>

ፋኖ ሀገር አደጋ ላይ ስትወድቅ ከአደጋ የሚያድን ነው! ይህ የማይናጋ ጽኑ አቋሙ ነው....!!!"  (አቶ እስክንድር ነጋ)

¨ፋኖ ሀገር አደጋ ላይ ስትወድቅ ከአደጋ የሚያድን ነው! ይህ የማይናጋ ጽኑ አቋሙ ነው….!!!” 
አቶ እስክንድር ነጋ

ጌጥዬ ያለው (ከወልዲያ)
 
*…. ለህወሀቶች ያለኝ መልእክት:- ከጀርባ እየተጨፈጨፍንም ቢሆን፤ ከጀርባ እየተወጋንም ቢሆንም ኢትዮጵያን ማፍረስ አይቻልም ብለን በአንድነት ቆመን እንጠብቃችኋለን…!!!
 
*…. *….. “ሕወሓቶች ‘እናንተ ራያዎች እባካችሁ ተውን’ ይሉን ነበር….!!!!”
ፋኖ ምሬ ወዳጆ
 
“ቁራናችንን ተናንቀን በእጃቸው እንዳይነኩት አድርገናል…….!!!!” 
ሼህ ኢብራሒም ያሲን
የባልደራስ ልዑክ የፋኖን የሥልጠና መርሃ ግብር ጎበኘ
ታጋይ ነኝ እኔ ማንንም ማልፈራ፣
ሕይዎቴን ለአማራ ስጋዬን ለአሞራ፤
ፋኖ ነኝ እኔ ማንንም ማልፈራ፣
ሕይዎቴን ለአማራ ስጋዬን ለአሞራ።
ባለፈው ጥር 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በአማራና አፋር መስተዳድሮች ጉብኝቱን የጀመረው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ልዑክ ቡድን ትናንት ጥር 15 ቀን ኮምቦልቻ ከተማ ሲገባ በጀግናው አርበኛ ፋኖ ያሬድ እንግዳው ዕዝ የሚመራው የአማራ ፋኖ በደማቅ ወታደራዊ ስነ ስርዓት ተቀብሎታል። ልዑኩ ለተቀበለው ሕዝብ ትናንት በአደባባይ ላይ የእንኳን ተገናኘን ንግግር ያደረገ ሲሆን ዛሬ ሰኞ ጥር 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ደግሞ በስታዲዮም ተገኝቶ የፋኖን ወታደራዊ ስልጠና ተመልክቷል። በሥልጠናው ከላይ የተፃፈው ስንኝ ከፍ ባለ ድምፅ በሕብረት ተዘምሯል።
የልዑኩ መሪ አቶ እስክንድር ነጋ “እኔ ማን ነን ስል፤ እናንተ የኢትዮጵያ ክንድ ትላላችሁ። ይህ መፈክር መልዕክቱ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ለሚሉትና አማራን በማንነቱ ለሚጨፈጭፉት ነው” ባሉት መሰረት ሞቅ ያለ ስሜት ቀስቃሽ መፈክር መርተዋል።
ከፋኖ ጋር የተገናኙት ለሁለት ጉዳዮች መሆኑን የገለፁት የልዑኩ አባል አቶ ስንታየሁ ቸኮል  “የመጣነው አንደኛ ላለፈው ልናመሰግናችሁ ነው። ሁለተኛ ደግሞ ለመጭው ትግል አይናችሁን ገልጣችሁ እንድትጠብቁ  ልናበረታታችሁ ነው” ብለዋል። ተረኞችና ወያኔ ፋኖን በእጅጉ እንደሚፈሩትም አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል።
“እስከ አሁን በተዘዋወርንባቸው ቦታዎች ሁሉ የሰማነው ወያኔ ፋኖ በተሰለፈበት ግንባር መሰለፍ እንደማይፈልግ ነው።
እኛም የአዲስ አበባ ፋኖዎች ነን። አማራ በታሪኩ ኢትዮጵያን ሲጠብቅ ነው የኖረው። ፋኖም ይሄን ነው እያደረገ ያለው። ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ‘አንድ አማራ’ ብሎ ነው የተሰዋው። #የአሳምነው መንፈስ የእናንተም መንፈስ ነው። እኛም የመንፈሱ ልጆች ነን። ይህ  ኢትዮጵያን የማስቀጠል መንፈስ ነው። እናንተን እናመሰግናችኋለን” ብለዋል።
