ዘመድኩን በቀለ
*…በአቡነ ዮሴፍ የታሰረው የቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ …….!!!
*…. “በመስቀል አደባባይ አንጻር የኢድ አደባባይ ተብሎ እንዲታወጅ፣ ለእናንተ ለጴንጤዎችም “የወንጌል አደባባይ” ለፖለቲከኞችም “የአብዮት እና የብልጽግና አደባባይ ” ተብሎ በሕግ ተደንግጎ አደባባዩ እንዲጠራ ብለው የጠየቁ ሲሆን ከንቲባዋ ይሄን ከበላዮቼ ጋር ተማክሬ እንጂ ብቻዬን መወሰን አልችልም የሚል ምላሽ የሰጧቸው ሲሆን
*… ሁለተኛውን የካቲት 16/2014 ዓም በመስቀል አደባባይ “የሂጃብ ቀን” ተብሎ እንዲከበርና ራሷም ከንቲባዋ ሂጃብ ለብሳ እንድትገኝ ተነጋግረው ወስነው፣ የፈቃድ ወረቀታቸውን ተቀብለው መውጣታቸው ተሰምቷል
“…በቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማና ማኅተም ቋሚ ሲኖዶሱ ለከንቲባ አዳነች አቢቤ የጥሪ ደብዳቤ ተጽፎ፣ የቅዱስ ፓትርያርኩ እና የብፁዕ ዋና ጸሐፊው ፊርማና ቲተር ያረፈበት ደብዳቤ ፓራፍ ተደርጎ ለከንቲባዋ ይላክላት ዘንድ ወጪ ተደርጓል። ነገር ግን ብፁዕ ዋና ጸሐፊው ደብዳቤውን አፍነው ለከንቲባዋ ሳይልኩት በጽሕፈት ቤታቸው አፍነው ማስቀመጣቸውም ትናንት ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ የመረጃ ምንጮቼ አድርሰውኛል ብሎ መዘገቡም ይታወሳል።
“…ከውስጥ ከእኛ ሰዎች ጋር በመናበብ የልብ ልብ ተሰምቷቸው የሚፏልሉት ከንቲባ አዳነችም አቢቤም ትናንት ጠዋት “የቋሚ ሲኖዶሱ ቀጠሮ ተሰርዞ የጋራ ኮሚቴ ይቋቋምና በጉዳዩ ላይ እንመካከር” የሚል ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶሱ መላካቸውም መዘገቡ ይታወሳል። ደብዳቤውን አፍነው የያዙት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በግልጽ በ70 እና 80 ሚልዮን ኦርቶዶክሳዊ አማኞች እንብርት እና አንገት ላይ እንደቆሙ ሊያውቁት ይገባል።
“…በሌላ በኩል ከንቲባ አዳነች አቢቤ ነገሩን የበለጠ ለማጦዝ ሲሉ ጽንፈኛ አክራሪ የወሃቢይ እስላሞችን በቢሮዋ ጠርታ ” ዝም አትበሉ እንጂ፣ አግዙኝ እርዱኝ እንጂ” ብላ መማጸኗንና የከንቲባዋን መፍራት ያዩት ወሄዎችም አጋጣሚውን ለመጠቀምና ነገሩን ለማጋጋል፣ ከአንቺም ጋር አብሮ ለመቆም ለመታገልም የሆነ ፈቃድ ያስፈልገናል በማለት ሁለት ጥያቄዎችን እንዳቀረቡላትና አንደኛውን ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ልማከር፣ ከባድም ነው። ሕግም ምን እንደሚል መመልከት አለብን ሁለተኛው ጥያቄአችሁ ግን በእኔ የሥልጣን ማዕቀፍ ሥር ስለሆነ ፈቅጄላችኋለሁ በማለት እናም ፈቃዱንም እንደሰጠቻቸው ከከንቲባ ጽሕፈት ቤቱና ከወሄዎቹ መንደር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
“…ወሄዎቹ የተከለከሉት “በመስቀል አደባባይ አንጻር የኢድ አደባባይ ተብሎ እንዲታወጅ፣ ለእናንተ ለጴንጤዎችም “የወንጌል አደባባይ” ለፖለቲከኞችም “የአብዮት እና የብልጽግና አደባባይ ” ተብሎ በሕግ ተደንግጎ አደባባዩ እንዲጠራ ብለው የጠየቁ ሲሆን ከንቲባዋ ይሄን ከበላዮቼ ጋር ተማክሬ እንጂ ብቻዬን መወሰን አልችልም በማለት ሁለተኛውን ግን የካቲት 16/2014 ዓም በመስቀል አደባባይ “የሂጃብ ቀን” ተብሎ እንዲከበርና ራሷም ከንቲባዋ ሂጃብ ለብሳ እንድትገኝ ተነጋግረው ወስነው፣ የፈቃድ ወረቀታቸውን ተቀብለው መውጣታቸው ተሰምቷል።
“…ጉዳዩን ወደ ሃይማኖት ጦርነት ለመክተት መንግሥት ተግቶ እየሠራ ሲሆን በውጤቱ ግን የሚገኝ ትርፍ አይኖርም። ይመጣ ያለው እሳት ማንንም አያተርፍም። የፕሮና የወሄም ያልተቀደሰ ጋብቻ በደርቢ ጨዋታ በአንዱ አሸናፊነት ይጠነቀቃል። ኦርቶዶክስን ለመግደል ከወሄ ጋር ወጥሮ እየሠራ ያለው ፕሮም የማታ የማታ የማረድ ልምድ ባለው በወሄ ይዝረከረካል። ለማንኛውም ቅዱስ ሲኖዶስ ለከንቲባዋ የላከውና በአቡነ ዮሴፍ ቢሮ በቁም እስር ላይ የሚገኘው ደብዳቤ ይህን ይመስላል። ሼር በማድረግ ለሁሉ አዳርሱትም ተብላችኋል።
ለክብርት አዳነች አበቢቤ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
አዲስ አበባ
“…ጥር 1/2014 ዓም በመስቀል አደባባይ የተከናወነው ሁነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችንን እጅግ ያስቆጣ ድርጊት በመሆኑ በጉዳዩ ዙሪያ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ለመወያየት ዐርብ የካቲት 4/2014 ዓም ከረፋዱ በ4 ሰዓት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የቅዱስ ፓትርያርኩ ፊርማና ማኅተም
የብፁዑ ዋና ጸሐፊው ፊርማና ማኅተም አለው።
“…ሻሎም ! ሰላም !