>

"ባልደራስ ስለ ወይብላ ማርያም ያወጣው መግለጫ‼

ባልደራስ ስለ ወይብላ ማርያም ያወጣው መግለጫ‼


 

’መንግስት’ ህግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ አበክረን እንገልፃለን
*. .. “ዛሬ ቀራንዮ  በሀዘን ተውጣለች፤ የዋይታ ድምጽ በርክቷል፤ ልጆቿ በእንባ ታጥበዋል፥ አንገታቸውን ደፍተዋል፤ 
ሁሉም ያልፋል…!!!”
 
ዛሬ ጥር 12/2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የወይብላ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለጥምቀት የወጣ ታቦታ እና አጅበውት በነበሩት ህዝበ ክርስቲያን ላይ የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል ተኩስ በመክፈት ታቦቱ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገባ ባደረጉት ክልከላ እና ይህን ተከትሎ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካታ ምዕመናን ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡
በዚህ ግጭት ከልጅ እስከ አዛውንት የአካል እና የስነ-ልቦና ጉዳት በምዕመናኑ ላይ መድረሱን የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ተገንዝቧል፡፡ በርካታ ምዕመናን በህክምና  መስጫ ተቋማት ህክምና እየተከታተሉ እንደሆነም ለመረዳት ተችሏል፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለፀ የኦህዴድ/ብልፅግና ’መንግስት’ አሁንም ህግ የማስከበር ተቀዳሚ ተግባሩን አለመወጣቱን ባልደራስ አበክሮ ያወግዛል፡፡
አሁንም እየደረሰ ላለው ውጥረት እና ግጭት ’መንግስት’ ህግ እንዲያስከብር እንጠይቃለን፡፡
 ጉዳት ያደረሱትን የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑም ባልደራስ ይጠይቃል፡፡
Filed in: Amharic