>

አስመሳይ የአማራ እና የአንድነት  ሀይሎች ሰሞኑን ምነው ጡጦዉን እንደቀሙት ህጻን ተንጫጩ...??? (ሸንቁጥ አየለ)

አስመሳይ የአማራ እና የአንድነት  ሀይሎች ሰሞኑን ምነው ጡጦዉን እንደቀሙት ህጻን ተንጫጩ…???

ሸንቁጥ አየለ

የምስለኔ ፖለቲካ አራማጆች:-
–በወለጋ ህዝበ አማራ ሲታረድ ዝማ ማለት ብቻ ሳይሆን   ስለ ህዝብ የሚቆረቆሩ ለምን ተጨፈጨፈ ብለዉ ሲናገሩ/ሲጽፉ ዝም በሉ እያሉ ይሳደቡ የነበሩ::ከዚያም ዘለዉ ስለ አማራ ህዝብ የሚጮሁትን  ወደ እስር ቤት መጣል አለባቸዉም ይሉ ነበር:: በወያኔነትም   ይከሷቸዉም   ነበር::
–በምራብ ሸዋ ህዝበ አማራ ሲጨፈጨፍ ዝማ ማለት ብቻ ሳይሆን ስለ ህዝብ የሚቆረቆሩ ለምን ተጨፈጨፈ ብለዉ ሲናገሩ/ሲጽፉ ዝም በሉ እያሉ ይሳደቡ የነበሩ::ከዚያም ዘለዉ ስለ አማራ ህዝብ የሚጮሁትን  ወደ እስር ቤት መጣል አለባቸዉም ይሉ ነበር:: በወያኔነትም   ይከሷቸዉም   ነበር::
–በመተከል አማሮች በገፍ ሲጨፈጨፉ:በግሬደር ሲቀበሩ ዝማ ማለት ብቻ ሳይሆን ዝም በሉ እያሉ ይሳደቡ የነበሩ::ከዚያም ዘለዉ ስለ አማራ ህዝብ የሚጮሁትን ወደ እስር ቤት መጣል አለባቸዉም ይሉ ነበር::በወያኔነትም   ይከሷቸዉም   ነበር::
–አጣዬ ሙሉ ለሙሉ ሲወድም ዝማ ማለት ብቻ ሳይሆን ዝም በሉ እያሉ ይሳደቡ የነበሩ::ከዚያም ዘለዉ ስለ አማራ ህዝብ የሚጮሁትን  ወደ እስር ቤት መጣል አለባቸዉም ይሉ ነበር::በወያኔነትም   ይከሷቸዉም   ነበር::
–በአጣዬ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቅሎ በርሃብ ሲያልቅ አንድ እርዳታ መሰብሰብ አይደለም እርዳታ የመሰብሰቡ ጩህት ኦህዴድ ወዳጃቸዉን ከመልካም እንቅልፉ የሚቀሰቅስባቸዉ እየመሰላቸዉ በጣም ተጨንቀዉ ነበር::
–የኦህዴድን ብልጽግና የሚያስከፋ ንግግርን ሁሉ እግር በግር እየተከታተሉ በአክቲቪስቶቻቸዉ በጋዜጠኞቻቸዉ:በሚዲያቸዉ:በታዋቂ ፖለቲከኞቻቸዉ :በታዋቂ ሰዎቻቸዉ:በአዝማሪዎቻቸዉ እና በተቃዋሚነት ስም በተሰለፉ ሰዎቻቸዉ ሁሉ ያስተባብሉ ነበር::
–ሌላዉ ቀርቶ በርካታ የአማራ ክልል አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ መዉደም እንዳይነገር እና የብልጽግና መንግስት እንዳይወቀስ በማሰብ ደሴ እኮ ለወታደርነት ስትራቴጂካዊም ጠቀሜታም ሆነ ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዉ አነስተኛ ነዉ ብለዉ እስከ ማጣጣልም የተራመዱ ነበሩ::
-አንዳንዶቹም የአማራ ክልል ወደመ እናም በፍጥነት ይገንባልን ማለት በራሱ የአኩራፊነት ፖለቲካ ነዉ እስከ ማለት የሄዱም አሉ::ይሄን ሁሉ የሚል በአማራ ስም የተሰለፈ የአማራ ፖለቲከኛ ነዉ እንግዲህ አሁን ተገልብጦ አቢይ አስከፋን የሚል እዬዬዉን ሰሞኑን የያዘዉ::
——
–ሆኖም የምስለኔ ፖለቲካ አራማጅ የአማራ እና አስመሳይ የአንድነት ሀይሎች ሰሞኑን ጡጦዉን እንደቀሙት ህጻን እየተንጫጩ ነዉ:: አቢይ አህመድ አስቀይሞናል እያሉ ነዉ::
–ለመሆኑስ የኦህዴድ ብልጽግና እስከዛሬ የአማራ ህዝብ ላይ ያደረሰዉ በደል አሁን እያደረሰዉ ካለዉ ያነሰ ነበር?ነዉ ወይስ አሁን አቢይ በድብቅ የቀማቸዉ አሻንጉሊት አለ?
–ለማንኛዉም የምስለኔ ፖለቲካ አራማጅ የአማራ እና አስመሳይ የአንድነት ሀይሎች መነጫነጫቸዉ የእዉነት ከሆነ አቢይ ኦህዴድ ሁኔታዉን አይቶ አሻንጉሊቱን ይመልስላቸዋል::
–ያኔም ወዲያዉ ዝም ማለት ብቻ ሳይሆን መላዉ የአማራን ህዝብ እንዲሁም መላዉ የኢትዮጵያን ህዝብ ዝም በሉ ማለት ይጀምራሉ:: እምቢ ብሎ ተቅዉሞዉን የሚቀጥለዉን ይሳደባሉ::ይታሰርልን ይላሉ::በወያኔነት ይከሱታል::እነሱ የኢትዮጵያም የአማራም ፖለቲካ ወኪል ሆነዉ ስለ አማራም ስለ ኢትዮጵያም ጮክ ብለዉ እየዘመሩ ስለቡራኬ ይናገራሉ::የፖለቲካ ኑፋቄያቸዉን ያጦፉታል::
የምስለኔ ፖለቲካ አራማጅ  ፖለቲከኛ ምኑም አይታመንም::ጡጡዉን ሲሰጡት ይፈነድቃል::ጡጦዉን ሲቀሙት ይነጫነጫል::እሱ የሚጠባት ጡጦ ለሱ አለሙ ነች::
የብዙሃን ህዝብ ህይወትና ህልዉና ለሱ ምኑም ነዉ::ለምሆኑስ የነዚህ የምስለኔ ፖለቲከኞች ጡጦ ምን እንደሆነ እየቆመሩበት ያለዉ ህዝብ ገብቶታል ወይ ብሎ መጠዬቅ ግን ወሳኝ ነዉ::
——-
ለማንኛዉም ህዝብ የፍትህ አምላክ እግዚአብሄር አለዉ::
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት !
Filed in: Amharic