በኮምቦልቻና አካባቢዋ የሚገኘውን የአማራ ፋኖ የሚመሩት ደጀግናው አርበኛ ፋኖ ያሬድ እንግዳው በበኩላቸው “ገና ምን ሠርተን፤ ምን አድርገን ነው የምታመሰግኑን። የምታመሰግኑበት ቀን ገና ነው። መናገር አልችልም። በተግባር ግን እናሳያችኋለን። ትልቁ የጦር ግንባር ያለው አዲስ አበባ ነው። ባላችሁበት ጠንክሩልን። እስክንድርና ጓደኞቹን ፈጣሪ ይጠብቅልን” ብለዋል።
“በዓለም ሊፈፀም የማይገባውን ግፍ ወያኔ በኮምቦልቻ ላይ ፈፅሟል። አማራ ሀገር ጠባቂ ነው። እናንተም የአባቶቻችሁ ልጆች ናችሁ። ግፈኞች ኢትዮጵያን ለመውረር ሲመጡ ከግፈኞች ጋር አልተባበራችሁም። እንዳውም ተፋልማችሁ መልሳችኋቸዋል” ብለዋል ሌላኛዋ የባልደራስ ልዑክ አባል ወ/ሮ አስቴር ስዩም (ቀለብ)።
“አዲስ አበባ ላይ ምዕመናን ተገርፈዋል። ታስረዋል። ተገድለዋል። ትናንተና ደግሞ ሰንደቅ አላማችንን ከሰዎች ነጥቀው አቃጥለውታል” ያሉት ወ/ሮ አስቴር ትግሉን አንድ ሆኖ ማጠናከር እንደሚጠባ አሳስበዋል።
በተመሳሳይ ሌላኛዋ የልዑኩ አባል ወ/ሪት አስካለ ደምሌ “ወሎ የፍቅር ተምሳሌት ነች። እስላም ክርስቲያኑ ተጋብቶ የሚኖርባት ከተማ ናት። ትናንት ያደረጋችሁት ትርዒት በጣም ደስ የሚል ነው። ይሄን የመሰለ ወኔ ያለው ጀግና ሕዝብ ግን መሪ አልባ ሆኖ መቆየቱ ያሳዝናል” ብለዋል። ሌላኛዋ የልዑኩ ተሳታፊ ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሒም ፋኖ እያደረገ ላለው ትግል አመስግነዋል።
በተጨማሪም አቶ እስክንድር ነጋ
“የሕወሓት መሪዎች ሆይ እዚህ ያለው መንግሥት አይደለም። እያሰለጠነ ያለው መንግሥት አይደለም። እየሰለጠነም፤ እያሰለጠነም የሚጠብቃችሁ ሕዝብ ነው” በማለት አሳስበዋል።
“ፋኖ ሀገር አደጋ ላይ ስትወድቅ ከአደጋ የሚያድን ነው። ይህ የማይናጋ አቋም ነው” ያሉት አቶ እስክንድር የያዙትን ሰንደቅ አላማም ለፋኖ በአደራ ሰጥተዋል።
ፋኖ ከወራሪው የትግራይ ሃይል ሕወሓት የሚለይባቸውን ሰባት ነጥቦችም ተንትነዋል። እነርሱም፦
1. ሕወሓት ብሔር ሲል ፋኖ ሰው ማለቱ
2 . ሕወሓት ትግራይ ሲል  ፋኖ ኢትዮጵያ ማለቱ
3. ወያኔ ጦርነት ሲል ፋኖ ፍትሐዊ ጦርነት ማለቱ
4. የትግራይ ወራሪ ጉልበት  ሲል ፋኖ ሕግ ማለቱ
5 . ሕወሓት በቀል   ሲል ፋኖ ፍትሕ ማለቱ
6. ሕወሓት ኢትዮጵያን ልበትን ሲል ፋኖ ኢትዮጵያን ልሰብስብ ማለቱ
7. የትግራይ ወራሪ ጥላቻ ሲል ፋኖ ፍቅር ማለቱ ናቸው።
የባልደራስ ልዑክ ቡድን በሸዋ ጉብኝቱን ይቀጥላል።
“እውነተኛውን የአድዋ አይነት ትግል  እየታገላችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ….!!!”
 እስክንድር ነጋ
*….. “ሕወሓቶች ‘እናንተ ራያዎች እባካችሁ ተውን’ ይሉን ነበር….!!!!”
ፋኖ ምሬ ወዳጆ
ቁራናችንን ተናንቀን በእጃቸው እንዳይነኩት አድርገናል…….!!!!” 
ሼህ ኢብራሒም ያሲን
#የመርሳ ሕዝብ አስቸኳይ የዕለት ደራሽ እርዳታ ይፈልጋል! 
በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ልዑክ ቡድን ወልዲያ ከተማ ገብቷል። በዚህም አሳምነው ፅጌ የምስራቅ አማራ ፋኖ አቀባበል አድርጎለታል። ከወልዲያ በ65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አሁንም ከትግራይ ወራሪ ቡድን ጋር ተፋጠው እንደሚገኙ የገለፁት አሳምነው ፅጌ የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪ አርበኛ ምሬ  “ኢትዮጵያ ማፍረስ የሚፈልጉ አካላት ጦርነቱ አልቋል ቢሉም አላለቀም” ብለዋል።
የባልደራስ ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ ፋኖ ጉዳዩ አገር የማዳን አጀንዳ በመሆኑ ኢትዮጵያን ወክለው መገኘታቸውን ገልፀው
“ቴዎድሮስ ከደርቡሾች ጋር የታገለውን ትግል እየታገላችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ። የአድዋን ትግል እየታገላችሁ ያላችሁት ክናንተ ናችሁ። የእኛ ትግል ከእናንተ ጋር ሲነፃፀር ኢመንት ነው” ብለዋል።
“አንዳዶች ሕወሓት የሚዋጋው ተመልሶ ስልጣን ለመያዝ ይመስላቸዋል። እርሱ ቢሆን ኖሩ ችግሩ ቀላል ነበር። ኢትዮጵያን እንደ ዘመነ መሳፍንቱ ጊዜ ለመበታተን ነው። ኢትዮጵያን እንደ ዩጎዝላቪያ ለማድረግ ነው። ይህ ፈረንጆች ‘ቦልካናይዜሽን’ የሚሉት ነው” ሲሉም ጨምረዋል።
አቶ እስክንድር
“ፋኖ ዛሬ የተፈጠረ አይደለም። በታሪካችን ያለ ነው። ባዶ እጃችሁን ወጥታችሁ ራሳችሁን ያስታጠቃችሁ ጀግኖች ናችሁ” በማለትም አመስግነዋል።
ፋኖ ምሬ ወዳጆ በበኩላቸው
“ሕወሓቶች ‘እባካችሁ እናንተ ራያዎች አሁን እንኳን ተውን’ እያሉን ነው እየተከታተልን ያስለቀቅናቸው። በየቦታው ተሰንክለው ተሰንክለው ቆስለው ያሉ የሰራዊት አባሎቻችንን እንኳን ቦታ ማስያዝ አልቻልንም። ለተሰውት እርም ማውጣት አልቻልንም። ሚስቶቻቸው እና እናቶቻቸው ‘ሞተው እንደሆነ ንገሩን’ እያሉን ከእነሱ ጋር ቁጭ ብለን መነጋገር አልቻልንም። አሁንም እዚያው ግንባር ተፋጠን ነው ያለነው” ብለዋል።
የፋኖን ጀግንነት መንግሥት ራሱ የመሰከረ ሲሆን ዲሽቃ እንደሰጣቸውም ተናግረዋል።  ዋጃ ላይ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀድመው የወያኔን አርማ ነቅለው የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ያውለበለበው የአማራ ፋኖ መሆኑን  ፋኖ አበበ ፈንታሁ ገልፀዋል።
“የባልደራስ አመራሮች እንደ ፓርቲ ሳይሆን እንደ ሀገር ሆናችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን። “ዱቄት ሆኗል” እየተባለ አማራውን የማዘናጋት ሥራ ሲሠራ ነበር።  ጦርነቱ አላለቀም። የአማራ ፋኖ አሁንም ጠንክረን ለአገራችን ክብር መውደቅ አለብን። ጠላት ይፈራናል።
ፋኖ ስሙ ብቻ ሜካናይዝድ ነው። ስሙን ብቻ ይፈሩታል። የትግራይ ወራሪ ሃይል የትግራይ ሰራዊት መስርቶ ነው የመጣው። እኛም በአንድ ዕዝ የሚመራ የአማራ ፋኖ ያስፈልገናል” በማለትም አርበኛው ፋኖ አበበ አብራርተዋል።
እስር ቤት እያሉ ፋኖን የሚያመሰግኑበትን ቀን ይናፍቁ እንደነበር የገለፁት የባልደራስ  የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በኩላቸው “ፋኖ ሽፍታ አይደለም። ሀገር ጠባቂ ነው። ፋኖ ዘራፊ አይደለም። በስነ ምግባር የታነፀ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ላይ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ አላማ ያዛችሁ ተብለው የተገደሉ ክርስቲያኖች መኖራቸውን  ያብራሩት አቶ ስንታየሁ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ቀዳሚ ሥራቸው ይህንን መከላከል እንደሆነም ተናግረዋል።
