የህውሃት ደጋፊ ምሁራን አቋም ምንና ምን?
ደረጀ መላኩ ( የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)
‹‹ ሰዎች በማሰብ ችሎታ እና ትምህርት ጋር መሃከል ያለውን ችሎታ ከመረዳት አኳያ ግራ ሲጋቡ ደስተኛ አይደለሁም፡፡ ድግሪ ሊኖርህ ይችላል፡፡ ያልተማርክ ደደብም ልትሆን ትችላለህ ›› ኤሎን ሙስክ
“I hate when people confuse education with intelligence, you can have a Batchelor’s degree and still be an idiot” Elon Musk
መግቢያ
ምሁራን ሰፊ (ብዙ) እውቀት እንዳላቸው ግለሰቦች ሊቆጠሩ ይገባል፡፡ ምሁራን ምክንያታዊ ሆነው ለማሰብ ችሎታ አላቸው፡፡ አንድ ምሁር የሚመራው በራሱ ንቃተ ህሊና እና እውቀት ፣ገለልተኛ በሆነ የምርምር ውጤት እንጂ በስሜት አይደለም፡፡ አንድ ምሁር ገለልተኛ አሰላሳይ ፣ ከሳጥኑ ውጭ ማሰብ የሚችል (who is capable of thinking outside the box )፣በእውነተኛ ምርምር ጥናትና አስተሳሰብ የሚደሰት፣ለመረጃ ስሁት የሆነና ዘውትር የሚከታተል፣ለፍትህ እና ነጻነት የሚታገል ወዘተ ወዘተ ነው፡፡ ምሁር ተብሎ ለመጠራት የሙያን ስነምግባር ማክበር ሰልፉ ከህዝብ ጋር መሆኑ ግድ ይላል፡፡
የወያኔ አሸባሪ ቡድን በራሱ አምሳል የቀረጻቸው ምሁራን በዚች ምድር ላይ መፈጠራቸው አስገራሚ ነው፡፡ የምሁራን ካባ ደርበው ልክ እንደፈጣሪያቸው ወያኔ አንድ አይነት እሳቤ ያላቸው ምሁራን መታየታቸው አስገራሚም አስደማሚም ነው፡፡ እንዲህ አይነት የፊደል ቆጣሪዎች የምሁራን ኢለመንት የላቸውም፡፡ እነርሱ ወያኔ ከርቀት በሪሞት ኮንትሮል የሚቆጣጠራት አንጎል እንደሌላት ድሮንስ የሚቆጠሩም ናቸው፡፡ ወያኔ እንደ ራሱ እንዲያስቡ አድርጎ የሰራቸው ሮቦትም ይመስላሉ፡፡ ልክ የሰሜን ኮሪያውን የኪምኢል ሱንግን ስርወ መንግስት (the Kim Il-sung dynasty) በጭፍን እንደሚያመልኩት የሰሜን ኮሪያውያን ተወላጆች ሁሉ እነኚሁ ምሁራን ተብዬዎች የወያኔ አሸባሪ ቡድንን በጭፍን የሚደግፉ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የትግራይ ምሁራን ተብለው የሚጠሩት ትእዛዝ የሚቀበሉት ከወያኔ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ምሁራን የወያኔ አምላኪዎች ናቸው፡፡ የራሳቸው አስተሳሰብና የሞራል ካምፓስ የላቸውም፡፡
የወያኔ ጦርነት በኢትዮጵያና የትግራይ ምሁራን ሚና
እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ2020 የወያኔ አሸባሪ ቡድን የጦርነት አዶከበሬ በሚመታበት ግዜ( የጦር ነጋሪት በሚጎስምበት ግዜ) ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተወጣጡ እና እምባቸውን የሚዘሩ እናቶች ወደ መቀሌ በማቅናት በጉልበታቸው ተንበርክከው ጦርነት እንዳይከፈት፣ከማእከላዊ መንግስቱ ጋር የገጠማቸውን የፖለቲካው ልዩነት በሰላም እንዲፈታ ተማጽኖ ሲያቀርቡ ዶክተር ደብረጽዮን የዝሆን ጆሮ ነበር