>

"ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ - ዕጩው የብልፅግና ፓትርያርክ....!!!"  (ዘመድኩን በቀለ)

“ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ – ዕጩው የብልፅግና ፓትርያርክ….!!!” 

ዘመድኩን በቀለ

“…ይሄን ከታች “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ” የሚል ጽሑፍ አዘጋጅታ የለጠፈችው ራሷ የአዲስ አበባ ከተማ ሊቀመንበሯ አዳነች አቢቤ ናት። በእነሱ ቤት ይሄም አጀንዳና ሴራ መሆኑ ነው። አዳነች አቢቢ ራሷን እንደ ጠቅላይ ሚንስትር ቆጥራ የምትንቀሳቀስ፣ ከአቅሟም በላይ የምትንጠራራ፣ በሜካፕ ብዛት ቆዳዋን ቀይ ማድረጓን እንደ እድገት፣ እንደ ብልፅግና የምትቆጥር፣ ሆያ ሆዬ የበዛላት፣ “ከእቴጌ ጣይቱ” ጋር አመሳስለው ሲያወድሷት እውነት የመሰላት፣ ዲፕሎማሲ በደጇ ያልዞረ፣ ከቀበሌ ሊቀመንበርነት ወደ ከተማ አስተዳደርነት ሳታስበው በዐቢይ ፈቃድ የተቀመጠች፣ የሃይማኖት እኩልነት ብሎ ነገር ያልገባት። የምትመራውን ህዝብ የማታውቅ ሴት ናት
“…እነ አህመዲን ጀበል በሁለት መስመር ጦማር የሚያሯሩጧት። ለኦርቶዶክስ ክብር የሌላት። ድፍረቷ ጣሪያ የነካ ሴት ናት። አሊ አብዶም እንዲህ አልናቀን። ቤተ ክህነት አልሄድም ሸራተን ኑ ብላ መኪና መላኳ ሳያንስ፣ በሸራተን ተቀምጣ ፕሮ ካቢኔዋን ሰብስባ ያላገጠችብን ሴት ናት። በሸራተን ባዘጋጀችው የሲኖዶሱ አባላት ወንበር ላይም “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ” የሚለው ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ፎቶ እንዲለጠፍ ያደረገችውም ሆን ብላ ነው። የፕሮወሄው ካቢኔዋ ንቀቱ እዚህ ድረስ ነው።
“…አሁን መንግሥት ያሰበውን በሙሉ በግልጽ እየነገረን ነው። አበው ሆድ ያባውን ጌሾ ያወጣዋል። በልብ የተረፈው በአፍ ይገለጣል እንዲሉ የዐቢይ አሕመድ መንግሥት ያሰበውን ክፉ ሃሳብ በዚህ መልኩ እየገለጠው ነው። ለዚህ ነው የቅዱሳን ፓትሪያርኮቹ ህይወት ያሰጋኛል የምለው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ።
“…ቀሲስ በላይና ዋና ጸሐፊው ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ምን እንደተባባሉ መድኃኔዓለም ይወቅ። አዳነች አቢቤ እኮ ተራ የአንድ ከተማ ሊቀመንበር ናት። 75 ሚልዮን ምእመናን ያሏትና የሃገሪቱን ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ ከምትመራ ቤተ ክርስቲያን ጋር መነፃፀርም የለባትም። ቤተ ክርስቲያኒቱም ከአንዲት የከተማ ሊቀመንበር ጋር ዝቅ ብላ ደጅ መጥናትም አይገባትም። አሳንሰው ለመሣል ከሚሞክሩት ጋር አንሳ መታየትም የለባትም።  እውነት እንነጋገር ሲኖዶሱ ከአዳነች አቢቢ ካቢኔ ጋር አባሮሽ መጫወት፣ የልጅ ዕቃቃ ጨዋታ ከመጫወት ተቆጥቦ ደረጃውን ቢያሳያት ተመራጭ ነው። በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመነጋገር የከተማ ሊቀመንበር ሳይሆን የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ካቢኔ ነው ማውራት መወያየት የሚችለው፣ የሚገባውም። ለዚህ ውርደት የሚያመቻቹን ግን በእኛው ውስጥ ነው የሚገኙት።
“…በጆከሩ ቀሲስ በላይ መኮንን የሚመሩት የኢዜማው የቤተ ክህነት ወኪል ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በመንግሥት የታሰበላቸውን የፕትርክና ማእረግ ከንቲባ አዳነች አቢቤና ካቢኔዋ ከወዲሁ እኛ እንድናውቀው እያለማመዱን ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ የሚጠሩበትን የማዕረግ ስም ለአሜሪካዊው በጠቅላይ ቤተ ክህነት የኢዜማው ሊቀጳጳስ በግልጽ ሰጥተዋቸው በአደባባይ አሳይተውናል። ያውም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሴፍ ብለው።
