>

"ዝና ፈላጊው ጠቅላይ ምኒስትርና የአማራና አፋር እጣ-ፈንታ....!!!" ቀለም ስዩም (የህሊና እስረኛ) ቃሊቲ

“ዝና ፈላጊው ጠቅላይ ምኒስትርና የአማራና አፋር እጣ-ፈንታ….!!!”

ቀለም ስዩም (የህሊና እስረኛ) ቃሊቲ፣ አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ እየተወጋች ያለው በብዙ መልኩ ይመሰላል፡፡ ለብዙ አመታት የተከማቹ፣ በየወቅቱና በየጊዜው መፈታት ያለባቸው ነገር ግን በችሎታ ማነስ፣ በንቀትና አክራሪነት፣ በዝምታና ማድበስበስ የታለፈ ፖለቲካዊ፣  ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ ተግዳሮቶች ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫና በሁለንተናዊ መልኩ ክፉኛ እንድትወጋ አድርጓታል፡፡
በሌላም በኩል በወቅታዊና አለምአቀፋዊ ሁኔታዎች ከሌሎች ነባርና አዳዲስ ችግርች ጋር ተዳምረው አገሪቱንና ህዝቧን ከአጣብቂኝ ውስጥ ከቷቸዋል፡፡ የእነዚህ አጠቃላይ ችግሮች መነሻቸው ህወሓት፣ ኦነግ- ሸኔ፣ የመንግሥትና የግብፅ ተፈጥሮአዊ ባህርይ መሆኑን ለመረዳት ብዙም አንቸገርም፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች በብዙ ነገር ይመሳሰላሉ፡፡ ሁሉም ፀረ- ኢትዮጵያ፣ ፀረ-አንድት፣ ፀረ-አማራጭ፣ ፀረ-ኦርቶዶክስ አቋም ያራምዳሉ፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ሁሉም በአማራ ህዝብ ላይ ጥላቻም-ጠላትነትም አላቸው፡፡
1.  “የአሣ ግማቱ -ከአናቱ
የአገርም ሆነ የቡድን ችግሮች ሁሌም መነሻቸው ከአናታቸው ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡ የብዙሀኑ ቁጥር ያለው ከታች ሲሆን ከላይ  ያሉት ደግሞ ጥቂቶች ናቸው፤ እንደዚያ ይባል እንጂ ጥቂቶቹም የሚዘወሩት ከአናቱ ባለው አንድ ሰው ነው ሊባል ይችላል፤ ይህ ሰው በሌላ አነጋርገር መሪው ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ኢትዮጵያዊ የሀገር ፍቅር ስሜት ያላቸው (Natioinalist) መሪ እንደሆኑ አድርገው ይቆጥራሉ፡፡ በሌላም በኩል የመንግሥት መገናኛ ብዙሃንም ይህንኑ የተሣሣተ ድምዳሜ ይዘው ሲያራግቡ እንታዘባለን፡፡ እነርሱም ምናልባትም የመንግሥት ተቀጣሪ በመሆናቸው ይመስላል ሁሌም የጋዜጠኝነት ሳይሆን የካድሬነት ሚና ነው ያላቸው፡፡ እጅግ በጣም መሠሪና ጎጠኛ ለነበረው ጠቅላይ ምኒስትሪ መለስ ዜናዊም እንዲሁ አቋም ይዘው ሲያሸሞነሙኑ የኖሩ ናቸው፤ እናም ዛሬም ከጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አብይ ጎን ሆነው ሰውየውን ያለስራቸው ሲያጀግኑና ክንፍ የለለው መልአክ አድርገው ሲያቀርቧቸው ይስተዋላሉ፡፡
 ሰውየው ወደ ተግባራዊነት በማይለወጡና ነባራዊውን ሁኔታ ባላገናዘቡ ባዶ ቃላት የበለፀጉ ናቸው፡፡ ጠለቅ ብለን ሰውየውን በንግግሮቻቸው ውስጥ ብናፈላልጋቸው ደግሞ ብዙ የሚያነጋግሩ ነገሮ ይኖራሉ፡፡
