የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የምርመራ መዝገብ ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተዛወረ … !!!!
ተራራ ሚድያ
ፖሊስ ከ14 ቀን በፊት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁን ተከትሎ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ፍርድ ቤት ቢቀርብም መርማሪ ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ አያስፈልገኝም የምርመራ መዝገቡም ይዘጋ ሲል ፍርድ ቤቱን በመጠየቁ የገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መዝገቡን ዘግቶ ጉዳዩም ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲተላለፍ ወስኗል።
በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የገለን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ከ14 ቀን በፊት ጋዜጠኛ ታምራትን ለዛሬ ታህሳስ 21/2014 ዓ.ም መቅጠሩ የሚታወስ ነው።
በዚህም በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የምርመራ መዝገብ ተዘግቶ ከዚህ በኋላ ጉዳዩን የሚከታተለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሆኑም ታውቋል።
የጋዜጠኛው ጠበቃ የደንበኛቸው የዋስ መብት እንዲጠበቅ ጠይቀው ፍርድ ቤቱም የተጠየቀውን የዋስ መብት ፋይል መክፈት እንዲችል ፈቅዶ የምርመራ መዝገቡን ዘግቷል።
የተራራ ኔትዎርክ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከአዲስአበባ ፖሊስ ተላልፎ በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከታህሳስ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ይታወሳል ።
ጋዜጠኛው ከቤቱ ከተወሰደ የመጀመሪያዎቹ 7 ቀናት የት እንዳለ ሳይታወቅ ቆይቶ ከ7ቀን በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡ አይዘነጋም ።
ታህሳስ 01/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ገደማ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ እንደተወሰደ ቤተቦቹ መናገራቸዎን መዘገባችን የሚታወስ ነው።
ይሁን እንጅ ጋዜጠኛ ታምራት መጀመሪያ ወደ ሶስተኛ ፖሊስ ቢወሰድም ከፌደራል ፖሊስ ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ እንደተዛወረም ታውቋል።
ፖሊስ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ አያስፈልገኝም ጉዳዩ ወደ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይዘዋወር በማለቱ የጋዜጠኛ ታምራት ነገራ የምርመራ መዝገብ ተዘግቷል።