>

የአቶ ርስቱ ይርዳው ንግግር ሆን ተብሎ የተለቀቀ ስለመሆኑና የአማራ ትግል መፍትሔ!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

የአቶ ርስቱ ይርዳው ንግግር ሆን ተብሎ የተለቀቀ ስለመሆኑና የአማራ ትግል መፍትሔ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ተመልሻለሁ ወገኖቸ! ፌስቡክ “በኮሜንት ላይ ተሳድበሀል!” ብሎ ለአንድ ወር የጣለብኝ እገዳ ከደቂቃዎች በፊት ተጠናቆ ነው የተመለስኩት፡፡ “በኮሜንት ላይ ተሳድበሃል!” እያለ ሲያግደኝ ይሄ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ የሚሰድበኝን መሳደብ አልቻልኩም፡፡ እራስን የመከላከል ተፈጥሯዊና ሕጋዊ መብትን ነው ፌስቡክ እየነፈገኝ ያለው፡፡ ጽሑፎቸን ግን በከፈትኩት አዲስ አካውንትና ቴሌግራም ላደርሳቹህ ሞክሬያለሁ፡፡
ወደ ርእሰጉዳዩ ስገባ ሴረኛው፣ አሻጥረኛው፣ ሸፍጠኛው፣ መሠሪው ወያኔ/ኢሕአዴግ እንደለመደው በሕዝብ ዘንድ እንዲናኝ የሚፈልገውን አስተሳሰብና አጀንዳ “በድብቅ ተቀርጾ የወጣ፣ ከውስጥ አዋቂ የተገኘ መረጃ…!” ወዘተረፈ. በሚል ፈሊጥ ሆን ብሎ ያዘጋጀውን የተጭበረበረ መረጃ እያወጣ ማስተዋልና ማገናዘብ ለማይችሉቱ ኤርሚያስ ለገሰና ሀብታሙ አያሌው በማቀበል እንዲናኝ ማድረጉን አሁንም ቀጥሎበታል!!!
ልብ ብላቹህ እንደሆነ ለውጥ ከሚባለው የወያኔ/ኢሕአዴግ ድራማ በፊትም ኢሳት “በድብቅ ተቀርጾ የወጣ፣ ከውስጥ አዋቂ የተገኘ መረጃ!” ምንንትስ ቅብርጥስ እያለ ይለቃቸው የነበሩ መረጃዎችን አገዛዙ ለዚሁ ጉዳይ ከመደባቸው ባለሥልጣናት እየተቀበሉ በኢሳት እንዲናኝ ያደርጉ የነበሩት በዋናነት እነኝህ ሁለት ግለሰቦች ነበሩ፡፡ እነሱ ኢሳትን ሲለቁ ኢሳት የእንደዚህ ዓይነት መረጃዎች ድርቅ አጠቃው ጭራሽም ተደመረና የአገዛዙ ልሳን ሆኖ ቁጭ አለ!!!
በጣም የሚገርመኝ ነገር ወይ እነዚህ ሁለቱ ግለሰቦች አሁንም እያስመሰሉ አገዛዙን የሚያገለግሉ ስለሆኑ እንደሆነ አላውቅም መረጃው ሲሰጣቸው “መረጃው በምሥጢር የወጣ በማስመሰል ሆን ተብሎ  የተለቀቀ ይሆን?” ብለው እራሳቸውን በመጠየቅ ትንሽም ሳይመረምሩ፣ ሳያገናዝቡ፣ ሳያመዛዝኑ የተሰጣቸውን እንዳለ እንደወረደ ለሕዝብ የሚያስተጋቡ መሆናቸው ነው፡፡ ለእነኝህ ግለሰቦች “እከሌ በድብቅ የወጣ መረጃን ይፋ አደረገ!” መባላቸው ብቻ ትልቅ ክብርና ዝና ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ምንም አሳስቡም፡፡ በመረጃው ላይ ማን ቁማር ሊሠራ እንደፈለገ ፈጽሞ አይረዱም!!!