ጠቅላይ ምኒስትሩ አለማችን በተካነችበት አባዜ ማለትም “PRS” (Problem, Reaction, Solution) በተባለው የፖለቲካ ሴራ የሚመሩ ይመስላሉ፡፡ በ “PRS” አገዛዝ መርህ፡- ህዝብ በተረጋጋና ሠላማዊ ህይወት እንዲኖው አይፈልጉም፡፡ ወይም ደግሞ በችግር ላይ ችግሮችን እየፈጠሩ በመደራረብ የህዝብን ፋታና ትኩረት (Attention) ማሳጣት ሊባልም ይችላል፡፡ ይህ የሚደረገው ሕዝቡ ጨርሶ በማይጠረጥረው መልኩ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- መንግሥት ራሱ የተለያዩ ችግሮች በሕዝቡ ላይ እንዲደርስ ያደርጋል፤ የችግሩ ምንጭ መንግሥት መሆኑ እንዳይጠረጠርም ራሱ የችግሩ ተቃዋሚ ሆኖ ይቀርባል፤ ሂደቱ በእዚህ አያበቃም… ችግሩን የፈጠረውን የተቃወመው መንግሥት ተመልሶ መፍትሔ አምጪ ለመሆን ይሞክራል፡፡ የአለማችን መንግስታት የሚያካሂደት የፖለቲካ ሴራ ጨዋታው እንዲህ ነው፡፡
ይህንን የፖለቲካ ሴራ መርህ ገዢው ፓርቲ (ኦህዴድ) ወይም ደግሞ የጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አብይ ካቢኔ ሰለመፈፀሙ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን አውዳሚ ጦርነት በአግባቡ መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡
ካለፉት ተሞክሮዎች ስንነሣ እንዲህ ነው ብሎ በእርግጠኝነት ማስቀመጥ በሚያስቸግር መልኩ በፖለቲካ አንቃኞችም ሆነ በራሱ በመንግስት በኩል ጥርስ የተነከሰበት ህዝብ ቢኖር አማራ ብቸኛው ተጠቃስ ይሆናል፡፡ ይህን ሁሉ መከራ፣ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ በደልና ግፍ በአማራ ህዝብ ላይ መድረሱ ሳይንስ የሕወሓትም ሆነ የኦህዴድ መንግሥታት በሩቁ የሚጠራጠሩትና የሚፈሩት ህዝብ ራሱ አማራ መሆኑ ደግሞ ነገሩን አሥገራሚ ያደርገዋል፡፡
የሕወሓትም ሆነ የኦህዴድ ብልፅግና መንግሥታት አንድ ቀን ጦር ሰብቀው ሊነሱበት እንደሚችሉም አማራ ቀድም ገብቶታል፡፡ እናም ጄኔራል አሣምነውን የመሳሳሉ የአማራ ልጆች፣ በአማራ ህዝብ ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለመከላከልም ሆነ ሊደርስ የሚችለውን ጥቃት መቀነስ እንዲቻል አንዳንድ ዝግጅቶችን ማድረግ ጀመሩ፡፡ እነዚህ የህዝብ ልጆች እያንዳንዱ የክልል መንግስታት እያደረጉ ያሉትን  የልዩ ሀይል ግንባታ እነርሱም ማድጋቸው እንደ የመንግሥት ግልበጣ ወንጀል ተቆጥሮ ገሚሶቹ ተገደሉ፣ ገሚሶቹም እንዲታሠሩ ተደረገ፡፡ ልዩ ሀይሉም ተበተነ፡፡ የአማራ ህዝብም ባዶ እጁን ሆኖ ለጥቃት ተጋልጦ እንዲቀመጥ ተደረገ፡፡ ለመደራጀት ሲሞክርም ብርድ ብርድ ይላቸዋል። የተደራጁም ሲኖሩ በተለመደው ሴራቸው መበተንና መከፋፈል ይጀምራሉ…..። ለእዚህ ደግሞ ዶክተር አብይ አህመድ እና ፓርቲያቸው የኦህዴድ ብልፅግና የታሪክ ተወቃሾች ናቸው፡፡ የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር አንድ ቀን የሕግ ተጠያቂ የማይሆኑበትም ምክንያት አይኖርም፡፡ የሆነው ሆኖ የአማራ ህዝብ ሠላምና ደህንነት የማግኘት አለም አቀፍ መብቱን (The right to peace and security) እንዲያጣ ተደረጎአል፡፡
“የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል” እህንዲል የአገሬ ህዝብ እብሪተኛው ህወሓት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ፡፡ በጥቂት ወራት ውስጥ፣ በልዩ ሀይል፣ በሚሊሻና በፋኖነት የተሰባሰበው የአማራ ህዝብ ከፌዴራሉ የመከላከያ ሀይል ጋር ተቀናጅቶ በወሰደው የመከላከልና መልሶ የማጥቃ እርምጃ ሕወሓት ከመቀሌው ቤተመንግስቱ ወርዶ ወደ ተንቤን በረሀ ተሰደደ፡፡ ወደ በረሀ የተሰደዱት የሕወሓት አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸውና የተወሰኑ የታጠቁ ጠባቂዎቻቸው ብቻ ነበሩ፡፡ በመቶ ሺዎቹ የሚቆጠሩትን ሠራዊታቸውን ግን ትጥቃቸውን እንደያዙ ወደየቤታቸው እንዲሄዱ ነበር የተደረጉት፡፡ ወይም ደግሞ በሌላ አገላለጽ በድርጅታዊ አሠራር ዳግመኛ ጥሪ እስከሚደረግላቸው ድረስ ሰራዊቱ በህዝቡ ውስጥ እንዲበታተኑ ተደረገ፡፡
በወቅቱ የመንግሥት ወታደሮችና የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት ሆኖ የተቋቋመው ሀይል ቀዬ ለቀዬና ቤት ለቤት ጥብቅ ፍተሻ እያደረጉ የሕወሓትን ወንጀለኞችን አድነው መያዝ ይችሉ ነበር፡፡ አልሆነም። ይሁን እንጂ ጦርነቱ እንዲያልቅ ስላልተፈለገ ይህን እርምጃ ላለመውሰድ ጠቅላይ ምንስትሩ አቅማሙ፡፡ ከዚያም በፊት መቀሌን ከበው የያዘው የፌደራል መንግሥቱ የጦር ሀይል የሕወሓት የወንበዴ ቡድን ከመቀበሌ እንዳይወጣ ማድረግ ይችል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በመቀሌና በአካባቢው ውጊያ ላለማድረግ ሲባል ወይም ደግሞ ምናልባትም ለመቀሌ ግዑዝ ህንፃዎች ደህንነት በማሰብ፣ አሊያም ጦርነቱ እንዳያልቅ በመፈለግ ሊሆን ይችላል፡፡ የሕወሓት ጦር መንገድ ተከፍቶለት ወደ ተንቤን በረሀ ያለምንም ችግር ሰተት ብለው እንዲሄዱ ተመቻቸላቸው፡፡ ይህን እውነት ደግሞ ጠቅላይ ምኒስትሩም ሆኑ የጦር ሀይሎች  ኤታማዦሩ እንደ ታላቅ ጀብዱ በየመገናኛ ብዙሀኑ ሲያወሩ የታዘብነው ጉዳይ ነበር፡፡
“ከፊተኛው ጥፋት የኋለኛውን ይብሣል” እንዲል ታላቁ መጽሐፍ፡- የትግራይ ህዝብ ከኋላችን ወግቶናል፤ አሊያም በተደጋጋሚ እንደተባለው የትግራይ ገበሬ እርሻውን እንዲያርስና የፋታ ወይም የጥሞና ጊዜ መሰጠት …. በሚሉ ተልካሻና ያረባባ ምክንያቶች ጦሩ ትግራይን ለቅቆ እንዲወጠ ተደረገ፡፡ ያኔ ነበር የሕወሓት አመራሮች ጦርነቱን በአማራ ክልልና ህዝብ ላይ እንደሚያካሂዱና ሂሳብ እንደሚያወራርዱ እቅድ መንደፋቸውን በአደባባይ የተናገሩት፡፡ ከእዚህ በኋላ የነበሩው ሁኔታ ዶክተር ደብረፅዮንና ዶክተር አብይ እየተማከሩ ያደረጉት ጦርነት ነው የሚመስለው፡፡