“…ብፁዕነታቸው በአንድ በኩል የቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ ናቸው። ቦታው ቁልፍ ቦታ ነው። የኢዜማ ወኪል ሚዛን አስጠባቂም ናቸው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይሄ ሁሉ በደል ሲደረሰባት እያዩ የመንግሥቱ ገፅታው እንዳይበላሽ ወጥረው ከያዙት መካከል አንደኛው እኚህ አባት ናቸው። ለውርደታችን ተጠያቂም ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ዋና ጸሐፊው ናቸው።
“…ምልዓተ ጉባኤው እንዳይጠራ አንቀው የያዙትም እኚሁ አባት ናቸው። የሥልጣን ዘመናቸው ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ከአቡነ ያሬድ ጋር ዘንድሮ የሚያበቃ ቢሆንም ምንአልባትም መንግሥት በቦታው ላይ ለተጨማሪ ሦስት ዓመታት ሊያስቀጥላቸውም ይችላል እየተባለም ነው።
“…መናገር እና ማውራት የማይችሉትን፣ በአርምሞ ላይ የሚገኙትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስንም ለርካሽ ፖለቲካዊ ትርፍ ሲሉ በዊልቸር ላይ አስቀምጠው ቤተ መንግሥት ከቢሮ ቢሮ የሚያሰቃዩትም እኚሁ አባት ናቸው። መነጋገር፣ መመካከር፣ መወያየት፣ መጠየቅ፣ መሞገት ካለብን ከራሳችን ነው ቤት ነው መጀመር ያለብን። አንዳንዶች ገመናችንን አደባባይ ባታወጡት ይላሉ። ይሄ ገበና አይደለም። ገበናው ሌላ ነው። እሱ ተከድኖ ይብሰል። ስለሱ የከፋ ቀን ካልመጣ በቀር አሁን የምናወራው አይደለም። ይሄ አስተዳደራዊ አሠራር፣ ቀኖናዊ ጥሰት ለምን ብለን የመጠየቅ አካሄድ ነው። ትናንት እኮ ፌስቡክ ላይ ጫጫታ ባይካሄድ ኖሮ አዋርደውን ነበር። አዳነች በላከችው መኪና ተንጋፈው ሄደው አዋርደው፣ መሳቂያ መሳለቂያ አድርገውን ነበር። የአንዳንድ አባቶች እሪታ፣ የምእመናን ቁጣ ነው ከመሄድ ያስቀራቸው። እና ገመና ሌላ ነው። ገመና እንዲህ ቀላል ነው እንዴ?
“…በአሜሪካ የሚኖሩት አባቶች ባለፈው ኋነጩ ቤተ መንግሥት ገብተው በኢትዮጵያ ጉዳይ ለዐቢይ አሕመድ መንግሥት ጥብቅና ቆመው ሲሞግቱ አይተናል። ያን ያደረጉት ደግሞ አብዛኛዎቹ አሜሪካዊ ዜግነታቸውን ተጠቅመው ነው። ዛሬ በኢትዮጵያ በወለጋ፣ በምዕራብ ሸዋ በሚኖሩ በነገድ ዐማሮች፣ በሃይማኖት ኦርቶዶክሳውያን የሆኑ ካህናትና ምዕመናን ላይ የሞት፣ የስደትና የመፈናቀል ተግባር ሲፈጸም ግን እሊህ ለኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ላይ የተሾሙ አብዛኞቹ በዜግነት አሜሪካውያን የሆኑ አባቶች ግን ደንታም፣ ጉዳይም ሲሰጣቸው አይታዩም። የሀዘን መግለጫ እንኳ አያወጡም። ይሄ ትክክል አይደለም። ሁሉንም ነገር ማውራቱ ለአሁን አይጠቅምም። የሆነ ቀን የበለጠ የከፋ ቀን የመጣ ዕለት፣ ከአቅም በላይ ሆኖ የስሜትን ልጓም መግራት ያልተቻለ ቀን ግን የምንናገረው፣ የምንጠይቀው፣ የምንሞግተውም ነገር ይኖረናል።
“…ለማንኛውም ቅዱሳን ፓትርያርኮቹን በፈጣሪ ጥሪ፣ በተፈጥሮ ሞት እንዲለዩን አጥብቀን እንጸልይ። አሜሪካውያኑ ብፁዓን አባቶቻችን ሆይ ፕሊስ፣ ፕሊስ ተረጋጉ። ይህም ቀን ያልፋልና ተረጋጉ።
“… መልእክቴ ለእነ አዳነች አቢቤ፣ ለብልፅግናው “ዕጩ ፓትርያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ” አቡነ ዮሴፍም ይድረስልኝ። ደግሜ እነግርዎታለሁ። አባታችን አይችሏትምና ከቅድስ ቤተ ክርስቲያን ጋር መታገልዎን ያቁሙ። በጎጃም አጎትዎን ነው ምንዎን የቅባት ጳጳስ አድርገው ጎጃምን ለትርምስ ዳርገው ሄዱ። አሁን ደግሞ ደቡብ ሃዋሳን ወንጌል እንዳይሰበክ፣ አገልግሎቱ እንዳይደምቅ አድርገው ቤተ ክርስቲያንን እጅ እግሯን አስረው በመኔ እንድትደፈር አመቻችተው ሰጡ። ይሄ ሁሉ አልበቃ ብሎ ከቀሲስ በላይ እና ከብልፅግና ሰዎች ጋር ሆነው ቅዱስ የእግዚአብሔር ጉባኤ  ሽባ ለማድረግ አይድፈሩ። የሚሄዱበት መንገድ አግባብ ልክ አይደለም እና በፈጠርዎ ሌላ ሀዘን አይሁኑብን። ይተዉን። ይልቅ ይፍቱን ይባርኩን።
Filed in: Amharic