የሰጡት፡፡ የኦሎምፒክ ጀግናውን ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ፣የሀይማኖት መሪዎችን እና ታዋቂ ሀገር ሽማግሌዎችን ያካተተ አንድ ቡድንም ለተመሳሳይ አላማ ወደ መቀሌ አቅንቶ የነበረ ቢሆንም የተሰጣቸው ተመሳሳይ መልስ ነበር፡፡ በነገራችን ላይ ከሚገባው በላይ በራስ መተማመን ፣በራስ መተማመንን ሊያጠፋው ይቻለዋል፡፡ Overconfidence/deceit is as dangerous as losing confidence ብዙዎች ኢትዮጵያውያን የትግራይ ተወላጅ ምሁራን ከፍርሃት ቆፈናቸው በመውጣት የወያኔ አሸባሪ ቡድን መሪዎች ከእብደታቸው እንዲወጡ ምክረ ሃሳብ ያቀርባሉ በሚል ተስፋ አደርገው ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ተስፋው ተስፋ ሆኖ ቀርቷል፡፡ በተቃራኒው አብዛኛው የአከባቢው ተወለጆች የሆኑ ምሁራን እነርሱ ጭፍን የወያኔ ቡድን ደጋፊ ሆነዋል፡፡ የወያኔ ቡድን የጦርነት አዱከበሬ ሲመታ እነርሱ አጃቢ ሆነው ቆመዋል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም የወያኔ አሸባሪ ቡድን የኢትዮጵያን ማእከላዊ መንግስት በማዳከም የታላቋን ትግራይ ሪፐብሊክ እመሰርታለሁ በማለት በመላው አለም የሚገኙ የትግራይ ምሁራንን በመሰብሰብ ሲሰብክ አብዝሃው ምሁራን ሰይጣናዊ እቅዱን ተቀብለውት ነበር፡፡ ( አብዛኞቹ የፒኤች ድግሪ፣ማስትሬት ዲግሪ የጨበጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሀኪሞችና የምህንድስና ወዘተ ዘወተ ይገኙበታል፡፡ ) ከትግራይ ምሁራን መሃከል አንዱ ግን በድፍረት ባነሳው ጥያቄ የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት ከማእከላዊ መንግስት ጋር ጦርነት የሚገጥም ከሆነ የትግራይ ህዝብ በመሰረታዊ ፍላጎቶች ሊሰቃይ ይችላል የሚል መሰረታዊ ጥያቄ በማንሳታቸው ምክንያት የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪዎችን አስቆጥቶ ነበር፡፡ ለአብነት ያህል ከድርጅቱ አንዷ አንጋፋ ተጋዳላይ የሆኑት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዛብሔር ( ሞንጆሪኖ) በቁጣ ጠያቂው ላይ በማንባረቅ እውን መቀሌ ጨለማ ውስጥ ተዘፍቃ አዲስ አበባ ሰላም የምትሆን ይመስልሃል፣ በምንም አይነት የመሰረታዊ ፍላጎት እጥረት እንደማይከሰት በሙሉልብ እንደተናገሩ በግዜው ከመገናኛ ብዙሃን እንደተከታተልኩ አስታውሳለሁ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም አብዛኞቹ የትግራይ ምሁራን የወያኔ አሸባሪ ቡድን የፖለቲካ ፊትአውራሪዎችን አላማ ደግፈው ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ከሚገባው በላይ በራስ መተማመን በራስ ያለመተማመንን ሊያስከትል ይችላል ብዬ አስተያየት የሰጠሁት፡፡ (That is why we say overconfidence is as dangerous as losing confidence.)
በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ አሸባሪው የወያኔ ቡድን ታጣቂዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ የጅምላ ፍጅት ሲፈጽሙ፣ አሰገድዶ የመድፈር ወንጀል ሲፈጽሙ፣በአማራ እና አፋር ክልሎች የሚገኙ የመገናኛ አውታሮችን ሲዘርፉና ሲያወድሙ ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት አለም አቀፉ የትግራይ ምሁራን ማህበረሰብ the
ከፈረሱ በፊት ጋሪው
ከ3500 በላይ አባላት አሉኝ የሚለው የትግራይ አለም አቀፍ ማህበረሰብ ምሀራንና ባለሙያዎች ማህበር በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የአለም ህዝብን ያስገረመ እና ለትግራይ ያደለ መግለጫ አውጥቶ ነበር፡፡ ይህ አቋም በ3ኛው ነጥብ ላይ የተቀመጠ ነበር፡፡ እንፈሚከተለው ይነበባል፡፡
‹‹ በአለም አቀፍ የባህር ህግ አንቀጽ 125 መሰረት ትግራይ አለም አቀፍ ድንበርና የባህር በር ያስፈልጋታል ›› የሚል ነበር፡፡ የእንግሊዝኛወ ቋንቋ የበለጠ ገላጭና ማስረጃም ስለሆነ እንደወረደ አቅርቤዋለሁ፡፡
“Equally essential and related to the territorial integrity of Tigray is access to international borders, and the right of access to and from the sea and freedom of transit as provided in article 125 of the Law of the Sea. These constitutional and international rights are non-negotiable vital interest of Tigray”
ምሁር ኢንቴጌሪቲ ከሌለው እንዴት ምሁር ተብሎ ሊጠራ ይችላል ? ይገርማል፡፡ ይደንቃል፡፡ ከላይ የተጠቀሰው አባባል ‹‹ ከፈረሱ ጋሪው ሥለመቅደሙ›› ድምጸት ይሰጠናል፡፡ በኢትዮጵያ የቆየ የአባቶች ብሒል አለ፡፡ ይሄውም ‹‹ እስቲ መጀመሪያ ሚዳቋ ሥጋ ትሁን ›› (“Let the common duiker be meat first ) እነኚህ ግለሰቦች ትግራይ ለብዙ ሺህ አመታት የኢትዮጵያ የግዛት አንዷና ዋነኛዋ ስለመሆኗ የሚያውቁ አልመስልህ አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ ስለ ትግራይ መጻኢ እድል የሚወስነው የአለም አቀፉ ብይነ መንግስታት ማህበር ወይም በሌላ አለም አቀፍ አካ ሳይሆን በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ነው፡፡ በነገራችን ላይ የትግራይ ነጻ አወጭ ድርጅት ብቻውን ያለ ኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍና ይሁንታ የተመኙትን የሚያገኙ አይመስለኝም፡፡ ለአብነት ያህል አብክሃዚ፣ ሶማሌ ላንድ እና የቱርክ ሪፐብሊክ ሰሜን ሳይፕረስ (For example, look at Abkhazia, Somaliland, and the Turkish Republic of North Cyprus) ለአስርት አመታት በተባበሩት መንግስታት እውቅና የሌላቸው ሀገር ሆኑ እንጂ ነጻና ሉአላዊ ሀገር መሆን