>

ፋሺዝምን ያስናቀ ከናዚም የከፋ ፍጅት ግፍና ውድመት ያስከተለ ወረራ.....!!! (ኤርሚያስ ተስፋለም)

ፋሺዝምን ያስናቀ ከናዚም የከፋ ፍጅት ግፍና ውድመት ያስከተለ ወረራ…..!!!
ኤርሚያስ ተስፋለም

*…. የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር የተጠቀመው ለጠላት ያገለግላሉ ያላቸውን ንብረቶች የማውደም ተግባር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ውድመት በማስከተሉ የጄኔቫ ኮንቬንሽን አንቀጽ 54 ላይ የተከለከለ የጦርነት ስልት በሚል ተፈርጇል፡፡
አሸባሪው ሕወሓት ግን የናዚው ሂትለር የተጠቀመበተን ይህን አውዳሚ የጦር ስልት ይበልጥ አሻሽሎ ሰይጣናዊ ባህሪ በማላበስ በደደቢት በረሃ ለቀረፀው ማኒፌስቶ ማስፈጸሚያ አድርጎታል፡፡
አሸባሪው ሕወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን፣ ሙዚዬሞችን፣ መካነ ቅርሶችን እና የሐይማኖት ተቋማትን አውድሟል፡፡
እንደዚህ አይነት አውዳዊ ጦርነት ስልት እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1977 በወጣው የጄኔቫ ኮንቬንሽን አንቀጽ 54 ላይ የተከለከለ የጦርነት አካሄድ (ስልት) በሚል ተፈርጇል፡፡
የአሸባሪው ቡድን አባላት በሰሜን ሸዋ ዞን ዓለም በቃኝ ብለው ስጋቸውን የከዱ የ85 ዓመት መነኩሴን አስገድደው በመድፈር ናዚንም ይሁን አይኤስ አይኤስ የሽብር ቡድንን ያስናቀ ተግባር ፈፅመዋል፡፡
ወደ ሆስፒታል በመግባት ከበሽተኞች ላይ ኦክስጅን እና ጉሉኮስ በመንቀል በነብስ ውጪ ነብስ ግቢ ላይ ለነበሩ በሽተኞች እንኳን ቅንጣት ያክል ርህራሄ እንደሌላቸውም አሳይተውናል፡፡
ሽብርተኛው ሕወሓት በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች ከናዚም የከፋ ግፍ ፈጽሟል፡፡ የናዚው መሪ አዶልፍ ሂትለር በእብሪት እና ዘረኝነት ተነሳስቶ ከፋሽስት ጋር በመሆን መላውን አውሮፓ ለመውረር ጦር አዘመተ፡፡
የናዚ ጦር ወረራ ጅምሩ እጅግ የተሳካ ነበር፡፡ የጀርመን ጦር በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ የአውሮፓ ታላላቅ አገራትን መቆጣጠር ችሎ ነበር፡፡ ጦሩ ኖርዌን በሁለት ወር፣ ፖላንድን በአንድ ወር መቆጣጠር ሲችል ታላቋን ፈረንሳይ በስድስት ወር ውስጥ መሉ ለሙሉ በመቆጣጠር ወደ ምስራቅ አውሮፓ ግስጋሴውን ቀጥሎ የምስራቅ አውሮፓዎቹን ዩክሬን እና ቤላሩስን በመያዝ የመጨረሻ ግቡ ሞስኮ ሆነ፡፡
የናዚ ጀርመን ጦር ዋና ከተማዋን ሞስኮን አልሞ የሚያደርገውን ግስጋሴ ቀጥሎ ለሞስኮ መንደርደሪያ ይሆነው ዘንድ የኢንዱስትሪ ከተማዋን ስታሌንጋርድን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ 300 ሺሕ ሰራዊት አሰልፎ ወደፊት መግፋቱን ተያያዘው፡፡
ያኔ ሩሲያዊያን አባቶች አገራቸውን ከወራሪው ለማዳን ለመሞት ወስነው በፅናት በመቆም የናዚን ጦር በከበባ ውስጥ በማስገባት የመጀመሪያውን የሽንፈት ፅዋ አስጎነጩት፡፡
የስታሊንጋርድ ጦርነት የአሁኑን የዓለም ቅርፅ የቀየረ፣ አውሮፓን ከጀርመኑ ናዚ ወረራ የታደገ የሁለተኛው የዓለም ጦርነት አሸናፊነትን የወሰነ የጦር ግንባር ነው፡፡
የአውሮፓን ግማሽ በቁጥጥሩ ስር አውሎ የነበረው የናዚ ጦር በሩሲያ ቀዩ ጦር የደረሰበትን ሽንፈት ተከትሎ ወደ ኋላ ለማፈግፈግ ተገደደ፡፡ ማፈግፈጉም ከሞስኮ አፍንጫ ስር እስከ በርሊን የዘለቀ ነበር፡፡
