>

"እስር ቤት ሆኘ ልጄ እንድታየኝ አልፈልግም....!!!"  (መዓዛ መሐመድ)

እስር ቤት ሆኘ ልጄ እንድታየኝ አልፈልግም….!!!”

 መዓዛ መሐመድ

*… የአንተ እስር  ጨምሮ አብረው የታሰሩ የግፍ እስረኞች መሆናችሁ ሁሌም ያስቆጨኝ ነበር! ከገዢው መንግስት የተቃርኖ ሃሳብ ያለውን ፣ ነገር ግን ለሃገሬ የምችለውን ላድርግ ፣ ልናገር የሚለውን እያሳደዱ ማሰር የወያኔን ውድቀት ስለ ማፋጠኑ አሁን ላይ አለን የሚሉ ሹማምንት ካልተማሩበት እዛው አዙሪት ውስጥ መሆናችን ያሳዝነኛል
     ከባለፈው አንድ ወር ጀምሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የምትገኘውን ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድን የባልደራስ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ  ዛሬ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ጠይቋታል።
      ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ፤ በአንድ አንስተኛ  ክፍል ውስጥ እስከ 35 ከሚሆኑ እስረኞች ጋር ታስራ የምትገኝ ሲሆን፤ የታሰረች ሰሞን ለሁለት ጊዜ ያህል መርማሪዎች መጥተው ከማናገራቸው ውጪ እስካሁን ያናገራት አካል የለም። ልጇ እንደናፈቀቻት ነገር ግን በእስር ላይ ሆና ልጇ እሷን ማየቷ” ለህሊናዋ ጥሩ ስለማይሆን እንድታየኝ አልፈለግኩም ፤ እናቴን እያለች እሷም እየጠየቀች ነው” በማለት መዓዛ በጥልቅ ሐዘን ውስጥ ሆና ገልፃለች።
    የባልደራስ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድን “የታሰርሽው በስራሽ ነው” በማለት አይዞሽ ፣ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እንዲሁም ሌሎች አላግባብ የታሰሩ ፍትሕ እንዲያገኙ  የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን ብሏል ።
    ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ለእስክንድር “ከእስር በተፈታህ ማግስት እኔንም  ለመጠየቅ መጥተህ መከልከልህን ሰምቻለሁ። ዛሬም መጥተህ አይዞሽ በማለትህ ደስ ብሎኛ፤ እግዚአብሔር ያክብርልኝ” ብላዋለች ። አያይዞም እንደገለጸችው ከእንዲህ አየነቱ አዙሪት የምንወጣው መቼ ይሆን?! የአንተ እስር ሁሌም ያስቆጨኝ ነበር፤ አንተን ጨምሮ አብረው የታሰሩ የግፍ እስረኞች ነበራችሁ። ከገዢው መንግስት የተቃርኖ ሃሳብ ያለውን ፣ ነገር ግን ለሃገሬ የምችለውን ላድርግ ፣ ልናገር የሚለውን እያሳደዱ ማሰር የወያኔን ውድቀት ስለ ማፋጠኑ አሁን ላይ አለን የሚሉ ሹማምንት ካልተማሩበት እዛው አዙሪት ውስጥ መሆናችን ያሳዝነኛል” ብላለች።
Filed in: Amharic