>

ለእውነት የቆሙትና ስለእውነት የታሰሩት ፓስተር ብንያም ከእስር ተፈቱ...!!! (ወንድወሰን በአሉግርማ)

ለእውነት የቆሙትና ስለእውነት የታሰሩት ፓስተር ብንያም ከእስር ተፈቱ…!!!
ወንድወሰን በአሉግርማ

የመስቀል አደባባይ ህጋዊ ባለቤት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ናት በማለት ለእውነት የቆሙትና ስለእውነት የታሰሩት ፓስተር ብንያም ከእስር ተፈቱ። ለነገሩ ለእውነት የቆመን የእውነት አምላክ የወህኒውን ደጅ ከፍቶ ሰንሰለቱንም ከእግር ፈቶ ነጻ ሲያወጣ አይተናል፤ ዛሬም የሆነው ይህው ነው። እውነት ነጻ ታወጣችኃለች እንዲል ቅዱስ ቃሉ።

እዛ ሆነው፣ እዚህ ላለው እውነት የሚመሰክሩትን ባየ ዓይናችን፣ እዚህ ሆነው ለዚህ የማይመሰክሩትን ማየት ደግሞ ያማል።
የፓስተር ቢንያም ሽታዬ ባለቤት:- የምስጋና እና የደስታ መልእክት።
“በመጀመሪያ ሁሉ ያደረገ እግዚአብሔር ነውና አብዝቼ አመሰግነዋለው። ባለቤቴ ፓስተር ቢንያም ዛሬ ምሽት ከእስር ተፈቷል ።ዘር ቀለም ሀይማኖት ሳይገድባችሁ ከኔም፤ ከልጆቼም ከመላው ቤተሰቤ ጎን የቆማችሁ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ በልዑል እግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ።”
አሜን እንኳን ደስ አለሸ። እናመሰግናለን።
 የተዋህዶ ልጆች እኛ ግን የአባቶችን ትዛዝ በማክበር ትግላችን ድምፃችን ይቀጥላል,,። ስለከፈለልን መስዋዕትነት አመስግኑት እንኳን ደስ አላችሁ በሏቸው።
Filed in: Amharic