>

የፓለቲካው የኃይል ሚዛን ወዴት እየሄደ ይሆን...??? (ኤርሚያስ ለገሰ)

የፓለቲካው የኃይል ሚዛን ወዴት እየሄደ ይሆን…???

ኤርሚያስ ለገሰ

፩ኛ፡ እነ ጀዋር መሐመድ በአዲስ መንፈስ በተደራጀ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ፓለቲካ ለመግባት እያሟሟቁ ነው።
፩ኛ፡ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወደ አገር ቤት መግባታቸው ተሰምቷል።
፪ኛ፡ አቶ ለማ መገርሳ ወደ አገር ቤት ገብተዋል የሚል ነገር ሰምቻለሁ።
፬ኛ. እያጣራሁት ቢሆንም ቱጃቱ አቶ ድንቁ ደያስም ወደ አገር ቤት ያለፈው ሃሙስ መግባታቸውን ሰምቻለሁ ።
፭ኛ፡ የኦህዴድ ብልጽግና እና እነ ኦቦ ሌንጮ ለታ በአገር ውስጥም ሆነ ከሃገር ውጪ ተጽእኖ ፈጣሪ የኦሮሞ ብሔርተኛ ፓለቲከኞችን ለማግባባት ጥረት እያደረጉ ነው።
ምክረ-ሃሳብ፡- በተደጋጋሚ እንደምገልጸው በየትኛው አደረጃጀት ውስጥ የታቀፉ የኦሮሞ ብሔርተኞች ከስልጣን ውጭ በመሰረታዊ የኦሮሞ ጥያቄዎች በሚሏቸው ላይ ይህ ነው የሚባል ጉልህ ልዩነት የላቸውም። መሰባሰባቸው ይህንን ጥያቄዎች የኢትዮጵያን አንድነት ባስጠበቀ፣ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ የዜግነት መብት ባስከበረ፣ በዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊና በሰላማዊ ትግል መንገድ የምትገልጡት ከሆነ እሰየው። እንኳንም ወደ አገራችሁ ኢትዮጵያ በሰላም ገባችሁ።  እናም የዘወትር የእኔ ምክረ-ሃሳብና ጥያቄ ‘የአማራ ኃይሎች’ ከዚህ ትምህርት በመውሰድ ትርጉም ያለው የፓለቲካ የኃይል ሚዛን ለመፍጠር ምን አይነት ስትራቴጂክ ስራዎች እየሰሩ መሆናቸውን ማወቅ ነው። የአማራ ማሕበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመለየት የኃይል ማሰባሰቡን ምን ያህል እየሰሩት መሆኑን ማወቅ ነው። ከዚህ በኋላ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አይን የሚያርፍብህ ትርጉም ያለው የኃይል ሚዛን (Power balance) ሲኖርህ ብቻ ነው። ከሌለህ የለህም!
ማሳሰቢያ፡- እኔ “ኢትዮጵያዊ ብሔርተኛ” ነኝ! ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለቱም ፓለቲካዊ ብሔርተኝነት ውስጥ የለሁበትም!… ለጊዜው ከስትራቴጂም ሆነ መሬት ላይ ካለው ነባራዊ እውነታ አንጻር የንዑስ ብሔርተኞቹ የኃይል ሚዛን መጠበቅ “ፓለቲካዊ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትን” ሊያመጣ ይችላል የሚል የሰለለና ያልተሟጠጠ ተስፋ ግን አለኝ።
Filed in: Amharic