(መአህድ) እና መላዉ ኢትዮጵያ አንድነት(መኢአድ) የተባሉ ሁለት አክራሪ ድርጅቶች አሉበት”  እያለ ለጋዜጣ አዟሪዎቹ ሲናገር እጅ ከፈንጅ ይዥዋለሁ::ሰዉዬዉን አልተጣላሁትም ነበር::ግን በደንብ ናላዉ እስኪዞር በወቅቱ ነግሬዋለሁ::
–ከዚያ ደግሞ ይሄዉ ሰዉ የአማራ ብሄረተኛ ሆንኩ ብሎም ቅድስት ኢትዮጵያን እንደ ኦነግ እና እንደ ህዉሃት ብትጠፋም አያገባኝም እያለ ሲንዠባረር ነበር::ያኔ ይሄን ነገር እንዳይናገር ብመክረዉም ጆሮዉ ላይ ተኝቶበት ነበር::አሁን ደግሞ በአማራ ብሄረተኞች መናደድ ጀምሯል:: አሁን እንዲህ አይነት ሰዉ የሚያነሳዉ ነገር ምን ይደንቃል::እራሱ የሚያደርገዉን ነገር ዞሮ የማያስተዉል ሰዉ ሌሎች ይሄን አደረጉብኝ ቢል አይደንቅም::
-ሰዉዬው እያወራ ይሄን ሁሉ አንሰላሰዬ ዝም አልኩ::ከዚያም “ለመሆኑ አለህ?” አለኝ::”አዎን አለሁ::አሁን የነገርከኝ ግን አንተ ያደረግህዉን እና እያደረግህዉ ያለዉን ነገር ነዉ::ስለዚህ ቆመህ ማስተዋል አልቻልክም እንጂ ይሄን እያደረግህ ያለህዉ እራስህ ነህ ስለሆንህ ከቶም አልደነቀኝም” ብዬ ስልኬን ዘጋሁ::
-የአማራ ፖለቲከኞች ስል የአማራ ሰዎችን ማለቴ እንጅ አንዳንድ አስመሳዮች እንደሚሉት የአማራ የፖለቲካ ፓርቲ ዉስጥ ወይም ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ዉስጥ ያሉትን ማለቴ አይደለም::እናም ዛሬ ኦህዴድን ያባለጉት እነዚህ አስመሳይ እና ብልጥብልጥ የአማራ ፖለቲከኞች ናቸዉ::ምክንያቱም ብአዴን ዉስጥ የሚግማሙት የአማራ ፖለቲከኞች:አብን ዉስጥ የሚርመሰመሱት አስመሳዮች:ኢዜማ ዉስጥ የሚቀላምዱት የአማራ ፖለቲከኞች:እንዲሁም በተለያዬ ማህበራት:የሀይማኖት ተቋማት እና ስብስቦች ዉስጥ የተሰገሰጉት የአማራ ምሁራን እና ልሂቃን ኦህዴድ አማራን ከመታረድ እንዲታገድ አንድም ቀን ተቆጥተዉ አይናገሩትም::
–አማራ ለምን በዘሩ ተለይቶ ይታረዳል?ኦህዴድ ይሄን የግድ እንዴት አያስቆምም?:ኦህዴድ ካላስቆመስ ፌደራል እንዴት ገብቶ ማስቆም ይችላል? በማለት አኩርፈዉ አያዉቁም::ይባስ ብሎም የፖለቲካ ነጋዴዉ ብርሃኑ ነጋ “አማራ በነገዱ ተለይቶ አልተጨፈጨፈም” የሚለዉን አባባሉን የአማራ ብዙሃን መገናኛ በሚለዉ ሚዲያቸዉ ያስተላልፉለታል:: ኦህዴድም እነዚህ ብልጣብልጥ እና አስመሳይ የአማራ ፖለቲከኞችን ስነልቦና ስለሚያዉቅ “አሁን አማራ በኦሮሚያ ተጨፈጨፈ ካላችሁ ሀገር ይፈርሳል::ኦነግ ያኮርፋል::ሸኔ ይቆጣል:” እያለ እጁን በአማራ ደም ከኦነግ/ሸኔ ጋር እየታጠበ ያስፈራራቸዋል::
–እነዚህ ብልጣብልት እና አስመሳይ ፖለቲከኞች ኦህዴድ ከሚያኮርፋቸዉ የአማራ ነገድ ተጠንፍፎ ቢያልቅ ግድም አይሰጣቸዉም::ሁሌም ብልጣብልትነት እና አስመሳይነት አትራፊ አካሂያድ እንደመሰላቸዉ የአማራ ፖለቲከኞች ከ1967 እስካሁን ድረስ  ሰባ አመታት እየተልመጠመጡ አሉ::አንዴ አባቶቻቸዉን ሲክዱ:አንዴ ነገስታቶቻቸዉን ሲራገሙ:አንዴም ቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ሲራገሙ ቅዱስ ክርስቶስ ኢየሱስን ሲያዋርዱ:አንዴም የአማራን ህዝብ መጨፍጨፍ በተባባሪነት እንደ ኢህዲን/ብአዴን ተሰልፈዉ ሲከዉኑ አሁን ደግሞ አማራዉ ተጨፍጭፎ እስኪያልቅ ድረስ የአማራ ሞቱ ለመዘገብ ወቅቱ አይደለም ሲሉ እስካሁን አሉ::