አልተቻላቸውም፡፡ ምክንያቱም የማእከላዊ መንግስታቸው እውቅና ስላልሰጣቸው ነበር፡፡ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር 1991 በባሩድ በርሜል የማእከላዊ መንግስቱን ተቆጣጥሮ የነበረው የወያኔ ኢህአዲግ አገዛዝ ለኤርትራ ባለውለታ ነበር፡፡ በተባበሩት መንግስታትና አፍሪካ ህብረት በመዘዋወር ኤርትራ በአለም አቀፍ ማህበረሰቡ እውቅና እንድታገኝ የወያኔ የፖለቲካ ፊትአውራሪ የነበሩት ሟቹ ጠቅላይ ሚንሰትር አቶ መለሰ ዜናዊ ባለውለታ ከመሆናቸው ባሻግር ኢትዮጵያ የባህር ወደቦቿን እንድታጣ በማድረጋቸው ታሪክ በጥቁር መዝገቡ አስቀምጦታል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ዛሬ ኤርትራ የኢትዮጵያ ሁነኛ ወዳጅ ሀገር ሆናለች፡፡ ስለሆነም አብዝሃው የትግራይ ተወላጅ ምሁራን ከእንቅልፋችሁ ትነቁ ዘንድ አስታውሳለሁ፡፡ ስለ አለም አቀፍ ድንበርና የባህር በር ጥያቄ በፊት ቡናውን እንድታሸቱ በድጋሚ አስታውሳለሁ፡፡ እናንተ የህግም ሆነ የሞራል መብት የላችሁም፡፡ ትግራይ በኢትዮጵያ ምድር የምትገኝ ግዛት ስሆን የትግራይ ተወላጅ ወንድሞቻችን ደግሞ ከብዙ ሺህ አመታት ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡ መራሩን ሀቅ መጋት አለባችሁ፡፡ (They need to swallow the bitter pill.) በትግራይ ኢትዮጵያ ተወልደው ያዱ ኢትዮጵያውያን ምሁራን ቁጥር ከ3500 በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ምናልባትም በ10 ሺህዎችም ሊቆጠር ይችላል፡፡ በትግራይ አለም አቀፍ የምሁራን ማህበር ስም የተደራጁት 3500 የሚሆኑ ምሁራን የፈጸሙትን ስህተት በዝምታ መመልከት ግን ከአጥፊዎቹ ጋር እንደ መተባበር ይቆጠራል፡፡ በቀድሞው አጠራር ቤጌምድር ግዛት ውስጥ የሚገኙት የሁመራ፣ ወልቃይት ጸገዴ እና ሌሎች አካባቢዎች በግፍ በጦርነት በትግራይ ወያኔ ተወስደው ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ከአንድ አመት በፊት በጦርነት መመለሳቸው የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ በታሪክም ቢሆን የጎንደር አንዱ ክፍል እንደነበሩ ክቡር ራስ መንገሻ ስዩም ሳይቀሩ በህይወት ታሪካቸው መጽሐፍ ላይ ጠቅሰውታል፡፡ የትግራይ አገረ ገዢ የነበሩት ክቡር ራስ መንገሻ ስዩም የትግራይ ክልል ተከዜን ተሻግሮ እንደሆነ የታሪክ ምስክርነታቸውን የሰጡበት ጉዳይ ነው፡፡ ከሆናለችሁ በኢትዮጵያ አንድነት ጥላ ስራ የመስራት መብታችሁ ተከብሮ በሁመራም ሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቻችሁ ጋር በሰላምና በፍቅር መኖሩ ያዋጣችኋል እንጂ ትግራይ ለብቻዋ አለም አቀፍ ድንበር ያስፈልጋታል ብሎ መነሳቱ ከባድ ስህተት ውስጥ ይዶላችኋል ብዬ በብርቱ እሰጋለሁ፡፡ ‹‹ አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል›› የሚለውን ያባቶች ብሂል ማስታወሱ ብልህነት ነው፡፡
በአማራና አፋር ክልሎች የተፈጸሙ ግፎች
