>

መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያየ...!!!  (የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ )

መስቀል አደባባይን በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያየ…!!!
 የኢ/ኦ/ተ/ቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ 

አዲስ አበባ፥ ኢትዮጵያ)
ሰሞኑን በመስቀል አደባባይ የተደረገውን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች መንፈሳዊና የገቢ ማሰባሰብ መርሀ ግብር ላይ የተነሱ የመብትና የይዞታ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስተላለፉት የተባለውን መልዕክት ተከትሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም ረፋድ 9 ሰዓት ላይ ጉባኤ አካሒዷል።
በጉባኤውም ከፍ ሲል የተገለጸውን ርዕስ መሠረት በማድረግ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ክብርት ከንቲባዋ ዓርብ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት 4 ሰዓት በቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ በሚካሔደው ጉባኤ ጉባዔ ላይ እንዲገኙና
ማብራሪያ እንዲሰጡ ቀጠሮ እንዲያዝ እና ጉዳዩ በተረጋጋ መንገድ ውሳኔ እንዲያገኝ መመሪያ ሰጥቷል።
ይህ ሲኖዶሳዊ ውሳኔ የቤተክርስቲያኒቱ የመጨረሻ የሥልጣን ባለቤት የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠው ውሳኔ በመሆኑ ለውሳኔው ተግባራዊነት ሁሉም ወገን የድርሻውን ማበርከት የሚጠበቅበት መሆኑን በመገንዘብ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቅዱስ ሲኖዶስ ዓርብ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም በሚካሔደው ጉባዔ
እልባት እንደሚሰጠው ይታመናል።
ስለሆነም ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ ዙሪያ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ ማንኛውም የቤተክርስቲያኒቱ እምነት ተከታይ ሕግና ሥርዓትን ጠብቆ ቅዱስ ሲኖዶሱ የሚሰጠውን ውሳኔ ማክበር እንደሚገባው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን
መልዕክቷን ታስተላልፋ ለች።
Filed in: Amharic