እነኝህ ሁለቱ ግለሰቦች ከወያኔ/ኢሕአዴግ ቤት የመጡ በመሆናቸውና መረጃ የተባለውን ሆን ተብሎ የተዘጋጀና የተጮበረበረ መረጃ የሚያቀብሏቸው ግለሰቦችም የሚያውቋቸው ሰዎች በመሆናቸው አገዛዙ እንዲናኝ የፈለገውን መረጃ ወይም አጀንዳ ተሰርቆ የወጣ አስመስሎ ለእነሱ በማቀበል እንዲናኝ በማድረግ አጀንዳውን ለማስፈጸም በእጅጉ ተመችቶታል!!!
በእነኝህ ግለሰቦች እስከዛሬ “በድብቅ የወጣ!” እየተባለ የወጡ መረጃዎችን መለስ ብላቹህ አሁን ላይ ብትመረምሯቸው መረጃ የተባለው የተጭበረበረ መረጃ አገዛዙ የወቅቱን ፖለቲካዊ ትኩሳት ለማቀዝቀዝ፣ ሕዝቡ ላይ መጫን የፈለገውን አጀንዳ ለመጫን የተጠቀመባቸው ሐሰተኛ መረጃዎች መሆናቸውን ትረዳላቹህ!!!
ለምሳሌ አገዛዙ ለውጥ የሚለውን ድራማ ሕዝብ ላይ ለመተወን ሲያስብ ድራማው ተአማኒነት እንዲያገኝ አስቀድሞ መደላድል ማመቻቸት ስለነበረበት የብአዴንንና የኦሕዴድን ባለሥልጣናት ጀግና ቆራጥና ለሕዝብ አሳቢ የሚያስመስሉ “ገዱ እንዲህ አደረገ፣ ደመቀ እንዲህ አደረገ፣ አምባቸው እንዲህ አደረገ፣ ለማ እንዲህ አደረገ!” ወዘተረፈ. እየተባለ የሚነዛ የፈጠራ ወሬ መንዛት ነበረበትና አስቀድሞ ያንን በሚገባ አድርጓል፡፡ በእነዚያ የፈጠራ ወሬዎች ተመሥርቶም ለውጥ የሚለውን ድራማ በሚገባ ለመተወንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማጃጃል ችሏል!!!
አገዛዙ ኢሳት ላይ በእነ ሀብታሙ አያሌውና በኤርሚያስ ለገሰ አፍ ጀግና አድርጎ ሲያወራላቸው የነበሩ የብአዴን ባለሥልጣናት እነ አቶ ገዱ፣ አቶ ደመቀ፣ አቶ አምባቸው… ያ የተወራላቸው የወያኔ ባለሥልጣናትን ያንበረከከ፣ ያርበደበደና ያባረረ ጀብድ ቆራጥነትና አቅም ግን ማሰብና ማገናዘብ ለሚችል ሰው የፈጠራና ማጃጃያ መሆኑን ለመረዳት ብዙ ጊዜ የጠየቀ አልነበረም!!!
ምክንያቱም ከኢኮኖሚው እስከ ሚሊተሪው የተቆጣጠረውን ክፉውንና ኃይለኛውን ወያኔን “አንበረከኩ፣ አርበደበዱ፣ አባረሩ!” የተባሉት የብአዴን ባለሥልጣናት ምንም በሌለው ኮሳሳው ኦሕዴድ ፊት መቀለጃና መጫወቻ፣ አቅመቢስና ልፍስፍስ፣ በእጅጉ የተናቁና የተዋረዱ ሆነው ታይተዋልና ነው፡፡ እነኝህ የብአዴን ባለሥልጣናት ወያኔን “አንበረከኩ፣ አርበደበዱ፣ አባረሩ!” በተባሉበት አቅም፣ ድፍረትና ጀግንነት ኦሕዴድን ለማንበርከክ መንቀሳቀስ አይደለም ጨርሶ ለማሰብም እንኳ አልሞከሩም፡፡ ለምን ይመስላቹሃል??? ወሬው የፈጠራ በመሆኑና ሁነቱ ድራማ በመሆኑ ነው ሌላ አይደለም!!!