በመጀመሪያው ዘመቻ እያንዳንዱ ጀኔራል በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ “ሕወሓት ዳግመኛ የኢትዮጵያን መንግሥትን መፈተንና በማይችልበት ደረጃ ተመትቷል፣ ካሥፈለገ ዛሬውኑ ተመልሰን መቀሌ መግባት እንችላለን….” እያለ መደንፋቱን ተያያዘው፡፡ ይሁን እንጂ ሕወሓት ዳግመኛ አንሰራርቶና ህዝባዊ ማእበል ፈጥሮ “ጦርነቱ” በአማራ ክልል ውስጥ እናደርገዋለን …” ብሎ እንደዛተው እቅዱን ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፡፡ የሕወሓት የሕዝብ ማእበል ከሰቆጣ ተነሥቶ በላሊበላ አድርጎ ኮምቦልቻና ሰሜን ሸዋ ድረስ አጣዬንና ሸዋሮቢትን ተቆጣጠረ፡፡ በዙ ዘግናኝ ግፍም ፈፀመ። ይህ ሁሉ ሲሆን መከላከያ ሠራዊቱ በማይገባን ምክንያት በሚሰጠው ትእዛዝ መሠረት ወደ ኋዋላ ያፈገፍግ ነበር፡፡ ግን ለምን?….
እንደሚታወቀው የፌዴራሉ መከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል ህዝባዊ ታጣቂዎች ባካሄዱት የመጀመሪያው ዘመቻ ላይ መላውን ትግራ ለመቆጣጠር የፈጀው ጊዜ ሶስት ሣምንታት (21 ቀናት) ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ የአፋር አራት ወረዳዎችንና የወሎን ዞን፣ እንዲሁም እስከ ሸዋ ሮቢት የተቆጣጠረውን የትግራይ ህዝባዊ ማእበል ጦር ለመደምሰስ የፈጀው ጊዜ ከአሥራ አምስት ቀና ያልበጠለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ይህ አጠቃላይ ሁኔታ አንድ ጥያቄ ያጭርብናል፡፡ የትግራይ አማፂ ጦር የአፋርና የአማራን ክፍል ሰፊ ይዞታ ለመቆጣጠር ወታደራዊ አቅሙ ነበው ወይ? ብለን ስንጠይቅ መልሱ “የለውም” የሚለው ይሆናል፤ እንዲያውም ለንፅፅር የሚቀርብ አይደለም፡፡ እናስ ታድያ ከ500 ኪሎ ሜትሮች በላይ ተጉዞ እስከ ሰሜን ሸዋ እስከሚደርስ ለምን ተጠበቀ!? የገበሬዎችን ሞፈርና ቀንበር፣ የትምህርት ቤቶችን ወንበርና ጠረጴዛ እያነደደ ሲሞቅና ለምግብ ማዘጋጃ ማገዶነት ሲጠቀም ለምን በዝምታ ታየ!? ብለን ስንጠይቅ እንቆቅልሹ በቀላሉ የሚፈታ አይደለም፡፡ በአጭር አገላለጽ የአማራ ሕዝብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ክስረት እንዲደርሰበት፣ የሞራልና የሥነ ልቦና ውድቀት እንዲፈጠርበት፣ ሚስቱና የደረሱ ሴት ልጆቹ በፊቱ ላይ በመደፈራቸው ዳግመኛ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዳይሄድ በከፍተኛ ጥናትና ቅንብር የተደገፈ ፖለቲካዊ ሴራ ተፈጽሞበታል፡፡
