>

ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ያለው እስረኛ ጉዳይ (ሱሌማን አብደላ)

ሳኡዲ አረቢያ ውስጥ ያለው እስረኛ ጉዳይ

ሱሌማን አብደላ

እነዚህን እስረኞች ወደ አገር መመስለ የአገርንም የዜጋንም ክብር መጠበቅ ነው። ዜጋና ዜግነት ረከሶ እንዲህ ተዋርዶ ማየት ለኢትዮጵያም ይሁን አገሪቱን ለሚመራው መንግስት ትልቅ ውርደት ነው።
የነዚህን የዜጎች ጉዳይ መንግስት መፍትሔ ይሰጥበታል ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን ድረስ መፍትሔ የለለው ጉዳይ ሆኗል። ሳኡዲ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥፋት የለባትም። ህገወጥ ሆኖ የአገሬን ህግ ጥሶ ነው ያገኘሁት ያለችውን ዜጋ ይዛ በህግ ጥላ ስር የማድረግ መብት አላት። አንዲት አገር ህጓን ጦሶ ያገኘችውን የውጭ ዜጋ ይዛ ከአገሯ የማስጣት መብትም አላት። አገሪቱ በዚህ ዙሪያ አትታማም። በአመት ከመቶሺ በላይ ህገወጥ ሰዎችን በራሷ ወጭ ወደኢትዮጵያ የምትመልስ ብቸኛዋ አገር ሳኡዲ አረቢያ ናት። አሁን ላይ ካኡዲ ተማራለች። 10ሺ ወደኢትዮጵያ ብትልክ 10ሺ በየመን በኩል ገብተው ያድራሉ። ነገሮች እስከዚህ ድረስ የተወሳሰቡ ናቸው። ለምጭውም ለወሳጁም ያደናገረ ነገር ነው።
ከዚህ አንፃር መንግስት ዝምታን መርጧል በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የሚሰሩ ስራዎች ካሉ መሞከር ነው። ከለሉም መንግስት ዜጎቹን የመቀበል ግዴታ አለበት። አሁን ላይ እስረኞቹ እጅግ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ከእስርቤት የሚወጡ እዚህ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምናያቸው ምስሎች ይመሰክራሉ።
የኢትዮጵያ ዜጋ እንዲህ ተዋርዶና ረክሶ ማየት መንግስት ለዜጎቹ ያለውን እይታ በውጭ አለም ሲታይ የሚያሶቅሰው ነገር ነው። ሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ እስረኞች፣ ትናንት ስራ ላይ በነበሩት ወቅት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆነው ቆይተዋል። ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከሌሎች የአለም አገራት ወደኢትዮጵያ የሚሄደን የብር መጠን ማወቅ ከፈለጋችሁ ሜዲልኢስት ቢዚነስ ግሩፕ በያመቱ የሚያወጣውን ጥናት ማየት ብቻ በቂ ነው።
ይሄንን እውነት የምታውቀው ግብፅ ናት። ግብፅ ይሄንን ነገር ስትሰማ እስከፓርላማ አባል ድረስ፣ ያጨቃጨቀ እውነታ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ይሄንን ነገር አላየውም።
ይሄንን ጥቅም የሚሰጥ ዜጋ  ዛሬ ላይ  ተጠያቂ መንግስት የለለው መሄጃ አገር የለለው እስኪመስል ድረስ እንዲህ እየተሰቃዩ ነው። አሁንም ቢሆን መፍትሔ ይፈለግላቸው። የነሱ እንደዚህ መሆን የዜጋና የዜግነት ጉዳይ መንግሥት ለዜጎቹ የሚሰጠውን ክብር ጥያቄ ውስጥ የሚያስገበው ጉዳይ ነው።
Filed in: Amharic