ጦርነቱ በተጀመረ በስድስት ቀን ውስጥ እና መሸነፋቸውን እንዳረጋገጡ ( እ.ኤ.አ.ህዳር 9 2009) የወያኔ አሸባሪ ቡድን አባላት በንጽኋን ኢትዮጵያዊ ዜጎች ላይ ግፍና ጭፍጨፋ ስለመፈጸማቸው በአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶችና መገናኛ ብዙሃን ተዘግቦ ነበር፡፡ ለአብነት ያህል በማይካድራ ይኖሩ የነበሩ በሺህ የሚቆጠሩ የወልቃይት አማራዎችን መፍጀታቸው ልብን የሚሰብር ነው፡፡ በሌሎች አካባቢዎችም ተመሳሳይ ወንጀል ለመፈጸም ቢያስቡም በአማራ ፋኖ አባላትና ሚሊሻዎች የሽንፈት ጽዋ በመጎንጨታቸው ወደ ሱዳን ሸስተው ለመሄድ ተገደው ነበር፡፡ እነኚሁ የጎሳ ማጽዳት ወንጀል ፈጽመው ወደ ሱዳን የሸሹት ወንጀለኞች በሱዳንና ግብጽ እየተረዱ ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ነው ይባላል፡፡ አላማቸውም ወልቃይት፣ ጸገዴ፣ሁመራን በሀይል ይዘው ለትግራይ አለም አቀፍ ድንበር ለማስገኘት ነው፡፡ ሙከራው አደገኛና ደም አፋሳሽ እንዳይሆን በብርቱ እሰጋለሁ፡፡ ምን አይነት አለም አቀፍ ድንበር ነው የሚፈልጉት ? በደቡብ አፍሪካዊት ሪፐብሊክ ከተከበቡት እና የባህር በር ከሌላቸው ከሌሴቶ እና ከስዋዚላንድ ስርወ መንግስት ታሪክ እንዲማሩ ሳስታውስ በአክብሮት ነው፡፡ (They should learn the history Lesotho and Kingdom Swaziland, which are surrounded by South Africa and landlocked.)
እነኚህ ምሁራን ተብዬዎች እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ1991 ኢትዮጵያ የባህር በሯን በግፍ ስትነጠቅ የብይነ መንግስታቱን የባህር ህግ አንቀጽ በመጥቀስ እውቁ የህግ ሰው ዶክተር ያቆብ ሀይለማርያም ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ሲከራከሩ ከሰዋቸው እንደነበር የአሁኑ ትውልድ ማስታወስ አለበት፡፡ በሌላው የሳንቲሙ ግልባጭ ትልቋ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዳይኖራት ለ27 አመታት ሲከራከሩ የነበሩት እነኚሁ ምሁራን ዛሬ ለትግራይ የባህር በርና አለም አቀፍ ድንበር ያስፈልጋታል በማለት ሲከራከሩ ማየት ያሳዝናል፡፡ እውን እነኚህ ሰዎች ማፈር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያውቃሉን ? አፋርን በወረራ የያዙት ለዚህ ነበርን ? የባህር ወደብ( አሰብ) ለማግኘት ኤርትራ መወረር ሊኖረባቸው ነውን ? በወያኔ አሸባሪ ቡድን ደንዝዘው ቡድኑን በጭፍን የሚደግፉት አብዝሃው የትግራይ ምሁራን በቀን ቅዠት ውስጥ ያሉ ይመስላል፡፡ እባካችሁን ወደ ህሊናችሁ በመመለስ ትልቋን የኢትዮጵያ ስእል በማየት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የምትሆን ሀገርን በአንድነት ለማቆየት ከሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቻችሁ ጋር የህብረት ችቦ ትለኩሱ ዘንድ እማጸናለሁ፡፡
እንደ መደምደሚያ