“ይሄ ጦርነት የአማራን ሕዝብ የጥይት ባሩድ እንዲሸተው አድርጓል። ላለፉት 50 ዓመታት ተዘናግቶ ነበር። አሁን ወደ ቀደመ ወታደርነቱ ተመልሷል” በማለትም ገልፀዋል።
አርበኛ ፋኖ ዳንኤል አለሙ የአማራን አንድነት ማስጠበቅና ፋኖን በአንድ ዕዝ መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። “ፋኖ መስለው አማራን ለመከፋፈል የገቡ አማራ መሳይ ባንዳዎች አሉ።  እኛ የሚዋጋልን መድሃኒዓለም ነው። ምሽግ ሰብሮ ለመከላከያ ያስረከበ ነው አሳምነው ፅጌ የምስራቅ አማራ ፋኖ። እኛን ልትከፋፍሉ የምትፈልጉ ሰዎች እናንተ እንደ ጎመን ትወድቃላችሁ እንጂ እኛ አንበታተንም” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
በተመሳሳይ የባልደራስ አመራር አባል የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ስዩም (ቀለብ) ከምንጊዜውም በላይ አንድነትን ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።
  “አገሩ ሲደፈርበት ፋኖ እምቢ ይላል። ሀይማኖቱ ሲደፈርበት ፋኖ እምቢ ይላል። ይህንን ደግሞ ከጥንት ፋኖዎች ከአባቶቻችን ታሪክ ነው የወረስነው። በሰሜኑ ጦርነት የሰራችሁት ጀብዱ ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ነው። ይህ የምስራቅ አማራ ፋኖ የዛሬ ጀብዱውን ወደ ፊትም እንደሚያስቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ” በማለትም ተናግረዋል።
“እስራኤሎች አንድ እስራኤል ለሁሉም እስራኤል እንደሚሉት እኛም አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ መሥራት አለብን። ሁሉም አማራ ደግሞ ፋኖ መሆኖን አለበት” ብለዋል ወ/ሮ አስቴር ስዩም።
የባልደራስ የሴቶች አደረጃጀት ሓለፊዋ ወ/ሪት አስካለ ደምሌ እና የፓርቲው የገንዘብ አስተዳድር ዘርፍ ሓላፊዋ ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሒም ፋኖ ኢትዮጵያን ጠብቆ ስላቆየ አመስግነዋል። እስር ቤት በነበሩበት ጊዜም ስለ ፋኖ ጀግንነት   ያስቡ እንደነበር ወ/ሪት አስካለ ገልፀዋል።
በመጨረሻም አቶ እስክንድር ነጋ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ሁለት ዓይነት ችግሮች እንደገጠሟት ተንትነዋል። እንደ እሳቸው አገላለፅ አንድኛው ውስጣዊ የፖለቲካ ችግር ሲሆን ሁለተኛውና እጅግ አደገኛው ደግሞ ሕወሓትና ኦነግ ሸኔ የያዙት ኢትዮጵያን እንደ ዩጎዝላቪያ የመበታተን ችግር ነው።
 “የፖለቲካ ችግሩ ስንታየሁ እንዳለው ባንዴራ አትያዙ የሚለው አይነት የፖለቲካ ክልከላና ግድያ ነው። ሌላኛውና ዋነኛው ችግር ግን አሁን ኦነግ ሸኔ እና ሕወሓት የያዙት ሀገር የማፍረስ እንቅስቃሴ ነው። ለዚህ ሁላችንም በአንድነት እንደ አንድ ሕዝብ መቆም አለብን” በማለትም አሳስበዋል።
ባለፉት መቶ አመታት በዚህ ችግር ያለፉ ሀገራት መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ እስክንድር ለአብነትም ናይጀሪያን ጠቅሰዋል። ናይጀሪያ ላይ የባይፍራ የመገንጠል እንቅስቃሴ አገሪቱን አደጋ ላይ ጥሏት ነበር። ዛሬ ግን ያን ችግር አልፈው አሁን ስለዴሞከሰራሲ ነው የሚነገገሩት።
የትግራይ ወራሪ ሃይል አዲስ አበባ ገብቶ ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ ልትበታተን እንደምትችል የገለፁት አቶ እስክንድር ከዚህ ከባድ አደጋ በመታደጋቸው የአማራ ፋኖን ኮፍያቸውን አውልቀውና ዝቅ ብለው አመስግነዋል።
*  *  *
ለህወሀቶች ያለኝ መልእክት:- 
ከጀርባ እየተጨፈጨፍንም ቢሆን፤ ከጀርባ እየተወጋንም ቢሆንም ኢትዮጵያን ማፍረስ አይቻልም ብለን በአንድነት ቆመን እንጠብቃችኋለን…!!!
Filed in: Amharic