“የመስቀል ዐደባባይ ማለት ምን ማለት ነው?”
ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው
ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እስኪ አንድ እጅግ ቀላል የሆነ ጥያቄ ልጠይቅሽ::በኛ ቤተ ክርስቲያን የሕጻናት ክፍል ተማሪዎች የሚመልሱት ነው::ለመ ሆኑ:-“የመስቀል ዐደባባይ ማለት ምን ማለት ነው?”
የድፍረት ንግግርሽን እንደ ሰማሁት መልሱን አላገኘሽውም::እንኳን ልትመልሽው በርቀት እንኳ በአጠገቡ አላለፍሽም::መልሱ ያለው በምሥራቅ ሲሆን አንቺ እየዳከርሽ ያለሽው በምዕራብ ነው:: ምዕራብ ደግሞ ይዞ የሚመጣው ጨለማን ነው:: ምሥራቅ ግን ብርሃንን ነው::አንድም ምሥራቅ ብሂል ማኅደረ እግዚአብሔር የሚለውን ጠቅሰን: ምዕራብ ብሂል … የሚለውን ግን ለጊዜው እንተ ወው::ብርሃን ዕውቀት የሚለውንም ይዘን የጨለ ማን ለጊዜው በሠላሳ እንግደፈው::
እስኪ ወደ መልሱ እንሂድ::የመስቀል ዐደባባይ ማለት:-ክርስቶስ በደሙ ፈሳሽነት ለቀደሰው እና ላከበረው ክቡር መስቀል በአደባባይ በገሃድ የሚሰገድ በት:የመስቀል ክብር በንባብም በዜማም የሚገ ለጥ በት ስፍራ ነው::መዝ:131%7::”የመስቀሉ ቃል ለሚ ጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብ ሔር ኃይል ነው::”ተብሎ የሚታወጅበት:”ከጌታችን ከኢየ ሱስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ክእኔ ይራቅ:: “የሚባልበት መቅደስ ነው::1ኛ::ቆሮ:1%18::ገላ:6% 14::ይህንን ደግሞ ከጥንት ጀምሮ በራሷ ይዞታ ላይ ስትፈጽም የኖረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ናት::የመስቀል አደባባይ ብላ የሰየመ ችውም እርሷ ናት::አንቺም በባለቤትነት ሳይሆን በእንግድነት በበዓለ መስቀል ላይ እየተገኘሽ ንግግር አድርገሻል:ደመራ ለኩሰሻል::ቤተ ክርስቲያን ባታከብ ሯትም እርሷ ግን እንዲህ አድርጋ ነው የምታከብራ ችሁ::
ታድያ የመስቀል አደባባይ ትርጉም ይሄ ከሆነ ክብረ መስቀልን በአደባባይ ከካዱ አክራሪ ፕሮቴስታ ንት እና ነገረ መስቀሉ ከማይመለከታቸው አክራሪ ሙስሊሞች ጋር ምን አገናኘው? ምንም::ሰሞኑን ሕወሓት ከጦርነቱ ባሻገር መንግሥትን እና ሕዝብን እየዘረፈ ነው እያላችሁ ነው::እውነት ነው::አንቺስ በሥልጣንሽ ተመክተሽ:ለእምነት ድርጅትሽ አድል ተሽ ከጥንት ጀምሮ ይዘን የኖርነውን ይዞታችንን በጠራራ ፀሐይ ትዘርፊናለሽ? ለመሆኑ ለጎሳሽም ለእሬቻም ለፕሮቴስታንትም እያደላሽ እንዴት ነው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ስትዪየከረምሽው? ያ የትኅትና ንግግርስ ከምን ግዜው ጠፍቶ ነው ወደ ትዕቢት ንግግር የተመለስሽው? መስቀል አደባባይ እኮ የ65 ሚሊዮን ኦርቶዶክሳውያን ርስት ነው::ኢትዮጵያም ከጥንት እስከ ዛሬ ሰማዕትነት የከፈልንላት ታቦት እና መስቀል ይዘን ዳዊት አንግተን የዘመትንላት ርስታ ችን ናት::በመሆኑም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የጋራችን: የአምልኮ ስፍራችን ግን የግላችን ነው::
ወደ መፍትሔው እንሂድ::መፍትሔው ምን መሰለሽ? ሌሎች ሁለት አደባባዮችን ሥሪ እና አንደ ኛውን ኢድ አደባባይ በዪው ሁለተኛውን ደግሞ ፓስተር አደባባይ በዪው::በተረፈ ስለ መስቀል አደ ባባይ የተናገርሽውን በባለቤቱ ፊት እንድትናገሪው
ለመስከረም 16 ቀን 2015 ብታቆዪው መልካም ነው::
ሀገር በውስጥም በውጭም በተወጠረችበት በዚህ የጭንቅ ወቅት ለሕዝቡ የሚከፋፍል አጀንዳ ባትፈ ጥሩለት ጥሩ ነበር::
አባቶች በመግለጫ የሚመለስ መከራ የለም…!!!
ቤተክርስቲያን ስትቃጠል መግለጫ::ካህናትና ምእመናን ሲታረዱ መግለጫ::የዐደባባይ በዓላትን እንዳታከብር እንቅፋት ሲፈጠር መግለጫ::በዐውደ ምሕረቷ የሰቀለቻቸው:ምእመናን የለበሷቸውና ከበሮዎቿን ጭምር ያለበሰቻቸው ሰንደቅ ዓላማዎች እየውረዱና እየተገፈፉ ሲጣሉ መግለጫ::የጥምቀተ ባሕርና የመስቀል አደባባይ ቦታዎቿ ሲነጠቁ መግ ለጫ::ለሁሉ ነገር መግለጫ:መግለጫ:መግለጫ::
ሰሚ ግን የለም::እንኳን የሚሰማ የመስማት ፍላጎት እንኳ ያለው የለም::አትድከሙ::
እባካችሁ አባቶች ለሀገራችሁ እና ለቤተ ክርስቲያናችሁ የምታስቡ ከሆነ እነርሱ መግለጫ ከማውጣት በስተቀር ምንም አያመጡም እየተባላችሁ መንጋውን አታስበሉ::ፈረጅያችሁን አውልቃችሁ በአጭር ታጥቃችሁ ከልጆቻችሁ ጋር ተሰለፉ:: ደረጃ ውን ከጠበቀ ቢሮ ተቀምጣችሁ የምታወጡት መግለጫ ከሚድያ ፍጆታነት አያልፍም::
ከልቤ የምወዳችሁ እና የማከብራችሁ አባቶቼ በመግለጫ ጋጋታ የሚመለስ መከራ የለም በጸሎት እና በትግል ነው::