አሁንም ቢሆን ሕወሓት የአማራ ሕዝብ ሥጋት እንዲሆነ እንዲቀጥል የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀይላት ስወር እገዛ የተደረገለት ይመስላል፡፡ ምክንያቱም “ሕወሓትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዳይነሳና እንዳያንሰራራ አድርገን እንደመስሰዋለን!….” የሚለው የኢትዮጵያ መንግሥት ፉከራ-ከባዶ ፉከራነት የዘለለ አልሆነም፡፡ ሕወሓትን ያለበት ቦታ ድረስ ሄዶ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ የተፈለገ አይመስልም፡፡ ሕወሓት ደግሞ ሙሉ በሙሉ ካልተወገደ በስተቀር ጊዜና አጋጣሚውን ጠብቆ ጥቃት መሰንዘሩ የማይቀር ይሆናል፡፡ አሁንም በጎንደርና በአፋር ኮሪደሮች በኩል እየሆነ ያለው ይሄው ነው፡፡ የሕወኀት አደገኛ ቡድን አውዳሚ የሆነውን ጦርነትን አማራጭ እንደ የመኖር ህልውና (existence) ወይም እንደ ቢዝነስ አድርጎ ያየው ይመስላል።
አንዳንድ ቅን አመለካከት ያልነጠፈባቸው ወገኖች የሕወሓትን ጦር ከወሎና ከአፋር ለማውጣት የተቻለው ጠቅላይ ሚነስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ግንባር በመዝመታቸው ነው ይላሉ፡፡ ይህ ድምዳሜ ለእኔ ብዙም አሳመኝ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፊትም የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ናቸው፡፡  አዛዡም ፣ አስተባባሪውም፣ የጦር እቅድ ነዳፊውም ፈቃም እርሳቸው ነበሩ፡፡ ጦሩን ግንባር ድረስ ሄደውም ሆነ በአዲስ አበባ ተቀምጠው እንዳሻቸው የሚዘውሩት እርሰቸውና እርሳቸው ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ በመሪነት ሳይንስ ሲታይ ግንባር ድረስ መሄዳቸውም ሆነ አለመሄቸው ከጉንጫልፋነት በቀር ሌላ መፍትሔ  የለውም፡፡ ወይም ደግሞ የቴዎድሮስንና የዳግማዊ ምኒልክን የጦር ውሎና የጀግንነት ታሪክ ለመሻማት የተደረገ ነው ሊባል ይችላል፡፡ የታሪክ ሽሚያው ካለፉት ንጉሠ- ነገሥታት ጋር ብቻ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ሚነስትሩ የአፋርና የአማራን ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖን ታላቅ የጀግንነት ተጋድሎ፣ እንደዚሁም የመከላከያ የጦር ጀነራሎቻቸውን የአመራር ብቃትና የአሸናፊነት ጥበታቸውን ጭምር መና እንዳስቀሩት ነው የሚሰማኝ፡፡ የጠቅላይ ሚነስትሩን ፊት እየተመለከተ የሚጀግን ጦር ከሆነ ያለን መከላከያና የፍትህ አካላቱነ ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከተው  ነው የሚሆነው፡፡
2.  የአለም አቀፉ ማህበረሰብና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አቋም 
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጦርነቱ በአማራና በትግራይ በአፋርና በትግራይ ወሰን ላይ እንዲቆም የፈለጉበት መሰረታዊ ምክንያቱ ምንድነው? የትግራይ ህዝብን በህይወት የመኖር መብት ስለሚያከብሩ፣ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ተጽእኖ ስለሚፈሩ?፣ ለአማራና ለአፋር ሕዝብ ደንታ ቢስ በመሆናቸው? ወይም የመጡበት የኦሮሚያ ክልል ከሌሎ ክልሎች ገዝፎና ጉልቶ  በሁሉም አቅጣጫ ሁሉንም በረጅም እርቀት እንዲመራ በመፈለጋቸው ይሆን!? የሚሉትን ጥያቄዎች በገረገር እይታ ስንመለከተው መልሱ “ሁሉም” የሚለው ሊሆን ይችላለ፡፡ ይሁን እንጂ ለርእሱ ጉዳዩ አፅንአት ሰጥተን በማስተዋል ብንመረምረው ዋነኛ ምክንያቶቹ የጠቃቀስናቸው ላይሆኑ ይችላሉ፡፡