ያኔ እንደ ብአዴን ባለሥልጣናት ሁሉ የፈጠራ የጀብድ ወሬ ወደተወራላቸው የኦሕዴድ ባለሥልጣናትም ነበሩ፡፡ ዋነኛውም ቲም ለማ የሚባለው የለውጡ ሞተር ሆኖ እንዲተውን ገጸ ባሕርይ የተሰጠውን ቡድን መሪው አቶ ለማ መገርሳ ነበር፡፡ አቶ ለማ መገርሳ የሚባል ጀግና ገጸ ባሕርይ የተፈጠረለት እና ገጸ ባሕርይውም የእውነት የመሰለው የኦሮሞ ልኂቃን የስሜት ስካር ውስጥ በመግባት “ጊዜው አሁን ነው!” በሚል ስሜት ጥያቄው ከልክ በላይ እየገዘፈና እየተጋፋ በመምጣቱ ሴረኛው ወያኔ/ኢሕአዴግ ለአቶ ለማ አንዳንድ ስም ማጠልሻ ወሬ ተፈጠረለትና በዚያ ምክንያት አቶ ለማን ለጊዜውም ከትወናው በማውጣት ከልክ በላይ እየገዘፈና እየተጋፋ የመጣውን የኦሮሞን ጥያቄ defuse አደረገው!!!
አቶ ለማ ጠባብነትን ማንጸባረቁ ሊያስጠላው የሚችለው ግን በተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ነው እንጅ በኦሕዴድ አለመሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ወይም ደግሞ አቶ ለማ ጠባብነትን ማንጸባረቁ በኦሕዴድ የበለጠ እንዲወደድ ያደርገዋል እንጅ ሥልጣኑን አጥቶ እንዲገለል የሚያደርገው አለመሆኑን መረዳት የምንችል ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የተፈለገው ነገር ለማን በማግለል ለማን ተመክቶ ፈጦ የመጣውን የኦሮሞ ልኂቃንና ቄሮ ጥያቄ ማቀዝቀዝ ስለሆነ የተፈለገው ብልጠትን በመጠቀም ማለትም አቶ ለማን ከኦሕዴድና አገዛዙ ኦሮሚያ ከሚለው የሀገራችን ክፍል ፕሬዲደንትነት አንሥቶ መከላከያ ሚንስትር በማድረግ ብዙ ሳይቆይም እንዲገለል ተደረገ!!!
ምክንያቱም ኦሕዴድ ጀግናው አድርጎ የሚያስበውን ለማን ሽሮ በኩታራው ሽመልስ ወይም በሌላ ሰው ሊተካ አይችልምና ለማን ለማግለል መጀመሪያ ከፕሬዚደንትነቱ ማምሣት አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህም መንገድ ወይም ዘዴ በቲም ለማ ትወና ስካር ውስጥ ገብቶ ከባባድ ጥያቄ በማንሣት ሥጋት ፈጥሮ የነበረውን የኦሮሞ ልኂቃንንና የቄሮን ተጋፊ ስሜት ማቀዝቀዝ ወይም ማብረድ ቻሉ፡፡ ለወደፊት ኦሮሞ ተቃውሞ የሚያነሣና ንቅናቄ የሚፈጥር ከሆነ ግን ሴረኛው፣ አሻጥረኛው፣ መሠሪው፣ ሸፍጠኛው ወያኔ/ኢሕአዴግ አቶ ለማን መልሶ ያመጣውና ተቃውሞውንና ንቅናቄውን ለመቆጣጠር የሚጠቀምበት ይሆናል፡፡ ለጊዜው ግን እረፍት ላይ ነው፡፡ አገዛዙ ለማ መገርሳን የሚጠቀምበት እንደ ዮሐንስ ቧያለው ነው፡፡ ሁለቱም የሚተውኑት ለየ ሕዝባቸው ተቆርቋሪ መስለው ነው!!!