–እንዲህ አይነቱን ፖለቲከኛ ብርሃኑ ነጋም:ኦህዴድም:ህውሃትም:ሻቢያም:ኦነግም ቢንቀዉ ምንም አይገርም::ሻቢያዎች ይሄን ሲተቹ አቋም አልባ የአማራ ፖለቲከኞች ይሏቸዋል::ኦህዴዳዉያን/ኦነጋዉያን ደግሞ ብልጣብልጥ የአማራ ፖለቲከኞች ይሏቸዋል::
-ይሄዉ አስመሳይነት እና ብልጣብልጥነት ግን በፖለቲከኞቹ እና በምሁራኑ ላይ የሚቆም አይሆንም::የግል ጋዜጣ መሰረትን የሚሉ በርካታ የአማራ ጋዜጠኞች የጋዜጣቸዉን ስም ኢትዮጵያም ቢሉት አማራም ቢሉት አንድ ወጥ ባህሪ ግን አላቸዉ::የአማራን ሞት ለመዘገብ ሁሌም ተሽኮርማሚ ብቻ ሳይሆን ፈጽሞ መነሳሳት የሌላቸዉ እና የወቅቱን ንፋስ አይተዉ የሚንቀሳቀሱ ናቸዉ::
አሁን ደግሞ የበለጡ ሞጭላፋ ዩቱበሮች መጥተዋል::ሳንቲም ለቅመዉ በዩቱዩብ ገቢ ለመኖር መጀመሪያ የሚያስተዉሉት የሁኔታዎቹን አዝማሚያ ነዉ::አማራ አማራ አማራ የሚባል ሁኔታ ያለ ሲመስላቸዉ የአማራ መዝሙር ፈልገዉ እንደ መጽሃፍ ቅዱስ አማራ አማራ አማራ እያሉ ይዘምራሉ::ልክ እንዳሁኑ የአማራ ሞቱ መዘገቡ እንኳን አዋጭ የማይሆን ከመሰላቸዉ ደግሞ ስለአማራ እልቂት አንዲት መስመር እንኳን አይዘግቡም::ዘገባቸዉ ገቢ ተኮር እንጂ እዉነት ተኮር አይደለም::
–እዉነት ሁሌም አንድ ሚዛን ብቻ አላት::ይሄዉም ለሰዉ ልጅ ሁሉ:ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ነገድ ወይም ለማንም ነገድ የማይገባዉ ተለይቶ  መጨፍጨፍ ለአማራ ነገድም ከቶም ሊደረግበት አይገባም::ይሄም ዘወትርም ዘላለምም ሊወገዝ ይገባዋል::በማንም በዬትም በማንኛዉም ወቅት ሊወገዝ የሚገባዉ ወንጀል ነዉ::
–ፖለቲከኛም:ጋዜጠኛም:ምሁርም:ካህንም:ሼክም: ሰዉ ሁሉ ከህጻን እስከ አዋቂ ሊኖረዉ የሚገባዉ አቋም ይሄዉ ነዉ::የአማራ አስመሳይ እና ብልጣብልጥ ፖለቲከኞች ግን የሚጨነቁት ጨፍጫፊዎቹ እንዳያኮርግፉ እንጂ ስለሚጨፈጨፈዉ ህዝብ አይደልም::በራሳቸዉ ነገድ ደም ላይ እየተረማመዱ ስለ ፖለቲካ ወዳጅነት ለመነጋገር ከቶም አይቀፋቸዉም::
—ሆኖም የአማራ ህዝብ ብልጣብልጥ እና አስመሳዮችን በብዛት እንደወለደ ያስተዋለዉ “የአማራ ህዝብ ከምድር ሳይጠፋ አማሮችን መጨፍጨፌን አላቆምም” ሲል የሚፎክረዉ የኦነጋዉያን/ሸኔ ሀይል ስለ አማራ ልሂቃን እና ምሁራን ግን አንድ እዉነተኛ ጽሁፍ ጽፈዋል::ይሄዉም “አማራ እማ ልጅም አልወለደም:” ሲል እዉነቱን አስቀምጦታል::
–በአማራ ብሄረተኞች ተበሳጨሁ ብሎ ለደወለልኝ ብልጣብልጥ እና አስመሳይ የአማራ ፖለቲከኛም ስልኬን እየዘጋሁ የነገርኩትም ይሄንኑ ነዉ::”አማራ እማ ልጅ አልወለደም::በብልጣብልጥነት እና በአስመሳይነት የሚመላለሱት የአማራ ፖለቲከኞች ሁሉም አልተወለዱም::”
Filed in: Amharic