>

ግርማዊነታቸው!! ጃ በአለም ከታዩ Mysterious መሪዎችም ዋናው ናቸው። (ምህረት አብ ደስታ)

ግርማዊነታቸው!!

ጃ በአለም ከታዩ Mysterious መሪዎችም ዋናው ናቸው።

ምህረት አብ ደስታ

👉አለም ከፃፈላቸውና ከተናገረላቸው አንፃር እሩቡን እንኳ እኛ አልተናገርንላቸውም። ሰውዬው ህልማቸው ከውቂያኖስ የገዘፈ አስተውሎታቸው ከባህር የጠለቀ ነበር። of course he made a lot of mistakes also
👉ኢትዮጵያ በታሪኳ እንደሳቸው ያለ ተፅእኖ ፈጣሪ መሪ አልነበራትም። እስካሁን እሳቸው ሰው ናቸው አምላክ? በሚል ርእስ ብቻ ከሃምሳ በላይ ትልልቅ ዲቤቶች አለም ላይ ተካሂደዋል።
👉ለአፍሪካ የሰሩት ውለታም ስፍር ቁጥር የለውም። እንደውም ብዙ የፓንአፍሪካኒዝም አቀንቃኞች «before mandela there was hailesilassie» ይላሉ። ያው ጀግና የሚመርጡልን ሌሎች ናቸው እንጂ ሃይለስላሴ ከኩዋሚ ንኩሩማ፣ ከማዲባ፣ ከሮዛ ፓርክስ፣ ከማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየርም በላይ ነበሩ።
👉ነጮቹ ሐገር ሄደው በባርነት ውስጥ ያሉ ጥቁሮችን በመሳሪያ ሳይቀር እንደግፋለን ብለው የሚናገሩ ኩሩና ወኔያም ንጉስ ነበሩን ወገን! በዘመናቸው ታላቋ ብሪታንያን ረድተዋል። ለኮርያ ወታደራዊ ድጋፍ አርገው «አይዟችሁ አንድ ቀን እንደኛ ነፃ ህዝብ ትሆናላችሁ» የሚል ማስተዛዘኛ ቃልም ልከዋል።
👉ለማንዴላ ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ከእንግሊዝ ጋር ተናንቀዋል። ያንን የአፓርታይድ ስርአት ለመንቀል ለሚታገለው ማንዴላ ስልጠና ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊ ዜግነትና በእጁ ይዟት የሚንቀሳቀሰው መሳሪያም አበርክተውለታል። By the way ያቺ መሳሪያ አሁን ያላት ቫልዩ ከአምስት ሚሊዮን ዶላር ያልፋል። ከዚያም አልፈው «Mandela’s Gun» የሚል ፊልም ሁሉ ሰርተዋል።
#መልካም የስራ ሳምንት
Filed in: Amharic