>
10:02 am - Tuesday March 21, 2023

የአፋር እና የአማራን ሕዝብ ቀብድ አስይዞ መግባባት ሊኖር አይችልም...!!!  ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ

የአፋር እና የአማራን ሕዝብ ቀብድ አስይዞ መግባባት ሊኖር አይችልም…!!! 
ዶ/ር ኮንቴ ሙሳ

ወንደሰን ተክሉ

 
– የአፋር ህዝብ የትግራይን ህዝብ ችግር፣ የናቶችን ህመምና ሀዘን ይጋራል!
–  አፋርና አማራ ተመሳሳይ ግፍና በደል በወያኔ የማንአለብኝ ወረራ ደርሶበታልና!
– ወያኔ ለፌደራሊዝም ቆሜያለሁ እያለ የፌደራሊዝም ሙሶሶ የሆኑትን መስፈርቶች እያፈረሰ ይገኛል!
የአፋር ህዝብና ክልል ለትግራይ የመጀመርያ ሰብአዊ እርዳታ ካደረጉ ክልሎች ግንባር ቀደም ነበር። ይህ ሆኖ ሳለ ወያኔ የአፋርን ክልል በመውረር፣ የአፋርን ሰንደቅ አውርዶ በትግራይ ተካው። በጋሊኮማ፣ በዲግዲጋ፣ በሲፍራ፣ በደርሳጊታ፣ በዳሌፋጌ፣ በበራህሌ፣ ሀዳሌ ኤላና በተለያዩ የአፋር ከተሞች ያድልተዘገቡ ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋና ውድመት አድርሷል። የአፋር ህዝብ በወያኔ የደረሰበት በደል ተዘርዝሮ ባያልቅም አንድም ቀን ለትግራይ ህዝብ የሚገባውን እርዳታ አላስቆመም፤ ፍላጎቱም የለዉሞ። ወያኔ ግን ለትግራይ ህዝብ ቆሜአለሁ እያለ የትግራይን ወጣት እየማገደ እርድታም እንዳይገባለትና መንገዶች እንዲዘጉ ፤ ክዚያም የዓለም አቀፉ ጫና ተጠናክሮ ወደ ድርድር በመምጣት የሰልጣን መጋራት ፍላጎት ያለው ይመስላል።
የኢትጵያ መንግስትም ጦርንቱ አልቋል ካለን የሰንበትም ቢሆንም ላለፉት አራት ሳምንታት ወያኔ የሰባዊ እርዳታ መግቢያ የሆነችውን አብዓላን በመውረር ተመሳሳይ ውድመትና የጭካኔ ተግባሩን ቀጠሏል።
አብዓላም ከርቀት በሚተኮስ ከባድ መሳርያ ሰውአልባ ሆናለች፣ ህጻናትና አዛውንቶች በግፍ ተገድለዋል፤ የተፈናቃይ ቁጥርም ከቀን ወደቀን እያደገ በመቶ ሺህዎች ይቆጠራል። አሁንም በመጋሌና አካባቢዎች ወረራና ግድያውና ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። አፋርም ጦርነቱን ብቻዉን እያስተናገደ ሲሆን የፖለቲካ ጫወታ ሰለባ የሆነ ይመስላል። የአፋር ህዝብ ለሃገር ብሎ የከፈለው ዋጋ ሌላ ተጨማሪ ዋጋ ልያስከፍለው ይገባል ወይ?
የሁሉም ጦርነቶችና ግጭቶች መቋጫቸው ሰላም መሆኑ ቢታወቅም የሰላም ፍላጎቱ ግን በተፋላሚ ሃይሎች የጋራ ፍላጎትና የዜጎችን ጥቅም ያገናዘበ መሆን አላበት። እንቆቅልሽ የሚመስለው ግን ወያኔ ጦርነቱን ሳያቆም ሰላም እፈልጋለሁ ማለቱና የኢትዮጳ መንግስት በአፋርና በአማራ ጦርነት እየትካሄደ ሳለ ጦርነቱ በድል ተጠናቋል ማለቱ ነው። አፋሮች ሲተርቱ “ግመልህን ከሰረቀህ ሰው ጋር ፍለጋ ከሄድክ ግመልህን መቸም አታገኛትም” ይላሉ። የሀገራችን ፓለቲካም ይህን እየመሰለ በመሄዱ ብዙዎች ግራ ተጋብተናል።
ወያኔ ለፌደራሊዝም ቆሜያለሁ እያለ የፌደራሊዝም ሙሶሶ የሆኑትን መስፈርቶች እያፈረሰ ይገኛል። ይሄውም ሌላ ክልል በመውረርና የክልሎቹን ሰንደቅ በማውረድ የራሱን ሰንደቅ በወረራቸው የአጎራባች ክልሎች መስቀሉ ጦርነቱ የወረራ እንጂ የራስን መብት ለማስከበር እንዳልሆነ በጉልህ ታይቷል። ካልተመለሱ ጥያቄዎች መካከል የእርዳታ መግቢያ መንገድ ሳይዘጋ ወያኔ አፋርን ለምን ወረረ፟? የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግስት በአፋር የሚካሄደውን ጦርነት ለምን ጆሮ ዳባ ልበስ አለው? ተደራደሩ እያለ የሚወተዉተው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የወያኔን ወረራና ዉድመትን ለምን ዝም አለ?
እውነትን ዛሬ በጥሬው ካልተናገርን እስካሁን የተከፈለውን የህይወትና የንብረት ዋጋ ከማራከስ ባሻገር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ስጋት ላይ ይጥላል።  የውጭ ጣልቃ ገብነትና የእጅ ጥምዘዛ ካለ በግልጽ  ይነገረን አብረን እንታገለዋለን እይታገልንም ነው።  ለማንኛዉም አፋርንና አማራን ቀብድ አሲይዞ የሚመጣ ሰላምና መግባባት ሊኖር አይችልምና ልብ ያለ ልብ ይበል።
Filed in: Amharic