>

የ16ኛው ክፍለዘመን ግራኝ አህመድና የ21ኛው ክፍለዘመን አቢይ አህመድ ተመሳሳይነት ብቻ ሳይሆን ፍጹማዊ አንድነት ሲገለጥ!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

የ16ኛው ክፍለዘመን ግራኝ አህመድና የ21ኛው ክፍለዘመን አቢይ አህመድ ተመሳሳይነት ብቻ ሳይሆን ፍጹማዊ አንድነት ሲገለጥ!!!
 ወንድወሰን ተክሉ

*…  ሁለቱም ኋይሎች – ማለትም አህመድ ግራኝና አቢይ አህመድ ፦
–  ኦርቶዶክስን 
–  የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይን
–  ነገደ አማራን እና ትግሬን
–  የኢትዮጲያን ታሪክና ቅርስን
–  በዘርና በእምነት ተኮር ጭፍጭፋ ምንጠራና ዘርና እምነት ተኮር ማጽዳት ዘመቻ  ሁለቱም ኋይሎች ዓላማዎቻቸውን ለመተግበር የመረጧቸው የመተግበሪያ መንገዶች ፍጹም ተመሳሳይነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
*    *    “
፠ መነሻ፦ የ16ኛው ክፍለዘመኗ ኢትዮጲያ
በ16ኛው ክፍለዘመን የመሀድ ግራኝ -አህመድ አብን አልጋዚ 15 ዓመታት የጭፍጨፋ ዘመን በኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ 41ዓመታት ከፈጀው የ7ኛው ክፍለዘመን ዮዲት ጉዲት ዘመነ ፍዳ በኋላ  የተከሰተ 2ኛው አስቃቂ የፍዳ ዘመን ሆኖ ይጠራል። ኢትዮጲያ ማእከላዊ መንግስት አልባ ሆኗ ባለፈቺበት 72 የመንግስት አልባማነት ዘመን  -ከ1779-1848 ዘመነ መሳፍንት ተብሎ በሚጠራው ዘመን እንኴን በማእከላዊ መንግስት ያለመኖር ወቅት እንኴን ያልተፈጸመና ያልታሰበ አሰቃቂ ጭፍጨፋ በመላ ኦርቶዶክሳዊያን በንጉሳዊያን ቤተሰብና ዘር ላይ፣በጥንታዊ ገዳማት፣በንዋየ ቅዱሳን፣በካህናትና በሀገረ ኢትዮጲያ ታሪካዊ መዛግብትና ቅርሳቅርስ ላይ የተፈጸመው እጅግ ዘግናኝና ኢትጲያን ለብዙ ዓመታት ወደ ኋላ የመለሰ አረመኔነት ነው።ግራኝ አህመድ ከዛሬዋ ሱማሌ ፑንትላንድ (ሀርጌሳ ) ተነስቶ ኢትዮጲያን እስላማዊ አድርጎ የቱርክ ኢምፓየር አካል አድርጎ ለመግዛት በተነሳበትና 15የመከራ ዘመን በፈጀበት ወቅት በዘመኑ ልእለ ኋያል ሀገር በሆነው ኦቶማን ቱርክ ሁለንተናዊ ድጋፍ -ማለትም በጦር መሳሪያ በተዋጊ ሰው ኋይል በገንዘብና በሎጀስቲክስ ድጋፍ እና እንዲሁም በሱማሌና በአረብ ተዋጊዎች ከዛሬዋ ሱማሌ ፑንትላንድ ተነስቶ መጀመሪያ ምስራቃዊውን የኢትዮጲያን ግዛት በመያዝና የየአካባቢውን ገዢዎች በማስገበር ጉልበቱን ካፈረጠመ በኋላ የወረራ አድማሱን በማስፋት ወደ መሀል፣ምእራብ፣ደቡብና ሰሜን ኢትዮጲያ ግዛቶች ድረስ ዘልቆ በመግባት ዘር ጾታና ቀለም ሳይመርጥ በመላ የኦርቶዶክስ እምነት አማኞችና በመላው ነገደ አማራ ተወላጆች ላይ ባሳረፈው ሰይፍ  ከባድ የዘርና እምነት ማጽዳትን ዘመቻን ያለአንዳች ርህራሄ በአረመኔያዊ ጭካኔ ጄኖሳይድ የፈጸመበት ዘመን ነው -ይህ 16ኛው ክፍለዘመን ታሪክ።