ዶክተር አብይ አህመድ ማንም ሰው ሊገምተው ከሚችለው በላይ “ስልጣን” ይወዳሉ፤ ይህ ሥልጣንን የሙጢኝ ብሎ የመፈለግ አዝማሚያ ደግሞ “ዝነኝነትን” አጥብቆ ከመሻት ይመነጫል፡፡ በሁሉም አቅጣጫና በሁሉም ርእሱ ጉዳይ ላይ የመነጋገሪያ ማእከል የመሆን ቀቢፀ-ፍላጎት አላቸው፡፡ እውቅ ደራሲ፤ እውቅ የጦር ጀኔራል፤ እውቅ የፊልም አክተር፣  የአንጓዴ ልማት ቁጥር አንድ ጀግና፣ ቁጥር አንድ ፈላስፋና ፖለቲከኛ … መባልን ይሻሉ፡፡ በሁሉም ነገር ሁሉንም ማስተማር ይዳዳቸዋል፡፡ በቃ! በሁሉም ነገር እርሳቸው የሚሉት ብቻ ትክክለኛ እንደሆነ አድርገው ራሳቸውን አሳምነዋል፡፡ በአጠቃላይም በእነዚህ ሁሉ ዝነኛ ሆኖ ለመገኘት ብቸኛው ምርጫ የታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሆኑ መቀጠል ከቻሉ ብቻ ይሆናል፡፡
ሰውየው በያዙት የጠቅላይ ምኒስትርነት ሥልጣን ለመቀጠል ያስችለኛል የሚሉትን ነገር ሁሉ አያደርጉም አይባልም፡፡ እስኪ የተወነሱትን በወፍ-በረር እንቃኛቸው፡፡
ሀ) በመንግሥታዊ ካቢኔያቸው፣ በተለይም በፖሊስና በመከላከያ፣ በሕዝብ ደህንነትና አስተዳደር በመሳሰሉ ወሳኝ አካባቢዎ የኦህዴድ ብልጽግና አባላትን በአብዛኛው የመመደብ አዝማሚያ ይታያል፡፡
ለ) የኢትዮጵያውያንን ሙሉ ድጋፍ ለማግኘትም ስለ ኢትዮጵያ ሉአላዊ አንድነት አብዝቶ ማውራትን ያውቁበታል፤
ሐ)  ያለ አማራና አፋር ህዝብ ንቁ ተሳትፎ ኢትዮጵያን ማስቀጠል ስለማይቻልና መዘዘም ብዙ ስለሚሆን የሕወሓት ወራሪ ሀይል ከአፋርና ከአማራ ክልል ማስወጣት አስፈልጓል፡፡
መ)  የትግራይን ህዝብና የአለም አቀፉን ማህበረሰብ ጨርሶ ላለማጣትም ጦሩ ወደ ትግራይ ክልል ዘልቆ እርምጃ እንዳወስድ ከድንበር ላይ አስቁሞ የተጋጋለውን የህዝብ ስሜ ለማቀዝቀዝ እየተሞከረ ይገኛል፡፡
      ልብ በሉ!! ጠቅላይ ምኒስትሩ ሁሉንም ላለማጣት ሲሉ እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ውሳኔዎችን ለማስተናገድ ሲጥሩ ይስተዋላሉ፡፡ በመሰረቱ አንድ መሪ ሁሉንም ሊያስደስት አይችልም፤ በሚወስዳቸው ውሳኔዎች አንደኛው ወገን ሲያስደስት ሌላኛውን ወገን ማስከፈቱ የማይቀር ነው፡፡ ማስከፈት ማስደቱ የማይቀር እስከ ሆነ ድረስ አደጋውን ለመቀነስ የብዙሀኑን ጥቅም መጠበቅና ማስከበር ያስፈልጋል፡፡ የሕወሓት-ኢህአዴግ መንግስት ይህን የአስተዳደር ጥበብ በማጣቱ አወዳደቁን ታላቅ አድርጎታል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ አንድ የሀገር መሪ ከቡድን ስሜት ወጥቶ ሁሉም ለፍትህና ለእውነት መቆም ያለበት