>

• ይህቺ ባንዲራ...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ይህቺ ባንዲራ…!!!

ዘመድኩን በቀለ
“…ሰሞኑን ነው ከንቲባ አዳነች አቢቤ በምትመራው ከተማ በወይብላ ማርያም ይህን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ የለበሱ፣ በእጃቸው የያዙ፣ ያውለበልቡ ኦርቶዶክሳውያን በኦሮሚያ እና በፌደራሉ ኃይል በጥይት ተመተው ቆስለዋል። ተገድለዋል። ታቦታቱም፣ ካህናትና ምእመናኑም የተንገላቱት። ነጠላ፣ ሻርፕ፣ ስካርፍ፣ በአንገት የሚጠለቅ፣ በእጅና በግንባር የሚታሰር ሰንደቅ ዓላማ በሙሉ ከምእመናኑ ላይ ተገፍፎ፣ ተቀምቶ የተቃጠለውም። ይህቺ ሴት አስቀድማ በምታዘው በፖሊስ ተቋሟ በኩል ባስነገረችው ዐዋጅ ምክንያት ነበር።
“…ዛሬ ግን እንዲህ ሆነ። በሕይወት ዘመኑ አንድም ቀን ኢትዮጵያ ብሎ ዘፍኖ ሰምቼ የማላውቀው፣ (ዹፌን ሲላላ፣ ዹፌን ሲላላ፣ ቢየኮ ዹፌን ሲላላ የሚለው¨ ለኢትዮጵያ ከሆነ እንጃ) አንጋፋው የኦሮሞ አዝማሪ አሊ ቢራ (ዶ/ር) ታሞ መዳኑን ምክንያት በማድረግ ቤቱ ለጥየቃ የሄደችው ከንቲባ አዳነች አቢቤ በአርቲስቱ ቤት ያላሰበችው፣ ይኖራልም ብላ ያልጠበቀችው ስጦታ ተበርክቶላታል። ስጦታውም የዚህች የመከረኛ ብዙ የኦሮሞ ልጆች ሞተው ያስከበሯትና በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ያጌጠ ስጦታ ነበር።
“…በቀጣዩ ፎቶ አዝማሪ አሊ ቢራ እየሳማት የፎቶ ቦለጢቃ ለመሥራት የሞከረችው ከንቲባዋ ብስጭቷን ፊቷ ላይ ለመደበቅ የቻለች አይመስልም። አሊ ቢራ ቤት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ምን ሊሠራ ገባ? የምትል ይመስላል። ስጦታዋን ይዛ ወደ ቤቷም ወደ ቢሮዋም የምትመለስ አይመስለኝም። ቄሮዎቿ ያቃጥሉት ዘንድ የምትሰጣቸው ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊነት ግን መንፈስ ነው። በግድ ኦሮሞ ነህ፣ ትግሬም ብቻ ነህ ብለህ የግብፅና የቬትናም ባንዲራ ሰፍተህ ብታለብሰውም ኢትዮጵያዊነቱን ልታከስመው ግን አይቻልህም።
• ማርያምን ኢትዮጵያዊነትማ ያቸንፋል  ‼
“…የሞቱትን ነፍስ ይማርልን ‼
Filed in: Amharic