ዛሬ እኛ ያለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን ከ16ኛው ጨለማ ክፍለዘመን እጅግ በተለየና በራቀ ሁኔታ ዘመናችን ስልጣኔ ሰብዓዊ መብትና ሰብዓዊ ክብር፣የሰው ልጅ ተፈጥሮ አዊ የሆነው – በነጻነት የፈለገውን የማመን የማመለክ፣ከስፍራ ስፍራ በነጻነት የመንቀሳቀስ፣በነጻነት ሰርቶ ሀብት ንብረት የማፍራት፣በነጻነት እራሱን የመምራትና ብሎም ይመራኛል ብሎ ያመነበትን በነጻነት የመምረጥና ….ወዘተ ዓይነት መብቶች የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አይነተኛ መገለጫ ሆኖ በተመድ፣በአፍሪካ ሕብረት፣በአውሮፓ ሕብረት መተዳደሪያ ቻርተር ላይና በመላው ዓለም ባሉት ከሁለት መቶ በላይ ሉዓላዊ ሀገራት መተዳደሪያ ሕገ መንግስት ላይ ጸድቆ የሰፈረ በሆነበት ወርቃማው የሰው ልጅ ዘመን አቢይ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ ኢትዮጲያን እና ኢትዮጲያዊያንን ወደ 16ኛው ክፍለዘመን ጎትቶ በመመለስ ዜጎችን በእምነታቸው፣በነገዳዊ ማንነታቸው፣በአመለካከታቸውና በእምነታቸው በግፍ ሲጨፈጭፍና ሲያስጨፈጭፍ እነሆ ወደ አራተኛ ዓመቱ እየተዳረሰ ያለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን።
ይህ ማለት ከሁለት ቀን በፊት በእለተ ዓመታዊው የጥምቀት ክብረ በዓል ላይ በቡራዩ ወይብላ ቅድስት ማሪያምን እና የቅዱስ ሚካኤልን ቅዱሳን ጽላታትን ከጥምቀተ ባህር አጅበው ወደ መንበሩ እያደረሱ ባሉ ኦርቶዶክሳዊያን ላይ በኦሮሚያ ልዩ ኋይል በተተኮሰ ገዳይ ጥይት የአራት ኦርቶዶክሳዊያን ሕይወት በሰማእትነት ለመቀጠፍ በመቻሉ 16ኛውን ክፍለ ዘመን በንፅጽሮሽ መልክ የቀረበ ሳይሆን ንፅጽሮሹ ወደ አራተኛ ዓመቱ እየተጔዘ ያለው አቢይ መራሹ መንግስት ዓይነተኛ መገለጫው ኦርቶዶክስን እና ኦርቶዶክሳዊያንን መጨፍጨፍ፣የነገደ አማራ ተወላጆችን መጨፍጨፍና ብሎም የኢትዮጲያን ታሪካዊ ቅርስ የኦርቶዶክስን ቤተ እምነቶችን አገልጋይ ካህናትን እና አምኞችን የማጽዳት ተግባር በመሆኑ ነው ዳግማዊው 16ኛው ክፍለዘመን በአቢይ አህመድ አገዛዝ በሚል ንፅጽሮሻዊ አገላለጽ ላቀርብ የቻልኩት።
፠ የከበበንን ታላቅ አደጋን ቀድሞ አውቆና አይቶ የተረዳው የነቢዩ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ከሁለት ዓመት በፊት ያስጠነቀቀው አንቂ ማስጠንቀቂያ።