ይመስለኛል፡፡ ጠቅላይ ምኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ግን ይህን እያደረጉ አይደለም፡፡ ጠቅላይ ምኒስትሩ ቢያንስ ቢያንስ ለአንድ ሥርዓት ዴሞክራሲያዊነት የግድ አስፈላጊ (Necessary for ademocratic society) ናቸው በሚባሉ አካሄዶች መራመድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የዶክተር አብይ አሁናዊ አካሄድ ጆርጅ አርዌል ፖሊቲካዊ ሽሙጥ (Poleteical satire) ጋር ይዛመድብኛል፡፡ ጆርጅ አርዌል፡ “ሁሉም እንሳሳት እኩል ናቸው፤ ጥቂቶች ግን ከሌሎች የበለጠ እኩል ናቸው” ነበር ያለው፡፡ ዶክተር አብይ አገር በጋራ የአመለካከት መዋጮ እንደምትመራ የዘነጉት ይመስላሉ፡፡ ሁሉም አገራዊ ጉዳዮ በእርሳቸው በጎ ፈቃድና ትእዛዝ በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ አዋጭ አማራጮችን እያቀረበ የሚሞግታቸው ሰው በመንበረ-ሥልጣናቸው ዙሪያ መኖሩን በበኩሌ እጠራጠራለሁ፡፡ ጠቅላይ ምኒስትሩ ሁሌም ልክ ናቸው የሚል አይነጥላ ሰዎቻቸውን እንደተጠናወተ ይሰማኛል፡፡ በእዚህና ይህን በመሳሰሉ ምክንያቶች ሰውየው ፈላጭ ቆራጭ አምባገነን በመሆን ሂደት ላይ ይገኛሉ፡፡
3.  የሰሜኑ ጦርነት በምን ይቋጭ!?
በበኩሌ የአፋርና የአማራ ህዝብ እንደተገደለው የትግራይ ሕዝብም መገደል አለበት፣ የአማራና የአፋር ህዝብ ሀብትና ንብረት እንደወደመው የትግራይ ሕዝብ ሀብትና ንብረት መውደም አለበት፤ ደም መፋሰሱም መቀጠል አለበት የሚል አመካከት የለኝም፡፡
ነገር ግን ጦርነቱ ጠቅላይ ምኒስትሩ ሲፈልጉ የሚያስቆሙት ሲፈልጉም የሚያስቀምጥሉት መሆን እንደሌለ እረዳለሁ፡፡ የእነ ደብረጽዮንና ጌታቸው ረዳ … ተፈጥሮአዊ ባህርይ እስከ እለተሞታቸው ድረስ በጦርትና በተግዳሮቶች ውስጥ መኖርን ነው የሕይወት መርሃቸው አድርገው የሚከተሉት፡፡
4.  ሕወሓት የአእምሮ ህሙማን ስብስብ ነው
ሕወሓት በመላለው አለም ከሚገኙ አማፅያን ሁሉ ይለያል፤ ሕወሓት ለጥፋትና ለውድመት ብቻ የተፈጠረ የወንጀለኞች ስብስብ ነው፡፡ ሕወሓት የአእምሮ ህሙማኖች ስብስብስ ነው፤ ሰዎችን ገድሎ ቆዳቸውን የሚገፍና የሚያቃጥል፤ እንዲሁም እንሰሳትን ሳይቀር በጥይት ደብድቦ የገደለና ያቃጠለ  ጤናማ አእምሮ ያለው ቡድን አይቼም ሰምቼም አላውቅም፡፡
ለምሳሌ አልሸባብ የተባለው አማፂ ቡድን ታላቋ ሶማሊያን መመሥረት ነው አላማው፤ ቦክሃራም እና አይሲስ”ን የመሣሠሉ አማፅያኖችም ግባቸው እስላመዊ መንግስት መመስረት ይሆናል፡፡ የትግራዩ ሕወሓት ግን እስከ ሲኦል ድረስ ወርዶም ቢሆን ኢትዮጵያን ማፍረስ፣ ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ ማወራረድድ፣ የአማራና የአፋር ሴቶችን አስገድዶ መድፈር …. የመሳሰሉ የእብደት ተግባራትን መፈፀም ነው አላማው፡፡ ታዲያ! ይህን ለመሰለው ፀረ-ህዝብና ፀረ-ኢትዮጵያዊ ቡድን በህልውናው እንዲቆይ የፋታ ጊዜ መስጠት ምንድነው የሚባለው!?
