>

በኢትዮጵያ የተሸነፈው ጀፍሪ ፊልትማን ...!!! (ሱሌማን አብደላ)

በኢትዮጵያ የተሸነፈው ጀፍሪ ፊልትማን …!!!

ሱሌማን አብደላ

.


በአሜሪካ ታሪክ ፊልትማን (ጀፍሪ)  ብዙ የሀላፊነት ቦታዎችን መርቷል። በብቃት የመራቸው ሃላፊነቶች ቢኖሩ አሜሪካ እንዴት የሌሎች አገሮችን መሪዎች መግደል ወይም መገልበጥ ወይም ማፍረስ እንዳለበት ተልዕኮ መስጠት ማስፈፀም
ነው።
ከሁለት አመታት በፊት በኢትዮጵያ እገዛ መንግስት የመሰረተችው ሱዳን በፊልትማን እገዛ መንግስት አልባ ሆናለች። አሁን ጎረቤት አገር ሱዳን መንግስት እንኳን ለመመስረት የምዕራባውያንን ይውንታ ማግኘት አለባት። የዚህ ስራ ባለቤት ፊልትማን ነው። መንግስት አልባዋን ሱዳን ለዚህ ያበቃትም ይሄው ጀፍሪ ፊልትማን ነው።
ፊልትማን የሴራ እቅዱን ሞክሮ ያልቻለው ኢትዮጵያን ብቻ ነው። በየ” ስምንት ቀኑ እየተመላለሰ የአሜሪካን ትዕዛዝ ለማስፈፀም የቻለውን ያህል ቢሞክርም በመጨረሻም እጅን ለኢትዮጵያ ሰቷል። ዛሬ የመጨረሻውን ጉዞ ኢትዮጵያ ላይ አድርጎ ስልጣኑን ይለቃል። ይመጣል መባሉን እንጅ መምጣቱን እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም። አመት ሙሉ ዞሮ ያላሳካውን ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መቶ የሚሳካለት አዲስ ነገር አያገኝም።
ፊልትማን በአሜሪካ መንግስት የ2021ዱ ተቀባይነት ያጣ የተሰጠውን የቤስራ መስራት ያቃተው የተናቀ ዲፕሎማቲኳ ነው የሚል ዜና ያነበብኩት ከ9 ቀን በፊት የዱባይ ጋዜጣ ላይ ተፅፎ ነበር። ይህንን ዜና አየሁት እንጅ ብዙም ትኩረት አልሰጠሁትም ነበር። ይህ ዜና ግን ያለምክኒያት አሎጣም ነበር። በዛ ሰፈር ነፍ መረጃዎች ይወጣሉ። በዱባይ የተሰገሰጉ የCIA” ሰዎች የሰሙት ነገር ነበር ማለት ነው።
ተሸናፊው ፊልትማን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ወያኔን ለማምጣት የቻለውን ሁሉ ሞክሯል። አገሪቱ እንደ ሱዳን መንግስት አልባ ሆና ቀጣይ የጦርነት አውድማ ለማድረግ አስቦ ቢሰራም ሀሳብ ሆኖ ቀረጅ አልተሳካለትም። ከሱዳን ጀነራልች እስከ ግብፅ መንግስት ከዱባይ እስከ ተርኩ ከአሜሪካ እስከ ኬኒያ የዘረጋው የፀረ ኢትዮጵያ ኔቶርክ ባለበት መክኗል።
በመጨረሻም ተሸንፎ ከስልጣን
የሚያስባርረውን ስራ ሰርቷል። ኢትዮጵያና ኤርትራን ከአሜሪካ አጋርነት ነጥቆ ለቻይና አስረክቧል። አሁን ቻይና የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ አገሮች ላይ ዝሆኖቿን አሰማርታለች። በቅርቡ የሚሰሙ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ።
ለእንዲህ ያለው ድል የበቃነው፣ ህዝባችን ከወታደራችን ጎን ቆሞ ወታደራችን ባገኘው የውጊያ ድል ሲሆን ለዚህም መንግስታችን በያዘው ፅኑ አቋም እና፣ ሚዲያ ላይ ባለን የተጣመረ አሰራር ነው። ፅናት የማይቀይረው አቋም የለም። አንድነት የማይገራው ጠማማነት የለም።
ታዲያ ይሄንን አስገራሚና አስጨናቂ ጊዜ በሩቅ ሆኖ ሲከታተል የኖረው የሱዳን ብሔራዊ ኡማ ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ፦ ኢብራሂም አልአሚን አልጀዚራ ላይ ብቅ ብሎ ይቺን የምስክርነት ቃል ሰቷል።
ቻይና በምስራቅ አፍሪካ ቀንድ በአሜሪካ ላይ ለተቀዳጀችው ድል ትልቋ ባለድርሻ  ኢትዮጵያ ናት። ኢትዮጵያ ለቻይና ለዋለችላት ትልቅ ውለታ ምላሽ የሚሆን ውላታ ውላለች። አለም በኢትዮጵያ ላይ ፊቱን ባዞረበት አስቸጋሪ ወቅት የቻይና መንግስት በማንኛውም ነገር ከኢትዮጵያ ህዝብና  የኢትዮጵያ ህዝብ ከተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት ጎን እቆማለሁ በማለት  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ አዲስ አበባ በመላክ ለ #ኢትዮጵያ ትልቅ የዲፕሎማሲ እና የጦር ሜዳ ባለድል እንድትሆን በማድረግ የድል ባለውለታዋን ሀገር በድል መልሳላታለች ።
የፊልትማንንና የኢትዮጵያ እልህ አስጨራሽ ትግል በዚህ ተጠናቋል።
Filed in: Amharic