« የአማራ ሕዝብ ከ500ዓመታት በፊት ካጋጠመው አደጋ የባሰ አደጋ ላይ ያለ በጠላት የተከበበ ሕዝብ ነው። ይህ ትውልድ እራሱን አደራጅቶ ህልውናውን ካላስቀጠለ ታላቅ ታሪካዊ ስህተት ይፈጽማል …» በማለት በግልጽና ቁልጭ ባለአንቂ ማስጠንቀቂያ ሊያስጠነቅቀን የተገደደበት ዋና ምክንያት ነቢያዊ የእይታ ጸጋን የተጎናጸፈው ጀግናው ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ መንግስታዊ መዋቅሩን የተቆጣጠረውን እና ኢ-መደበኛ በሆነ አደረጃጀት ተደራጅቶ እራሱን ያፈረጠመውን ጣምራ የሆነውን ጸረ ኦርቶዶክሳዊ፣ጸረ ኢትዮጲያዊና ጸረ አማራዊ የሆነውን እና በሰሜን በምእራብና በደቡብ የኢትዮጲያ ክፍል የተነሳውን ኋይል እቅድ ዓለማ እና ዝግጅትን ከሁላችንም በፊት ቀድሞ በማየቱና በማወቁ ያስተጋባው ማንቂያ ሀቅ ነው እንጂ  በምናቡ የፈጠረው ማንቂያ ፕሮፖጋንዳ አይደለም። ለዚህም እንቁ ነገሮችን ቀድሞ የማወቅ ጸጋው ጀግናው እስከመሰዋት ድረስ ያደረሰን ዋጋን በምትክ የለሽ ውድ ህይወቱ የከፈለቕ ሰው ሆኗል።
ወያኔ ወልዲያ ላይ በ2017ቱ ዓመታዊው የጥምቀት ክብረ በዓል ላይ የዛሬው ኦነጋዊው ኦህዴድ በፈጸመው ግፍ እቻ የሆነ ጭፍጨፋን ቅዱሳን ታቦታቱን አጅቦ በሚጋዘው ሕዝበ ምእመን ላይ በከፈተው ተኩስ የ12ዓመት ታዳጊውን ወጣት ዮሴፍን ጨምሮ በርካታ
 ኦርቶዶክሳዊያን ሰማእትነትን ተቀብለው ነበር። ወያኔ ይህንን የ2017ቱን የወልዲያ ጭፍጨፋን የፈጸመቺበት የጥምቀት ክብረበዓል የተከበረበት ሀገራዊ ድባብና ዛሬ ኦህዴድ መራሹ ኦነጋዊው ጸረ ኦርቶዶክስ ኋይል በቡራዩ ወይብላ ቅድስት ማሪያም አማኞች ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ የተፈጸመበት ሀገራዊ ድባብ እጅግና ፍጹም የተለየ ሁኔታ ሆኖ የመገኘቱ ጉዳይ የዘመነ ኦህዴዱን ጭፍጨፋ በቅርጽና ይዘቱ፣ በዓላማውና በመሰረታዊ ግቡ ፍጹም የተለያየና የተራራቀ ሆኖ ያለ መሆኑን በጥልቀት ማስተዋል ይፈልጋል። በነገራችን ላይ ወያኔ ከ2017ቱ በዓለጥምቀት ላይ ከፈጸመቺው ጭፍጨፋ በኋላ ጥምቀትን ዳግመኛ በገዢነት ሳታከብር ከገዢነቷ ተነቅላ የተጣለች ነው የሆነቺው።
የዘንድሮውን በቡራዩ በኦሮሚያ ልዩ ኋይል በኦርቶዴክሳዊያን ላይ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ስንመለከት አራት እጅግ በአፍላ ወጣትነት እድሜ ላይ ያሉ ኦርቶዶክሳዊያን ሰማእትነትን የተቀበሉበት፣በርካቶች ከባድና ቀላል ጉዳት ያደረሰ ድብደባ የተፈጸመባቸውን እና ቅዱሳን ታቦታቱ ወደ መንበራቸው የሚያደርጉትን ጉዞ አቌርጠው ወደ ቀጨኔ መድሃኒያለም ደብር እንዲሸሹ  የተገደዱበትን እርምጃን መንስኤ ስንመለከት ክቡር ሰንደቅ ዓላማ፣የዘማሪያን እና አገልጋዮች አልባሳት ምክንያትት መሆኑ ነው የታየው። አረንጔዴ ቢጫ ቀይ ቀለማትን በተለያየ ቅርጽና ይዘት የለበሰ ማንም ሆነ ማን በግዛታችን ኦሮሚያ እንዲገባ አንፈቅድም በሚል ነው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ልዩ ፖሊስ ኋይል ታቦታቱን አጅቦ በሚጔዘው ሕዝበ ምእመን ላይ  ተኩስ በመክፈት የአራቱን ሰማእታትን ህይወት በግፍ ሊቀጥፍና በርካቶችን ደግሞ ለማቁሰልና በጅምላ አፍሶ ማሰሩን ያየነው።
የውይብላማሪያም ጭፍጨፋ ምን ያሳየናል???