ሕወሓት የአፋርንና የወሎን ምድር በሀይል እንዲለቅ ከተደረገ በኋላም ጦር መስበቁን አሁንም አላቆመም፡፡ ከእዚህ በኋዋላ ህወሓት በሁመራና በአፋር በኩል መተላለፊያ ኮሪደር ለማግኘት እንደሚፋለምም ሶስተኛውን እቅድ ነድፎአል፡፡ እናስ የወታደሩ የውጊያ ተነሳሽነት እስኪቀዛቀዝ መጠበቅ ጦርነቱ እንዳያበቃ ከመፈለግ የመነጨ ነው ቢባል ስህተት ሊሆን ይችላል!? አይመስለኝም፡፡
የአማራና የአፋር ህዝብ በጦርነቱ ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ከደረሰበት ኢኮኖሚው ውድመት በቀላሉ ያገግማል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ምናልባትም እንደገና ለማገገም 30 እና 40 አመታት ያስፈልጉታል፡፡
5.  አፋርና አማራ ለአፍታም ቢሆን አይዘናጋ!
ከላይ እንደገለጽኩት ህወሓት የአእምሮ ህሙማን ስብስብ በመሆኑ በፈጸማቸው ጥፋትና ውድመቶች የሚኩራራ እንጂ የሚፀፀት አይደለም፡፡ አሁንም ተደጋጋሚ ጥቃት በአማራና በአፋር ሕዝብ ላይ ለማድረስ ሰፊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑ በመነገር ላይ ይገኛል፡፡ የትግራይ ህዝብ ህፃናት አዋቂ ወንድ ሴት ሳይል እስከ መጨረሻው መዋጋት እንዳለበት፣ አንዱ ተዋግቶ በሚያቆየው የትግራይ መሬት ሌላው ያልተዋጋው ሕዝብ መኖር እንዳማይችል እየዛ አስጠንቅቋል፡፡
 ይህ ምን ማለት እንደሆነ የመከራው ገፈት ቀማሽ የሆነው የአማራና የአፋር ህዝብ በሚገባ ያውቀዋል፡፡ ማንም ሰው በአምላክም፣ በብሔራዊም ሆነ በአለም አቀፍ ህግ ራሱን ከማንኛውም ጥቃት የመከላከል መብት አለው፡፡ ህወሓት እስከ መጨረሻው የአማራና የአፋር ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት ነው፤ በመሆኑም የአማራና የአፋር ህዝብ ለራሱ ህልውና ሲል ለደቂቃም ቢኖን ትጥቁን ሳይፈታ ለፍልሚያ መዘጋጀት አለበት፡፡ በተለይ በተለይ ወደ መቀሌ የተወሰዱና የተሰወሩ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም ቀን ከሌት ሲጋዝ የነበረውን ሀብትና ንብረት ባስቸኳይ ሊመለስ ይገባል። ከተቻለ ክልላቸውን ከትጋሩዎች ማጽዳት ካልተቻለም በአይነ ቁራኛ መጠበቅ የግድ ይላል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ከመጨረሻው ዘመን መቅሠፍቶች ይጠብቅ!!!  አሜን።
Filed in: Amharic