የናዚው ጦር በዚህ ማፈግፈግ ውስጥ አንድ አውዳሚ የሆነ የጦር ስልትን ተከተለ፡፡ ይህ ስልት ጠላት ሊጠቀምበት ይችላል ተብሎ የታመነበትን ሁሉንም ሀብት ማውደም “scorch earth policy” ሲሆን በዚህ አካሄድ ጠላት ሊጠቀምበት የሚችለውን ምግብ፣ መገናኛ እና ስነ-ተግባቦት መዋቅሮች፣ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች እንዲሁም ኢንዱስትሪዎችን ማውደም ሲሆን ከፍ ሲልም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ለአቅመ ውትድርና የደረሱ ወጣቶችንም መጨፍጨፍ ይጨምራል፡፡
በዚህ አውዳሚ በሆነ የጦር እስትራቴጂ ዓለም አይታም ሰምታም የማታውቀውን ውድመት አስተናገደች፡፡ የናዚ ጦር ከሩሲያ ተነስቶ ወደ ዩክሬን ባደረገው ማፈግፈግ ብቻ 28 ሺሕ መንደሮች እና ከተሞችን አውድሟል፡፡
የጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር የተጠቀመው ለጠላት ያገለግላሉ ያላቸውን ንብረቶች የማውደም ተግባር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከፍተኛ ውድመት በማስከተሉ እንዲህ አይነት ውድመት በዓለም ላይ ዳግም እንዳይደገም እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1977 በወጣው የጄኔቫ ኮንቬንሽን አንቀጽ 54 ላይ የተከለከለ የጦርነት ስልት በሚል ተፈርጇል፡፡
አሸባሪው ሕወሓት ግን የናዚው ሂትለር የተጠቀመበተን ይህን አውዳሚ የጦር ስልት ይበልጥ አሻሽሎ ሰይጣናዊ ባህሪ በማላበስ በደደቢት በረሃ ለቀረፀው ማኒፌስቶ ማስፈጸሚያ አድርጎታል፡፡
አሸባሪው በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች አንድም የጤና ተቋም አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎ በማውደም እና በመዝረፍ ነብሰ ጡር እናቶች በየመንገዱ እና በየጫካው በህክምና እጦት ለሞት ዳርጓቸዋል፡፡
ከወለዱ ጥቂት ቀናት የሆናቸው ደማቸው ያልደረቀ አራሶችን በመድፈር የጭካኔ ጥግን አሳይቷል፡፡ እናትን በልጅ ፊት፤ ሚስትን በባል ፊት በቡድን በመድፈር ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ፈጽሟል፡፡ እራሳችንን አናረክስም ብለው በወሮበላው ቡድን ላለመደፈር የተከላከሉ ሴቶች በጭካኔ የጥይት አረር አርከፍክፎባቸዋል፡፡
በጤናው ዘርፍ ላይ እንደዚህ አይነት የከፋ በደል እና ውድመት ሲከሰት የዓለም የጤና ድርጅትን የሚመሩት የሕወሓት ሰው ቴድሮስ አደሃኖም ጉዳዩን ባላየ በማለፍ የሽብር ቡድኑ የቁርጥ ጊዜ ሰው መሆናቸውን ዳግም አስመስክረዋል፡፡
የሕወሓት ኅልውና የተመሰረተው ጠላት በመፍጠር ላይ ነው፡፡ ጠላት ከሌለ የሕወሓት ኅልውና አይቀጥልም፡፡ ሕወሓት የተወለደው በበታችነት ስሜት ነው፡፡ ዋናዎቹ የሕወሓት ሰዎች አባቶቻቸው ኢትዮጵያን የካዱና የወጉ ባንዳዎች ናቸው፡፡
ለዚህ ደግሞ አቦይ ስብሓት ህያው ምስክር ናቸው፡፡ የድርጅቱ ቁመና በብርቱ ሲፈተሽ ደግም በአንድ ቤተሰብ የተደራጀ የስብሓት ነጋ እና ቅዱሳን ነጋ ሰረው-መንግስት መሆኑ እሙን ነው፡፡
እነ ስብሓት ከገጠማቸው የበታችነት ስሜት ለመውጣት በ1968 ዓ.ም ኢትዮጵያን እስከማፍረስ የደረሰ ፕሮጀክት ነደፉ፡፡ አሁን ኢትዮጵያን እየፈተናት ያለው ይኸው ቅርሻት ነው፡፡
Filed in: Amharic