የዘንድሮው የ2022 ዓመታዊው የጥምቀት ክብረበዓል ላይ ኦነጋዊው የኦህዴድ ብልጽግና የፈጸመው ጭፍጨፋ መንስኤያዊው አስኴል፦
👉 ጥንታዊውና ታሪካዊው የኢትዮጲያ ሰንደቅ ዓላማ
👉 በተለያየ ቅርጽና ይዘት የተሰራ ማንኛውም አልባሳትና ጌጣጌጥ ቀለሙ አረንጋዴ ቢጫ ቀይ የሆነ
👉 የኦሮሚያ ግዛት 
👉 የኦርቶዶክስ እምነት….. መሆናቸው ይታያል።  አቢይ አህመድ ቃለ መሀላ ፈጽሞ በትረስልጣኑን ከጨበጠበት ሚያዚያ 24 ቀን 2018 ጀምሮ የኢትዮጲያ ሰንደቅ ዓላማ፣አረንጔዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት፣የኦርቶዶክስ እምነት ቤተክርስቲያናት፣የኦርቶዶክስ እምነት አጋልጋዮች፣የቤተክርስቲያኒቷ እምነት ተከታይና አማኞች፣የኢትዮጲያ ታሪክ ቅርሶችና የነገደ አማራ ተወላጆች በመላ ኦሮሚያ፣በድሬደዋ፣በቤኒሻንጉልና ጉምዝ፣በሀረሪ፣በሱማሌና በደቡብ ክልሎች እና ብሎም በአዲስ አበባ በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣በግፍ ወድመዋል ተከታታይነት ባለው ዘመቻ ተዘምቶባቸዋል።
ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በ16ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጲያን በካሊፋት የምትገዛ እስላማዊት ሀገር አድርጎ የኦቶማን ቱርክ ኢምፓየር ግዛት ለማድረግ የተነሳውና ለ15ዓመታት ኢትዮጲያን ያወደመው መሀመድ ግራኝ የጭፍጨፋ ሰይፉ ኢላማ ያደረገው ማንን እና የትኛውን የሕብረተሰብ ክፍል ነበር ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው መልስ፦
👉 የኦርቶዶክስ እምነት ተቌማትን፣አቢያተክርስቲያናት ገዳማትንና ንዋየ ቅዱሳናትን- አገልጋይ ቀሳውስትን እና የኦርቶዶክስ እምነት አማኞችን በሙሉ
👉 ጥንታዊውን የኢትዮጲያን ታሪካዊ ቅርሳቅርስ፣ሰንደቅ ዓላማን እና ታሪካዊ መዛግብቶችን
👉 ንጉሳዊ ቤተሰብን እና ንጉሳዊ ዘርን
👉 ከብሄር የአማራና  የትግሬ ነገድን በማንነታቸው እየለየ ለ15 የጨለማ ዓመታት ከባድ ጭፍጨፋና ውድመትን በሀገርና በህዝብ ላይ የፈጸመበትን ጥቁር ዘመን መሆኑን ነው የምናየው።
የ16ኛው ክፍለዘመኑ ግራኝ አህመድና የ21ኛው ክፍለዘመኑ አቢይ አህመድ መራሹ የብልጽግና መንግስት የሚያመሳስላቸው ብቻ ሳይሆን አንድ የሚያደርጋቸው ክስተታዊ ግጥምጥሞሽ ምንድነው ብለን ስንጠይቅ ሁለቱን ተመሳሳይ ብቻ ሳይሆን አንድ የሚያደርጋቸውን ወሳኝ ማንነታዊ መገለጫ ነጥቦችን እንደሚከተለው ማስቀመጥ ይቻላል፦
•1ኛ -የሁለቱን ዋና ዓላማን በተመለከተ፦
👉 ግራኝ አህመድ ጥንታዊውን የኢትዮጲያን ስነመንግስት ታሪክና ኢትዮጲያዊ እምነትን አውድሞና አጥፍቶ ኢትዮጲያን  እስላማዊ በማድረግ የኦቶማን ቱርክ ኢምፓየር እስላማዊ ሀገር የማድረግ