ታስታውሱ እንደሆነ ወያኔ/ኢሕአዴግ አቶ ዐቢይ አሕመድን ያመጣው መጨረሻ ላይ ነው፡፡ ዐቢይ እነ አቶ ለማ መገርሳ “ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!” የሚል ነጠላ ዜማ ይዘው ባሕርዳር ሲያቀኑ እንኳ በቲም ለማ ውስጥ አቶ ዐቢይ አሕመድ አልነበረም፡፡ አገዛዙ ከኦሕዴድ ውስጥ ሌላ ሰው ፈልጎ ዐቢይን ያመጣበት ምክንያት ለማ የፓርላማ አባል ስላልነበረና ጠ/ሚ ሆኖ ለመሾም የማይችል ስለነበረ ነው፡፡ አቶ ዐቢይ አሕመድ እንደ እነ ለማ መገርሳ እና እንደ እነ ገዱ “እንዲህ አደረገ!” የሚል የጀብድ ወሬም አልተፈጠረለትም ነበር፡፡ ለማ ጠ/ሚ ሆኖ ለመሾም ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ መጨረሻ ላይ ድንገት ነው አቶ ዐቢይን ብቅ ያደረጉት!!!
እናም ሁሉም ነገር የወያኔ/ኢሕአዴግ ድራማ ነበር እንጅ እውነት አልነበረም፡፡ አገዛዙ ይሄ ድራማውን እውነት እንዲመስልና ሕዝብ እንዲጃጃልለት ማድረግ የቻለው የእነ ሀብታሙ አያሌውንና ኤርሚያስ ለገሰን አፍ ተጠቅሞ “በድብቅ ተቀርጾ የወጣ፣ ከውስጥ አዋቂ የተገኘ መረጃ!” ምንንትስ እያለ ለሕዝብ ሲነዛው በነበረው የፈጠራና ሆን ተብሎ ተዘጋጅቶ በሚለቀቅ የተጭበረበረ መረጃው ነው!!!
የሸፍጠኛው ወያኔ/ኢሕአዴግ የስርቆት ልሳን ሆነው በማገልገል ይሄንን ሁሉ ኪሳራ በሀገርና በሕዝብ ላይ ያደረሱት ደናቁርቱ ኤርሚያስ ለገሰና ሀብታሙ አያሌው ይሄው አሁን ደግሞ “ርስቱ ይርዳው ሲናገር በድብቅ የተቀረጸው!” ብለው ንግግሩን ይዘው መጥተዋል፡፡ ንግግሩ ግን በድብቅ የተቀረጸ ሳይሆን በአገዛዙ ትዕዛዝ እራሳቸው የኤምባሲው ሠራተኞች እዚያው ስብሰባው ላይ የቀረጹት ንግግር ነው፡፡ በድብቅ የተቀረጸ በማስመሰል ለኤርሚያስ እንዲደርሰው የተደረገውም እንደተለመደው ሁሉ በራሱ በአገዛዙ ትዕዛዝ ነው፡፡ አቶ ርስቱ ይርዳው ያንን ንግግር እንዲናገር የተደረገውም በራሱ በአገዛዙ ትዕዛዝ ነው!!!
ዓላማው ምን መሰላቹህ በዚህ የአቶ እርስቱ ንግግር በኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሰበሰበውን የጉራጌ ልኂቃን ለማግባባት እንደሞከሩት ሁሉ በኢትዮ 360 በኩል ለጉራጌ ሕዝብ እንዲደርስ በማድረግ ጉራጌን ለማግባባትና ለመውሰድ ነው!!!
በመሠረቱ የጉራጌ ልኂቃን መወላወል ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል፡፡ እርስቱ ይርዳውማ የአገዛዙ ሹም ነው ከዚህ የተለየ ሊያስብ አይችልም፡፡ የጉራጌ ልኂቃን ግን “አማራን በመምሰላችን ብዙ ዋጋ አስከፍሎናል፡፡ አሰላለፋችንን ካልቀየርን ወይም ከአማራ ጋር ካልተፋታን ወደፊትም ከእስከአሁኑ የከፋ ዋጋ ያስከፍለናል!” የሚል አስተሳሰብ እያንሸራሸሩ እንደቆዩ ኢመደበኛ በሆኑ መድረኮችና ማኅበራዊ መስተጋብሮች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እያንሸራሸሩት መምጣታቸውን ስንታዘብ ቆይተናል!!!