አንዳንዶች የትግራይ ምሁራን ነን በማለት ራሳቸውን ለሚያንቆለጳጵሱት ይህንን መራር እውነት እንዲገነዘቡት ማድረግ ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ አንዲት ሉአላዊት ሀገር ደንበር ተቆርሶ እገነጠላለሁ ለምትል ክፍልሀገር ወይም ክልል የባህር በር እንዲሰጥ የሚያዝ አለም አቀፍ ህግ ያለ አይመስለኝም፡፡ ካለ የህግ ምሁራን ከእነ ምክንያቱ በማቅረብ እንድታስረዱን ስጋብዝ በአክብሮት ነው፡፡ ኤርትራ እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር ግንቦት 28 1993 (28 May 1993 ) ጀምሮ ነጻ ሀገር ለመሆን ለመብቃት ወግ ደርሷታል፡፡ ( እንደ ወግ ከተቆጠረ ማለቴ ነው፡፡) ምስጋና ለወያኔ ይግባውና ፡፡ ወያኔዎች የራሳቸውንም ሆነ የኢትዮጵያን እድል በ1993( እ.ኤ.አ.) አጥተውታል፡፡ ዛሬ ማንም አሰብን ለትግራይ የሚሰጥ የለም፡፡ አነርሱ በዲጂቡቲም የባህር ወደብ እንዲያገኙ ህጉ አይፈቅድላቸውም፡፡ የትግራይ ክልል በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ እስካለች ድረስ አለም አቀፍ ድንበር ይሰጠኝ ለማለት ህጋዊ መብት የላትም፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ የግዛት ድንበር የሚመለከተው የኢትዮጵያን መንግስት እንጂ አለም አቀፉን አካል ባለመሆኑ ነው፡፡ በአንድ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ላይ የውጭ አካል ጣልቃ እንዳይገባ የሚከለክል አለም አቀፍ ህግ አለ፡፡ ኢትዮጵያ የተለየች ሀገር አይደለችም፡፡ እነርሱ ነጻ ሀገር ከሆኑ ኢትዮጵያ የራሷ አለም አቀፍ ድንብር ይኖራታል፡፡
እንደ ጎርጎሮሲያኑ አቆጣጠር በ1991 ወያኔ የኢትዮጵያን ማእከላዊ መንግስት በሃይል ከተቆጣጠረ በኋላ በታሪክ በቀድሞው አጠራር (የቤጌምድር) የጎንደር አካል የነበሩትን ወልቃይት፣ጸገዴ እና ሁመራን ለ27 አመታት በመቆጣጠሩ ምክንያት ትግራይ ወደ ሱዳን የሚዘረጋ አለም አቀፍ ድንበር አግኝታ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ይሁንና ለ27 አመታት ያህል የወልቃይትና ሁመራ ህዝብ ሲታገል ቆይቷል፡፡ ትግሉም ወደ ቀደመው ግዛታቸው ለመመለስ ነበር፡፡ በወልቃይትና ሁመራ የሚኖሩ ዜጎች ራሳቸውን የሚቆጥሩት ኢትዮጵያዊ ዜጋ እና ይዞታችንም በአማራ ጎንደር ይገኛል ባዮች ናቸው፡፡ የአከባቢው ተወላጆች በወያኔ የጎሳ ማጽዳት ወንጀል ተፈጥሞባቸው እንደነበር፣በቋንቋቸው አማርኛ እንዳይናገሩ፣እንዳይዘፍኑ ወዘተ ወዘተ ጥቃት እንደደረሰባቸው በተለያዩ ግዜያት ለመብት ተቆርቋዎች ከአቀረቡት አቤቱታ ለማወቅ ይቻላል፡፡ የወያኔ አሸባሪ ቡድን አለም አቀፍ ህግን ካልጣሰ በቀር እነኚህን ኢትዮጵያውያንን ከርስታቸው ለማንሳት የሚቻለው አይመስለኝም፡፡ የወያኔን እኩይ አላማ ገቢራዊ ለማድረግ ሲባል የትግራይ ተወላጆች የበለጠ መሰቃየት የለባቸውም ባይ ነኝ፡፡ ወንጀለኞች ሰሚ ጆሮ ሊሰጣቸው አይገባም፡፡ የትግራይ ምሁራን የጦር ወንጀለኞችን የውሸት ትርክት ባለመቀበል፣ እውነተኛ ታሪክን በመመርመር ለኢትዮጵያ የሚበጅ ምክረ ሃሳብ እንዲያቀርቡ በመማጸን ለዛሬው እዚህ ላይ ልሰናት፡፡ ሰላም፡፡