👉 አቢይ አህመድ የኢትዮጲያን ታሪክ ቅርስ፣ስነመንግስትና ጥንታዊቷን ኦርቶዶክስን አውድሞ አክስሞና አጥፍቶ በምትኩም አዲስ ኦሮሞናይዝድ የሆነችን ሀገር በአዲስ ባንዲራ በአዲስ መጠሪያ ስምና በአዲስ መንግስታዊ እምነት አዲስ ሀገረ መንግስት የመፍጠር ዓላማ ያለው መሆኑ የሁለቱን ዋና ዓላማን አንድ መሆን ያሳያል።
• 2ኛ – የ16ኛው ክፍለዘመኑ አህመድ ግራኝ እና የ22ኛው ክፍለ ዘመን አቢይ አህመድ የያዙትን አዲስ ሀገረ መንግስት የመገንባት ዓላማቸውን ለመፈጸም የተጠቀሙበትን ስልት እቅድና ዘመቻን በተመለከተ፦
👉 ሁለቱም ኋይሎች – ማለትም አህመድ ግራኝና አቢይ አህመድ ፦
👉 ኦርቶዶክስን 
👉 የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይን
👉 ነገደ አማራን እና ትግሬን
👉 የኢትዮጲያን ታሪክና ቅርስን
👉 በዘርና በእምነት ተኮር ጭፍጭፋ ምንጠራና ዘርና እምነት ተኮር ማጽዳት ዘመቻ  ሁለቱም ኋይሎች ዓላማዎቻቸውን ለመተግበር የመረጧቸው የመተግበሪያ መንገዶች ፍጹም ተመሳሳይነትን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
• 3ኛ- የ16ኛው ክፍለዘመኑ ግራኝ አህመድና የ22ኛው ክፍለዘመኑ አቢይ አህመድ አጋር አድርገው የመረጧቸውን የውጭ ሀገራትን በተመለከተ፦
👉 የግራኝ አህመድ የጀርባ አጥንት በመሆን የጉልበትና አቅም መሰረት የሆኑት  የኢትዮጲያ ጠላት የሆኑት አረቦች፣ኦቶማን ቱርክና የሱማሌ ተዋጊዎች  መሆናቸው
👉 የአቢይ አህመድ የጀርባ አጥንት በመሆን ጉልበት አቅም ኋይልና የገንዘብ የሎጀስቲክስና የተዋጊ ኋይሎች ምንጭ የሆኑት በኢትዮጲያ ጠላትነቱ ቀንደኛ የሆነውን ኢሳያስ አፈወርቂ፣የሻእቢያና የሱማሌ ወታደር፣የቱርክና የአረብ ሀገራት መንግስታቶች መሆናቸውን ስናይ የሁለቱን ኋይሎች – ማለትም  የግራኝ አህመድና የአቢይ አህመድን በዓላማ፣በአፈጻጸም፣በድጋፍ ምንጭና በአጋር ሀይሎችና ብሎም በሁለቱም ዘንድ በጠላትነት የተፈረጀውን ወገን እና ክፍል ስንመለከት የሁለቱን ኋይሎች ፍጹማዊ ተመሳሳይነት ብቻ ሳይሆን ፍጹማዊ አንድነትን ቁልጭ ብሎ እናያለን።
• መደምደሚያዊ የመፍትሄ ሀሳብ፦
አበው ሲተርቱ የአገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ ይላሉ። አባባሉ ድንቅና ሳይንሳዊ መሰረት ያለውም ስለመሆኑ ብዙዎች ባያስተውሉም ቁሉ ግን የኴንተም ፊዚክስ ትምህርት እያንዳንዱ ችግር የየራሱን መፍትሄን የያዘ ነው በሚል ይገልጸዋል። ዛሬ ያለንበት ሁኔታ በ16ኛው ክፍለዘመኑ ክስተት ጋር ፍጹማዊ ተመሳሳይነትና አንድ መሆን ቁልጭ ብሎ ከታየን የ16ኛ ክፍለዘመኑን አደጋን አባቶቻችን የፈቱበትን እና አክሽፈው ያመከኑበትን ሂደት ስንመለከት የነቢዩ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ ትንቢታዊ ንግግር ቁልፍ መፍሄ ሆኖ ብቅ ሲል ይታየናል።