በእርግጥ አቶ ርስቱ ይርዳው “የአማራ ፖለቲካ!” ሲል የገለጸው የአማራ ትግል ነገር በእጅጉ ተስፋ አስቆራጭ ነው፡፡ አንዳንድ ዘገምተኞች አቶ ርስቱ የአማራ ፖለቲካ ለራሱ እንደማንሆንና ተስፋ የሚጣልበት እንዳልሆነ የተናገረውን ብአዴንን ማለቱ እንደሆነ አድርገው ተርጉመውታል፡፡ ብአዴንና እነ አቶ ርስቱማ ድሮም ሆነ አሁን ለአንድ ዓላማ የተሰለፉ የሚሠሩና የአንድ ፓርቲ አባላት አይደሉም ወይ??? ስለሆነም አቶ ርስቱ የአማራ ፖለቲካ ሲል የገለጸው “ለአማራ እታገላለሁ!” የሚለውን ክፍል ነው፡፡ ይሄ ክፍል ወይም የአማራ ልኂቅ ደግሞ እንደምታዩት ከዳያስፖራ እስከ ሀገር ውስጥ ድረስ ወያኔ በፀረ አማራ አህያው ብአዴን በኩል እያቄለ እንደፈለገ የሚጫወትበትና የሚቀልድበት ሲበዛ ዘገምተኛ የሆነ የኅብረተሰብ ክፍል ነው፡፡ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከሀገር ውስጥ እስከ ዳያስፖራ ፀረ አማራው የወያኔ/ኦሕዴድ አህያ ብአዴን የማይቆጣጠረውና የማይዘውረው የአማራ ሲቪክና የፖለቲካ አደረጃጀት አንድ እንኳ ለምልክት የለም!!! እንዲህ መጫወቻና መቀለጃ የሆነው የአማራ ልኂቃን ነቅቶና የጠላትን ወጥመድ በጣጥሶ ሕዝቡን በማታገል ለነጻነት ያበቃል ብሎ ማሰብ እጅግ ሲበዛ ሞኝነት ነው!!!
በተደጋጋሚ ነግሬያቹሃለሁ አማራ ከአገዛዙ ዝወራ ወይም ሰርጎገብነት ነጻ ሆኖ ትክክለኛ ትግል ሊያደርግ የሚችልበት የመርፌ ቀዳዳ ታክል እንኳ ዕድል ወይም ክፍተት የለም!!! ይሄንን ለማረጋገጥ ጠላት ምንም የሚቆጥበው ነገር የለም!!! ሁሌም ቢሆን የጠላት ሁለት ዓይኖች አማራ ላይ የተተከሉ ናቸው፡፡ ለሰከንድ እንኳ ተነቅለው አያውቁም፡፡ ይሄንን በመረዳትም ነው እኔ በተደጋጋሚ “ከሕዝባዊ ዐመፅ ውጭ አማራን ከወያኔ/ኢሕአዴግ አገዛዝ ሊገላግለው የሚችል ሌላ ምንም ዕድል የለም!” የምለው!!!
በእርግጥ ትግል የሚደረገው ምቹ ሁኔታ አለ ተብሎ አይደለም፡፡ ትግል የሚደረገው የሌለን ነገር እንዲኖር ለማድረግ፣ የተነጠቅነውንና የተነፈግነውን ነገር ለማግኘት በመሆኑ ምቹ ሁኔታ አለ የለም ተብሎ አይደለም የሚደረገው ምቹ ሁኔታ በሌለበትም የግድ ይደረጋል እንጅ፡፡ እኛን የገጠመን ነገር ግን ምቹ ሁኔታ አለመኖር ብቻ ሳይሆን አስቻይ ሁኔታም ጨርሶ እንዳይኖረን ነው የተደረገው፡፡ ለምሳሌ በወያኔና ሸአቢያ የትጥቅ ትግል ወቅት ወያኔና ሸአቢያ በደርግ ሠራዊት ላይ ጥቃት ፈጽመው ሲያበቁ ሔደው የሚሸሸጉበትና ታጣቂዎቻቸውን የሚያሠለጥኑበት ተገንና ካምፕ እኛ ከሱዳንም ሆነ ከየትኛውም ጎረቤት ሀገር ልናገኝ አንችልም፡፡ ለወያኔና ሸአቢያ የስንቅና ትጥቅ እንዲሁም የintelligence ድጋፍ ይሰጡ የነበሩ ሀገራት ለእኛ ፈጽሞ የሚሰጡ አይደሉም ወዘተረፈ. ሕዝባችን ይሄ ወያኔና ሸአቢያ ያገኙት ዕድል ቢኖረው ወያኔ የፈጀበትን 17 ዓመት፣ ሸአቢያ የፈጀበትን ሰላሣ ዓመት አይደለም መንፈቅ እንኳ ባልፈጀበት ነበር!!!
