>

ድርድር በሁለት አይነት መልኩ ሊካሄድ ይችላል!!! ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው

ድርድር በሁለት አይነት መልኩ ሊካሄድ ይችላል!!!
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋው

 

1ኛ፦ ተደራዳሪዎችና የተስማሙበት አደራዳሪ ፊት ለፊት ተገናኝተው ድርድር ሊያካሂዱ ይችላል።
2ኛ፦ ተደራዳሪዎች ፊት ለፊት ሳይገናኙ በተስማሙበት አደራዳሪ በኩል ሊካሄድ ይችላል።
***
ይህን ከግምት በማስገባት የአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያን ጉዳይ እንዲፈቱ ወይም ተፋላሚዎቹ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ የሚያስችለውን ጥረት እንዲያደርጉ የቀድሞውን የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆን ሲሾም በፌደራል መንግስትም ሆነ በህውሃት በኩል አልተቃወሙም ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ግዜ የአፍሪካ ህብረት ሹሙን በመቀበል ለጥረቱ በጎ ምላሽ ሲሰጡ ታይቷል። ይህ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ መድረስን አላማው ያደረገ በ3ኛ ወገን በኩል የሚደረግ ድርድር ይባላል።
***
በቅርብ ግዜ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አቶንዮ ጉቴሬዝ ከኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ጋር ተገናኝተው ሁለቱ ተፋላሚዎች የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ የሚደረሱበት ሁኔታ ተስፋ ሰጪ ደረጃ ላይ መድረሱን መረዳታቸውን በሚመለከት (በቀጥታም ባይሆን) መግለፃቸው ሲደመር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ ከዲያስፖራ ተወካዮች ጋር በነበረና 5 ሰዐታትን በፈጀ ቆይታቸው ከትግራይ ኃይሎች ጋር ድርድር ሊኖር እንደሚችል መጠቆማቸውና መረጃው በተዘዋዋሪ ለህዝብ እንዲደርስ መደረጉ ድርድሩ የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ በመድረስ ሊጠናቀቅ የሚችልበት ዕድልና ግዜ መስፋቱንና መቃረቡን የሚጠቁሙ ናቸው። ስምምነቱ ላይ ሲደርሱ የምትሰማውና የምታየው ተኩስ ይቆማል የሚል ተስፋ አለ።
Filed in: Amharic