የአረመኔውንና ግፈኛውን ግራኝ አህመድን ዘመቻ ግብአተ መሬት በማብቃት ደረጃ ከፖርቹጋል የመጡት 400ወታደሮች ግራኝን በመግደል የአንበሳውን ድርሻ የተጫወተ ቢሆንም ለፖርቹጋሎቹ ወታደር ወደ ኢትዮጲያ መጥቶ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ያስቻለው ግን ለ15 ዓመታት ያህል መግዛት የቻለውን  የግራኝ አህመድን ወረራንና ገዢነቱን አንቀበልም በማለት እምቢ ብሎ አምጾ ሲዋጋ የነበረው የአማራው አርበኛ ኋይል መኖር መቻሉ ነው ፖርቹጋሎቹን ጠርቶ ለግራኝ አህመድ ፍጻሜ መንስኤ የሆነው። ይህ ማለት ምን ማለት ነው ስንል የብ/ጄ አሳምነው ጽጌ አማራ እራሱን በማንነቱ ካላደራጀና ካላዘጋጀ ይህ ትውልድ ታሪካዊ ስህተት የሚፈጽም ይሆናል ያለውን ማስጠንቀቂያዊ ማንቂያን ቃል ለዛሬ ችግሮቻችን መፍትሄነቱ እንዳለ ወስደን መተግበር አለብን ማለት ሆኖ እናየዋለን።
በ16ኛው ክፍለዘመን የግራኝ አህመድ ወረራን እንቢ አልቀበልም ሽንፈትንም አልቀበልም ብሎ ያመጸና የታገለ ገዢ ኋይል ባይኖር ኖሮ የፖርቹጋሎችን ድጋፍ የሚጠይቅ ባልኖረና ኢትዮጲያም እስላማዊት የኦርቶማን ቱርክ ግዛት ሆና በተገዘች ነበር። ነገር ግን ያንን ክስተት አክስሞ ያከሸፈው የግራኝን ጊዜያዊ አሸናፊነትን አልቀበልም ብሎ በየጫካውና በየዱሩ እየማሰነ ሲዋጋ የነበረው የአማራ ተዋጊ ክፍል ትልቁን ሚና የተጫወተውን ያህል ዛሬም የአቢይ መራሹን ጸረ ኦርቶዶክስ፣ጸረ አማራና ጸረ ኢትዮጲያን ዘመቻን አክሽፎ ለማክሰም ሙሉ በሙሉ ኋላፊነታዊ ግዴታ የተጣለው በአማራው ላይ ነው። አማራው ይህንን ህልውናዊና ሀገራዊ ታላቅ ኋላፊነትን ለመወጣት ብ/ጄ አሳምነው ጽጌ እንዳለው እራሱን ማደራጀት ማስታጠቅ እምቢ ለአቢይ አልገዛም ማለትና እራሱን አደርጀቶና አጠንክሮ ካልተሰለፈ አይደለም የውጭ ሀይል ድጋፍ ሊያገኝ ይቅርና የሀገር ውስጡንም አማራ ያልሆኑ ኢትዮጲያዊያንን ድጋፍ ፈጽሞ ሊያገኝ አይችልም። አንተ ጠንክረህ ስትበረታና ከራስህም አልፈህ ለሀገር እንደምትበቃ ተስፋ ስታሳይ ያኔ በተስፋፊውና በሰልቃጩ የኦሮሙማ ፖለቲካ ተሰልቅጦ የመዋጥ አደጋ የተጋረጠባቸው በደርዘን የሚቆጠሩ የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦች ተስፋ ሆነህ በመገኘት የሁሉንም ድጋፍ -ከውስጥም ከውጭም – ማግኘት ትችላለህና ትኩረትህ ሙሉ በሙሉ በአንድ የተጠናከረ አማራዊ ኋይል አጠንክሮ ማውጣት ላይ ብቻ ያተኮረ ይሁን–በሚለው መፍትሄያዊ ሀሳብ መጣጥፌን እደመድማለሁ።
Filed in: Amharic