በመሆኑም አማራ ተደራጅቶ ለመታገልና ለድል ለመብቃት የሚያስችል ምንም ዓይነት ክፍተት አልተተወለትምና መሥራት ካለብን ሕዝቡ እንዲያምፅ እንጅ ተደራጅቶ እንዲታገል ለማድረግ መሆን የለበትም፡፡ ምክንያቱም አንደኛ የተጋፈጠው የህልውና አደጋ ጊዜ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ሁለተኛ ጠላት አማራ ተደራጅቶ ለውጥ ሊያመጣ የሚችልበትን ቀዳዳ ሁሉ ፍጹም ዝግ ስላደረገው ወይም ጠላት የፈጠረው ነባራዊ ሁኔታ ተደራጅቶ በመታገል ለውጥ ለማምጣት ስለማይፈቅድ ነው፡፡ እንደምታውቁት “አማራ ተደራጀ!” ከተባለ ወይ ያ አደረጃጀት የአማራን ሕዝብ ፍላጎት በመገንዘብ በጠላት የተፈጠረ የውሸት ወይም የጠላት አደረጃጀት ሆኖ ይገኝና አደረጃጀቱ የአማራ ውድ ልጆች የሚበሉበት የማጥመጃ አደረጃጀት ይሆናል ወይ ደግሞ  ወደዚህ አደረጃጀት ጠላት ቅጥረኞቹን አስርጎ ያስገባና አደረጃጀቱን ወዲያው በቁጥጥሩ ስር በማድረግ ለአማራ የቆመ መስሎ እየተወነ እንዲኖርና ሕዝባችንን እያጃጃለ እንዲኖር ያደርገዋል፡፡ አማራ የሚፈጥረው አደረጃጀት ከሁለቱ ውጭ የሆነ ዕጣ ፋንታ የለውም፡፡ እንዲህ በሆነበት ሁኔታ ብቸኛው አማራጭ የሚሆነው ምድር አንቀጥቅጥ የሆነና የማይመለስ ወይም የማይቀለበስ ዐመፅና ዐመፅ ብቻ ነው!!!
ሕዝባችን በቅጥረኛ የአማራ አደረጃጀቶች እየተታለለ ተደራጅቶ መታገልና ለውጥ ማምጣት የሚችልበት ምኅዳር ያለ ስለመሰለው ነው እንጅ ሁኔታው ከላይ የገለጽኩትን ያህል ተስፋ አስቆራጭና ተደራጅቶ ለመታገልና ለውጥ ለማምጣት ፈጽሞ እንዳልተፈቀደለት፣ የተተወለት ብቸኛው አማራጭ ሞት ብቻ መሆኑን ቢያውቅ ኖሮ መደራጀት ሳያስፈልገው በግብታዊ ዐመፅ ለውጥ ማምጣቱን ያውቅበት ነበር፡፡ ነገር ግን እነ ፀረ አማራው ብአዴን፣ ቡችላው አብን እና ሌሎች ከዳያስፖራ እስከ ሀገር ውስጥ ያሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በብአዴን የሚዘወሩ ቅጥረኛ የአማራ አደረጃጀቶች እያሉ አማራ በየት በኩል ለዚህ ይበቃል???
እናም አቶ ርስቱም ሆነ ሌሎቹ የጉራጌ ልኂቃን “የአማራ ፖለቲካ ለራሱም አልሆነ እንኳን ለእኛ ሊተርፍ ይቅርና!” ብለው ተስፋ ቢቆርጡበትና “አማራን በመተው አሰላለፋችንን እናስተካክል!” ቢሉ ፍርዳቸው ነው!!! ነገር ግን እንዲህ የሚሉ የጉራጌ ልኂቃን አንድ የሳቱትና ያልተረዱት ሀቅ አለ፡፡ ኦሮሙማም ሆነ ወያኔ የአማራ ጠላት የሆኑት የአማራ የሆነውን ሁሉ የራሳቸው ለማድረግ መሆኑን መረዳት አልቻሉም፡፡ የአማራ የሆነውን የራሳቸው ለማድረግ የፈለጉት ወያኔና ኦሮሙማ የጉራጌ የሆነውንም ለመውሰድ ጉራጌን እንደሚያጠፉ አልገባቸውም!!!
