>

"ታስሩን እንደሆነ እናያለን...!!!"  (እስክንድር ነጋ)

“ታስሩን እንደሆነ እናያለን…!!!”
እስክንድር ነጋ

*….. አቶ እስክንድር ነጋ ድሪቶ አልባውን ንፁህ ሰንደቅ አላማ ከአማራ ፋኖ በደሴ ሲቀበሉ “አዲስ አበባ ያላችሁ ገዥዎች ሆይ እናንተ ሕገ ወጥ የምትሉትን ሰንደቅ አላማ ተቀብለና። ይዘነው እንመጣለን። ታስሩን እንደሆነ እናያለን” ብለዋል።  አቶ እስክንድር አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ አላማ ያዛችሁ ተብለው  ሰዎች መገደላቸውን እና መታሰራቸውንም አስታውሰዋል
#በአማራ መስተዳድር የተለያዩ አካባቢዎች ፋኖን እና በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን እየጎበኘ የሚገኘው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ልዑክ ዛሬ እሁድ ጥር 15 ቀን 2014 ዓ.ም. ደሴ ከተማ ገብቷል። በአካባቢው የሚገኘው የአማራ ፋኖ  ከሐይቅ ከተማ ጀምሮ ደሴ እስከ ሚገባ ድረስ ሰንደቅ አላማ በሚያውለበልቡ አይሱዙ፣ ሚኒ ባስ፣ ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎችና በሞተር ብስክሌቶች የታጀበ ለልዑኩ እጅግ ደማቅ አቀባበል አድርጓል።
በደሴ ከተማ፤  ወሎ ዩኒቨርሲቲ በርላይ በደመቀ ወታደራዊ ስነ ስርዓት የአቀባበሉ ማሳረጊያ ተደርጓል።
በማጠናቀቂያውም በቅርቡ ከእስር ለተፈቱት የባልደራስ አመራሮች ማለትም ለአቶ እስክንድር ነጋ፣ ለአቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ለወ/ሮ አስቴር ስዩም (ቀለብ) እና ለወ/ሪት አስካለ ደምሌ ለእያንዳዳቸው የሰንደቅ አላማ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አቶ እስክንድር ነጋ ድሪቶ አልባውን ንፁህ ሰንደቅ አላማ ከአማራ ፋኖ በደሴ ሲቀበሉ “አዲስ አበባ ያላችሁ ገዥዎች ሆይ እናንተ ሕገ ወጥ የምትሉትን ሰንደቅ አላማ ተቀብለና። ይዘነው እንመጣለን። ታስሩን እንደሆነ እናያለን” ብለዋል።
አቶ እስክንድር አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ አላማ ያዛችሁ ተብለው  ሰዎች መገደላቸውን እና መታሰራቸውንም አስታውሰዋል።
በአቀባበል ማሳረጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ የባልደራስ አመራር አባል የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ስዩም (ቀለብ) በእስር ቤት ሆነው የፃፉትን መፅሐፍ ለፋኖ በስጦታ አበርክተዋል።
መጽሐፉ ‘የመሪዎች ሴራ በኢትዮጵያ፤ የተካደው አማራና አዲስ አበቤ’ የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን የብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ታሪክም ተካቶበታል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በአፋር፤ ሰመራ ጉብኝቱን የጀመረው ልዑኩ በቀጣይ ወደ ሸዋ ያመራል።
ትናንት አመሻሹ ላይ ኮምቦልቻ የገባው የባልደራስ ልዑክ የአማራ ፋኖዎችን በኮምቦልቻ አመሰገነ
ላለፉት አስራ አንድ ቀናት በተለያዮ የአፋርና የአማራ ከተሞች እየተዘዋወረ ትህነግ በከፈተው ጦርነት በግምባር መስዕዋትነት ለከፈሉ እና እየከፈሉ ለሚገኙ ሀይሎች የምስጋና መርሃ ግብር   እያደረገ ይገኛል።
ትናንት አመሻሹ ላይ በፋኖ እና በህዝቡ ደማቅ የጀግና አቀባበል ኮምቦልቻ የገባው የባልደራስ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት የአማራ ፋኖ በኮምቦልቻ ሰልጣኞችን በአካል በመገኘት ምስጋናና እና ዕውቅና ሰጥቷል።
በምስጋና መርሃ ግብሩ ላይ የልዑካን ቡድኑ መሪ የሆኑት  አቶ እስክንደር ነጋ “ፋኖ የኢትዮጵያ ጠባቂ ታላቅ ክንድ ነው፤ፋኖ የሚያደርገው ስልጠና እና ጦርነት ለፋትህ እና ለኢትዮጵያ እንድነት በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።ይህንን ደግሞ በውጭም በአገር ውስጥም የሚገኝ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሁሉ ሊደገፍና ሊያበረታታ ይገባል።”ብለዋል።
በተጨማሪም “ፋኖ የመንግስት ጠባቂ ሳይሆን የህዝብ ወገንተኛ በመሆኑ እንኮራለን።”ሲሉ ገልፀዋል።
በሰመራ(አፋር) በባህር ዳር፣ በሰሜን እና ደቡብ ጎንደር ፣ በወሎ(በወልድያ፣ደሴና ኮምቦልቻ) በመገኘት ህዝባዊ ሃይሉን/ፋኖ/ እና ሌሎች ሃይላትን በማመስገን ፣እንዲሁም በወራሪው ሃይል ሀብት ንብረት የወደመባቸውን እና የህይዎት  መስዕዋትነት የከፈሉትን ሁሉ ሲያፅናና የሰነበተው የባልደራስ ልዑክ በዛሬው እለት ወደ ሸዋ አቅንቷል።
Filed in: Amharic