>
5:13 pm - Monday April 19, 9779

ህዉሃት ለኦህዴዶች ካቀረበችዉ መደራደሪያ ነጥቦች አንዱ "  ፋኖ ምቱልኝ!" መሆኑ ታውቋል ...!!! (ሸንቁጥ አየለ)

ህዉሃት ለኦህዴዶች ካቀረበችዉ መደራደሪያ ነጥቦች አንዱ ”  ፋኖ ምቱልኝ!” መሆኑ ታውቋል …!!!
ሸንቁጥ አየለ

*…..ክዛም እያንዳንዱ የብአዴን ባለስልጣን  በህዉሃት እየተሳደደ ይገደላል ወይም ይታሰራል:፤ ኦህዴድም የመጨረሻዉን የፖለቲካ ቁማር ሊበላ ተዘጋጅቷል…!!!
ለኦህዴዶች ህዉሃት ካቀረበችዉ መደራደሪያ አንዱ በአማራ ክልል ያለዉን ፋኖ ምቱልኝ እና እታረቃችኋለሁ የሚል ነዉ::ኦህዴድ ከህዉሃት ጋር ድርድር ላይ ነዉ::
በብልጽግና መንግስት በኩል የአማራ ክልል ፋኖን ለመምታት ብአዴን ዋና ተዋናይ ሆኖ ወጥቷል::
——-
ብአዴን ፋኖን አጠፋለሁ ብሎ ሲነሳ የአማራ ክልል ሙሉ ለሙሉ ሊወድም እና ወደ ጦርነት ቀጣና ሊለወጥ ይችላል::
ከዚያ ብኋላ ህዉሃት የአማራ ክልል የሚባለዉን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥርው ስር ታደርገዋለች::በመጨረሻም እያንዳንዱ የብአዴን ባለስልጣንንም  በህዉሃት እየተሳደደ ይገደላል ወይም ይታሰራል::ኦህዴድም የመጨረሻዉን የፖለቲካ ቁማር ሊበላ ተዘጋጅቷል::
*…..የብልፅግና መኳንንት ያኔ ወያኔ ስታስጨንቃቸው “በእኛ መደበኛ አደረጃጀት ስላልቻልናት ነገ ዛሬ ሳትል፣ቢለዋም ሆነ ቆመጥ ይዘህ ድረስልን”  ያሉትን  ኃይል #ዛሬ አደገኛ ሲሉ ፈርጀው እርምጃ እንደሚወስዱበት እየገለፁ ነው፡፡  
#ይህ ውሳኔ የተላለፈው በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰውን የፋኖ አደረጃጀት ታሳቢ አድርጎ እንደሆነ ለሽመልስ አብዲሳ ካባ ያለበሰው ሰውየ ካወራው መረዳት ይቻላል፡፡ ሰውየው በጣም ያስጨነቀው በአጃቢ ታጅበው የሚሄዱ ሰዎች ጉዳይ እንደሆነ ነው ያወራው፡፡ ጭራሽ ህዝቡ ሊዘርፉት ሰለሚችሉ እነዚህን የሚታጀቡ ሰዎች  እንድናስወግድለት ስሞታ አቅርቧል ብሏል ይህ የክልሉ ፕሬዚደንት በነበረ ጊዜ የአማራን ህዝብ ያለ ተቆርቋሪ ያስቀረ ሃፍረተ ቢስ ሰውየ ፡፡
 የብልፅግናው መንግስት አማራ ክልል ስለሚደረገው እያንዳንዱ ነገር ጆሮውን እንደሚጥለው፣ቀልቡን እንደሚሰበስበው በሌላው የሃገር ጉዳይ ላይ  ጥንቁቅ ቢሆን ኖሮ ሃገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ለማንኛውም  ሰው ስለሆንን ጥያቄ እንጠይቃለን
1. መደበኛው ሃይል ሃገር ማዳን አይችልና ማንኛውም  አካላዊ ቁመናው የሚችል ሁሉ  ይድረስልን ከተባለ ከሶስት ወር አይበልጥም፡፡ ይህ መደበኛ ሃይል ዛሬ ከየት ሰማይ ወርዶ፣እንዴት ብሎ  ባመጣው አቅሙ ሃገር ሊታደግ ነው እንዲህ ያለ ነገር ይዞ ወደ ህዝብ የተመጣው፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ ትልቅ ዝግጅት ስታደርግ ተመጣጣኝ ዝግጅት ሳያደርግ በመቅረቱ እንዝላልነት ህዝብ ያስፈጀው መንግስት ስለጠፋው ነፍስ ሁሉ ተጠያቂ ነው፡፡ ወያኔ ያን ሁሉ ዝግጅት ስታደርግ በነበረበት ወቅት ዛሬ የደህንነት ሹም የሆነው ሰውየ የአማራ ክልል ፕሬዚደንት ነበረ፡፡ ሆኖም ይሄ ሰውየ ተመጣጣኙን ወታደራዊ ዝግጅት ከማድረግ ይልቅ በአማራ ክልል እነማንን እያደነ ሲያሳድድ እንደነበረ ግልፅ ነው፡፡በመሆኑም በአማራ ክልል ለደረሰው ውድመት ሁሉ ዋናው ተጠያቂ ራሱ ነው፡፡ እንጨምር ከተባለ ለጦርነቱ ሲባል ከአማራ ህዝብ በጀት ላይ አንስቶ ሳያስመልስ የአዛዦቹ ጉያ መግባቱም ከተጠያቂነት አያድነውም፡፡
2. ኢመደበኛው አደረጃጀት ላይ እርምጃ እንወስዳለን ማለት በብልፅግና ቋንቋ  “የአገልግሎት ጊዜህ  አልቋልና  ውለታህን በጥፊ በመምታት እመልሳለሁ” ማለት ነው፡፡  የሆነው ሆኖ ይህ ኢመደበኛ የተባለው ሃይል የአገልግሎት ጊዜው እንዳለቀ ተደርጎ የሚወራው ጦርነቱ አልቆ ነው? ከሆነ ወያኔ በአፋር በዚህ ሰዓት ምን እያደረገች ነው?ወይስ ወያኔ አፋር መግባቷን አልሰማንም፣ስንሰማ ደንግጠናል ሊሉ ነው?
3. ወያኔ በአፋር በኩል ጦርነት እንደከፈተች ነገ ደግሞ እንደምትስፋፋ  እኛም እነሱም እናውቃለን፡፡ ይህን በመደበኛ ሃይሉ ለመመከት መንግስት ምን ዝግጅት አድርጓል? ጦርነቱ መቆም አለመቆሙን በተመለከተ እንኳን ሁሉም የመንግስት አካላት ተመሳሳይ ቋንቋ ተጠቅው መልስ ይሰጣሉ? ጦርነቱ ማለቅ አለማለቁን አስረግጦ በአንድ ሃሳብ  ለህዝቡ የማይናገር መንግስት ህዝቡን ከወያኔ ጥይት ይታደጋል ብሎ ለማሰብ ግብረበላ ካድሬ መሆን ያስፈልለጋል፡፡  ህዝቡ ዳግም በወያኔ ጥይት ሲያልቅ እንደ በፊቱ ደጀን ህዝባችን ምናምን እያሉ መሸንገል አይቻልም፡፡
Filed in: Amharic