የአማራ የሆነውን ሁሉ ለራሳቸው ለማድረግ አማራን የሚያህል ኃያል ሕዝብ ባዕዳን የዚህችን ሀገር ጠላቶችን ከጎናቸው በማሰለፍና ብርቱ አቅማቸውን በመጠቀም አማራን ለማጥፋት በአማራ ላይ የተነሡ ወያኔና ኦሮሙማ አናሳ የሆናቹህትን እናንተን አጥፍተው የእናንተ የሆነውን ሁሉ የእነሱ ለማድረግ ይመለሳሉ ብላቹህ ማሰባቹህ ሲበዛ ቂልነታቹህንና የፖለቲካ መሃይምነታቹህን ያሳያል!!!
በዚሁስ ላይ የጉራጌ ሕዝብ አማራን መስሎ የሚኖረው “አማራ ፈጣሪን ፈሪ፣ ግፍ ተጸያፊ፣ ሀገር ሠሪ፣ ሕግ አክባሪ፣ ፍትሕ አዋቂ፣ ባለ ርእይ ሕዝብ …. ነው!” ብሎ ስለሚያምንና እንደ አማራ ሁሉ ሀገርን በመውደዱና ባለ ርእይ በመሆኑ ነው እንጅ “አማራ ጉልበት አለው እሱ ይጠብቀኛል እሱን ልጠጋ!” ብሎ ነው ወይ ጉራጌ አማራን መስሎ የሚኖረው??? እንዴት ነው ታዲያ ጉራጌ ሀገር አፍራሾችን፣ ሁሉንም ነገር “ለእኛ ብቻ!” ባዮችን፣ ዘራፊዎችን፣ ወንበዴዎችን፣ ሕሊናቢሶችን፣ ግፈኞችን፣ አረመኔዎችን ተጠግቶ ወይም ደግፎ ጥቅሙ ሊጠበቅለት የሚችለው??? ከሀገር አጥፊ ጋር መሰለፍ ወይም መተባበር ሀገርን መጉዳት ወይም መውጋት አይደለም ወይ??? የሀገርን ጠላትና ቀማኛን እንደምንም ብለው ተባብረው ያጠፉታል እንጅ ይተባበሩታል እንዴ???
መሰላቹህ እንጅ ወያኔና ኦሮሙማ እንኳን ለእናንተ ሊሆኑ ሊበጁ ይቅርና ገና እስር በርሳቸው የሚባሉበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ሌባ ሲሰርቅ ስለማይጣላ ነው አሁን ተስማምተው የሚዘርፉት፣ የሚገሉት፣ የሚያፈናቅሉት፣ የሚያወድሙት፡፡ እንደሚመኙት አማራ ቢጠፋላቸውና የአማራ የሆነውን ሁሉ መውረስ ቢችሉ ሲካፈሉ መጣላታቸውና ጭራሽ እንዲያውም አንዱ ሌላውን አጥፍቶ የሌላውንም ጠቅልሎ ለመውሰድ መነሣቱ የሚቀር አይደለም፡፡ ሌባ፣ ዘራፊ ወይም ወንበዴ ከዚህ የተለየ ተፈጥሮ የለውም፡፡ እንኳንና እናንተን ሊምሩ ይቅርና!!! እንደእነዚህ ዓይነቶችን አረመኔዎች ተባብሮ፣ ቆርጦና ጨክኖ መታገል ነው እንጅ የሚያስፈልገው እየተጃጃሉ ለመበላት መመቻቸት የከፋ ድንቁርና ነው!!!
እናም “አሰላለፋችንን ከግፈኞች፣ ከቀማኞች፣ ከዘራፊዎች፣ ከወንበዴዎች ጋር እናድርግ!” የሚለው እሩቅን የማይመለከት የጉራጌ ልኂቃን አስተሳሰብ የንቁውን፣ የእንቆቆውን፣ የብልሁን፣ የትጉውን፣ የአስተዋዩን፣ የታታሪውን የጉራጌን ሕዝብ ማንነት፣ አስተሳሰብና ፍላጎት ፈጽሞ የማይመጥንና የሚቃረን በመሆኑ በወንበዴዎች ተወስውሳቹህ በመታለል እንዲህ ዓይነት የደነቆረ ከንቱ አስተሳሰብ የያዛቹህ የጉራጌ ልኂቃን በጊዜ ይሄንን የደነቆረ አስተሳሰባቹህን ጥላቹህ ወደቀደመው አስተሳሰባቹህ ብትመለሱ የሚሻላቹህ ይመስለኛል!!!
መሰላቹህ እንጅ አማራ ቃልኪዳን ያለው ሕዝብ በመሆኑ ጠፍቶ አይጠፋም፡፡ ዛሬ ለአማራ እንዲህ ዙሪያው ገደል ቢሆንበትም ይብላኝላቸው ለጠላት ቅጥረኞችና ባንዶች ለእነ ወያኔና ኦሮሙማ እንጅ ቃልኪዳን ያለው ሕዝብ ነውና አምላክ በሚታደግበት መንገድ አማራን መታደጉ አይቀርም!!! ይሄንን አትጠራጠሩ!!!
አቶ ዐቢይ አሕመድ “አይደለም ክልል መሆን ከፈለጋቹህ ሀገር መሆንም ትችላላቹህ!” ያላቹህ የክልልነት ጥያቄያቹህን መያዣ በማድረግ ሊቆምርባቹህ ስለፈለገ ነው እንጅ ጥያቄያቹህን ሊመልስላቹህ ስለፈለገ አይምሰላቹህ፡፡ አዎ በእርግጥ ክልልነት ለጉራጌ ይገባዋል፡፡ ለጉራጌ ብቻ ሳይሆን የአገዛዙ ሕገ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ክልል የመሆን መብትን ለጠየቀ ሁሉ እንዲሰጥ ደንግጓልና ለ84ቱ ብሔረሰብና ጎሳ ሁሉ ክልልነት ይገባል!!!
በተደጋጋሚ እንደገለጽኩት የአገዛዙ ጎሳ ተኮር የክልል መዋቅር ጠንቀኛ ለሀገርና ለሕዝብ የማይጠቅም መሆኑን ማሳየትና ማስቀረት የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡ ዘጠኝ ክልል ሆኖ በድንበር ይገባኛል ጥያቄ እንዲህ እየተባላ የጎሳ ተኮር ክልል መዋቅር የማይጠቅምና መውደቅ ወይም መወገድ ያለበት መሆኑን መረዳት ያልቻለ ሕዝብና አገዛዝ ከ84 ተከፋፍሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማየትና የጎሳ ተኮር የክልል መዋቅር ምን ያህል ፀረ ሕዝብና ፀረ ሀገር መሆኑን ማየትና መረዳት አለበት፡፡ ሀ ብሎ ከፊደል መማር የተሳነው ዋ ብሎ ከመከራ ይማራልና፡፡ ስለሆነም ክልልነት ለሁሉም ብሔረሰቦችና ጎሳዎች መፈቀድ አለበት፡፡ የአገዛዙ ሕገመንግሥት እንደሚለው ሁሉም ብሔረሰቦችና ጎሳዎች ዕኩል መብት ካላቸው ክልልነት ለአንዱ ተሰጥቶ ለሌላው የሚከለክል ሊሆን አይችልም!!!
አቶ ዐቢይ አሕመድን የአንድነት ጠበቃ አድርጎ የሚጃጃለው ዘገምተኛው መንጋ ግን አቶ ርስቱ ይርዳው “ዐቢይ ‘ክልል መሆን አይደለም ከፈለጋቹህ ሀገር መሆንም ትችላላቹህ!’ ብሎናል!” ካለው ነገር የአቶ ዐቢይን ፀረ ኢትዮጵያነትና ፀረ አንድነትነት መረዳት ቢችል መልካም ነው!!!
Filed in: Amharic